ኦብነግ “በገዢው ፓርቲ ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው” አለ

ኦብነግ “በገዢው ፓርቲ ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው” አለ

ኦብነግ “በገዢው ፓርቲ ጥቃት እየተፈጸመብኝ ነው” አለ

የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ) የሶማሌ ክልልን ከሚያስተዳድረው ገዢ ፓርቲ “ብዙ ጥቃቶች እየተፈጸሙብኝ ነው” አለ። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከ50 በላይ የኦብነግ አባላት መታሰራቸውን አንድ የግንባሩ አመራር ተናግረዋል።

የኦብነግ የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ አህመድ መሐመድ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጠራው ስብሰባ ላይ ዛሬ እንደገለጹት፤ በሶማሌ ክልል በዶሎ፣ ቸረር፣ ሸበሌ እና ቆራሔይ ዞኖች በሚገኙ የድርጅታቸው አባላት ላይ የእስራት እና ሌሎችም ጥቃቶች ደርሶባቸዋል። ከታሰሩት አባላቶቻቸው ውስጥ ለመጪው ምርጫ ግንባሩን ወክለው የሚወዳደሩ ዕጩዎች እንዲያዘጋጁ የተላኩ ልዑካን እንደሚገኙበት አስረድተዋል።

“በዶሎ ዞን በዋርዴር የእኛ ቢሮ ተዘግቷል። ዕጩዎች እንዲያዘጋጁ የላክናቸው ሰዎች ደግሞ ከዞኑ ወደ ጅግጅጋ አምጥተዋቸው፤ ሰሞኑን ጅግጅጋ ታስረው ነው የነበሩት” ብለዋል። በቀድሞው የድርጅቱ ሊቀመንበር የተመራና ወደ ደገሐቡር የተጓዘ ልዑክም ወደ ከተማይቱ እንዳይገባ መከልከሉንም አክለዋል።

አንድ ድርጅት “መንቀሳቀስም ሆነ ዕጩ ማዘጋጀት ካልቻለ”፤ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር የስራ አስፈጻሚ አባሉ ገልጸዋል። ኦብነግ በምርጫው ለመሳተፍም ሆነ ላለመሳተፍ ገና ውሳኔ ላይ እንዳልደረሰም በንግግራቸው ጠቁመዋል።

“አሁን ሀገሪቱ ባለችበት ሁኔታ እኛ ምርጫውን ለመሳተፍ መገምገም አለብን። ሜዳው ነጻ አይደለም” ያሉት አቶ አህመድ፤ “አሁን ባለው ሁኔታ ሂዱና [ምርጫ] ተወዳደሩ ማለት፤ ሂዱና ተጣሉ ማለት ነው” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ለአቶ አህመድ አቤቱታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪል ማህበራት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለሙ ስሜ ምላሾችን ሰጥተዋል። የሰብሳቢዋን እና የኃላፊውን ምላሽ ከታች የተያያዘውን ቪዲዮ ተጭነው ይመልከቱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Ethiopia Insider


ደቡብ ሱዳን የሰፈረዉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት አባላት የነበሩ ኢትዮጵያዉን የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች« ለህይወታችን ያሰጋናል» በሚል ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለመፍቀዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ትናንት አስታወቀ።የድርጅቱ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት 169 የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊቶች በተለመደው አሰራር መሠረት ከጁባ እንዲወጡ ተደርገው በአዲስ ሰራዊት ይተኩ ነበር። ይሁንና 15 የሰራዊቱ አባላት ከጁባ ኤርፖርት ለመሳፈር ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ስቴፈን ዱጃሪክ « ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚያስፈልገው ማንኛውም ሰው ጥገኝነት የመጠየቅ መብት አለው።» ሲሉ መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ AFP ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ሁኔታውን “ተገንዝቦ” ጥገኝነት መጠየቅ በፈለጉት የሰራዊት አባላት ጉዳይ ላይ ከደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጋር እየመከረ ነውም ተብሏል።

1 Comment

  1. ONLF is not above the law. ONLF needs to get with the program, the TPLF era lawlessness is long gone, the future of Ethiopia only lets law abiding political parties operate legally.

Comments are closed.