ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተጠራ

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ ሕዝባዊ ውይይት ተጠራ

 (ethiopianreporter)—የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደር እንዲሁም የከተማና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩጥቅም ለመወሰን የተረቀቀውን የሕግ ሰነድ በዝርዝር ለመመልከት ሕዝባዊ ውይይት ጠሩ።

ሕዝባዊ የውይይት መድረኩ የተጠራው ለፊታችን ዓርብ ታህሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. መሆኑን፣ የሕግ ፍትሕና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ ጴጥሮስወልደ ሰንበት ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ውይይቱ የሚካሄደው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አዳራሽ እንደሚሆንና በጉዳዩ ላይ መሳተፍና አስተዋጽኦ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ኢትዮጵያዊመገኘት እንደሚችልም አስረድተዋል። ረቂቅ አዋጁ ለፓርላማው የቀረበው ለክረምት ዕረፍት ሊበተን ሁለት ቀናት ሲቀሩት በመሆኑ በጥድፊያ መፅደቅአይገባውም ተብሎ፣ ለ2010 ዓ.ም. የሥራ ዘመን መተላለፋን በወቅቱ መዘገባችን ይታወሳል።

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅም ለመወሰን የቀረበው ረቂቅ አዋጅ አስገዳጅ እንዲሆን የኦሕዴድ የፓርላማ አባላት በወቅቱ አስተያየት በመስጠት፣ለዝርዝር ዕይታ የሚመራለት ቋሚ ኮሚቴ ያነሱትን አስተያየት እንዲያጤን አሳስበው ነበር። የረቂቅ አዋጁ የተለያዩ አንቀጾች የኦሮሚያን ጥቅም የሚያስከብሩሳይሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የሚመስሉ አንቀጾችን የያዘ በመሆኑ አስገዳጅ ሊሆን ይገባል በማለት የክርክር ነጥቦችንአንስተዋል።

‹‹የኦሮሞ ሕዝብ ማንነት የሚያንፀባርቅ አሻራ በከተማው ውስጥ በቋሚነት እንዲኖር፣ ከክልሉ ሕዝብ ጋር በተያያዙ ታሪካዊ ክስተቶች ስም መታሰቢያዎችእንዲኖሩ አመቺ የሆኑ እንደ አደባባዮች፣ ጎዳናዎች፣ ሠፈሮችና የመሳሰሉት ቦታዎች እንዳስፈላጊነቱ በቀድሞ የኦሮሞ ስማቸው እንዲጠሩ ይደረጋል፤›› የሚለውን የረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 6(2) አስገዳጅ መሆን አለበት የሚለው ከተነሱት ነጥቦች መካከል አንዱ ነበር።

በሌላ በኩል በረቂቁ የተቀመጡትን የኦሮሞ ልዩ ጥቅሞች ለኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ለማቅረብ እንዲቻል አፋን ኦሮሞ በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ቋንቋ ሆኗልመባሉን የኦሕዴድ የፓርላማ አባላት የተቀበሉ ቢሆንም፣ የሥራ ቋንቋ እስከሆነ ድረስ እንደ አማርኛ በሁሉም የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች እንደ አንድየትምህርት ዓይነት እንዲሰጥ የሚል የማሻሻያ ነጥብ አንስተው ነበር። በተጨማሪም በከተማዋ በመንግሥት የሚሠራጩ የመገናኛ ብዙኃን በአፋን ኦሮሞጭምር የሚጠቀሙበት ሁኔታ ይኖራል የሚለውን የረቂቁን አንቀጽ 6(5) አስገዳጅ እንዲሆን የማሻሻያ ሐሳብ አቅርበዋል።

ከአካባቢ ብክለት የሚጠብቅ መብትን አስመልክቶ በተቀመጠው የረቂቁ አንቀጽ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ካሳ እንዲያገኙ ቢደነገግም፣ ጉዳቱን ባደረሰው ላይቅጣት እንዲጥል ጠይቀዋል፡፡ ረቂቁ በሰጠው ትርጓሜ የአዲስ አበባ ከተማ ወሰን ማለት የከተማው አስተዳደር ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚያደርገው ስምምነትተወስኖ ምልክት የተደረገበት ወሰን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ማለት ፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የምክር ቤቱ አባል አድሃኖ ኃይሌ (ዶ/ር) ይህ ዞን የት ድረስ እንደሆነ በአዋጁ እንዲካተት የሚል ሐሳብ ማቅረባቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።


“ተደናገርና” አለች አሉ ጸደናይ፤ የምትይዘው የምትጨብጠው ቢጠፋት ሳትዘጋጅ ድንገት የባሏን መርዶ ተረድታ። የብአዴንና የኦፒድኦ አንድ ላይ መቆም እንዲህ ያሸብራል ለካ! በአዲስ አበባ ጉዳይማ መጣላታቸው አይቀርም ከሚል ስሌት የቀረበች የውይይት ጥሪ። እነሃጎስ እንዲህ አይነት ትንንሽ ጭንቅላት ይዘው እስከዛሬ ስልጣን ላይ መቆየታቸው ግን አስገራሚ ነው። እነለማና ገዱ ይህች ሲሳይ ልታመልጣቸው አይገባም፤ አጀንዳውን ቀይረው መንግስት ለመቀየር መጠቀም ይኖርባቸዋል። ለምሳ ያሰቡንን ቁርስ ላይ በላናቸው አይደል መንጌስ ያለው?

Muluneh Eyoel


ይቺ ህዝብን ለማደናገር እና እያስቦካቸው ያለውን የኦሮማራ ትብብር ያፈርስልናል ብለው የመዘዟት የተበጫጨቀች ካርድ ናት። የህዝብ ለህዝብ ውይይት ይካሄድ ሲባል እምቢ ብለው አሁን የይስሙላ ውይይት በሙታኑ ፓርላማ በመከፈት ጭቅጭቅ ለመፍጠር አስበው ነው። ይህ ጉዳይ ጠለቅ ያለ የምሁራን ጥናት እንዲውህም ህዝባዊ ውይይት በማድረግ የሚፈታ እንጂ ወያኔ ከገበችበት ቀውስ የምትትነፍስበት ማስታገሻ መሆን የለበትም። ስለዚህ

Boycott

Jawar Mohammed