እፀገነት ከበደ ትባላለች። ብዙ ጊዜ እነ ዳንኤል ክብረት እና ጋሻ ጃግሬዎቹ በሚያዘጋጁት የግጥም ምሽት ላይ ፅሁፎቿን ተጋብዛ በማቅረብ ትታወቃለች።

እፀገነት ከበደ ትባላለች። ብዙ ጊዜ እነ ዳንኤል ክብረት እና ጋሻ ጃግሬዎቹ በሚያዘጋጁት የግጥም ምሽት ላይ ፅሁፎቿን ተጋብዛ በማቅረብ ትታወቃለች።

በዚህ ፅሁፏ አፋን ኦሮሞን “የወፍ ቋንቋ” ብላ ስታፌዝበት ትደመጣለች። አባይ ሚዲያም ይሄን ነውር እንደወረደ አስተላልፎታል። ልጅ እያለን ተወልደን ባደግንበት ፊንፊኔ (አዲስ አበባ) ይህ አባባል የተለመደ ነበር። ወላጆቻችን አፋን ኦሮሞ ሲያወሩ ብዙ አላዋቂዎች “ይሄን የወፍ ቋንቋችሁን ደግሞ ጀመራችሁ” ይሏቸው ነበር። ብዙ ሰው ማንነቱን ትቶ ሌላ ማንነት ፍለጋ እንዲሄድ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ጫና ይደርስበት ነበር። ዛሬም መድረክ ላይ ከ45 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሚናገረውን ቋንቋ የወፍ ቋንቋ ሲባል መስማት በእጅጉ ይገርማል። ሰሞኑን ከያኒና ገጣሚ ነን ባዮች ታዋቂ ለመሆን የጀመሩት አዲስ ዘዴ ደግሞ ህዝብን መዝለፍ ነው። እንዴት የወፍ ቋንቋ ትያለሽ ብትባል መች ብሄር ጠራሁ እንደምትል የሚጠበቅ ነው። ባለፈው ቢሾፍቱ በተካሄደ የመደመር ፍልስፍና ውይይት ላይ ደረጄ ገረፋ በዚሁ ጉዳይ ላይ ጠ/ሚ አብይን ፊትለፊት መውቀሱን ጭምጭምታው ደርሶናል። የዛሬ አመት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአካል ተገኝተው ቡራኬ የሰጡት “የነቁና የበቁ ከተሜዎች” የሚሳተፉበት የግጥም ምሸት በቋሚነት ኦሮሞና ኦሮሙማ ላይ የግጥምና መነባነብ ጦርነት ከከፈተ ሰነባብቷል። ኧረ ይሄ ነገር አያኗኑርም። ተዉ በሏቸው።
THE FINFINNE INTERCEPT

Finfinneetti irreecha kabajuun, sadarkaa injifannoon Oromoo irra gahe agarsiisa:

Obbo Shimallis Abdiisaa.