የኦሮሚያ ጸጥታ ቤሮ ሃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጀኔራል ከማል ገልቹ ስለ አብይና

እስከ ቀርብ ጊዜ የኦሮሚያ ጸጥታ ቤሮ ሃላፊ የነበሩት ብርጋዴር ጀኔራል ከማል ገልቹ ስለ አብይና ለማ የሚከተለውን ይላሉ:-

“ደብዳቤ ጽፎ ባንክ ሲያዘርፍ የነበረው ኦዴፓ ነው።”
“በንግግር ጋጋታና በቃላት ምርቃና ራሳቸውን ወንበር ለማጠናከር ከሆነ የሚያስቡት ሌላ የትግል እሳት ነው የሚያቀጣጥሉት።”

ጉለሌ ፖስት


የተፈጥሮ ሃብቱ ያለው ኦሮሚያ ውስጥ ነው። የሚፈራረመው የአዲስ አበባ ከንቲባ። ፕሮጀክቱ #በዋናነት ተጠቃሚ የሚያደርገው የአዲስ አበባ (በተለይም የጉለሌና የካ) ነዋሪዎችን ነው። የአካባቢውን አርሶ አደር ህዝብ ግን #እግረመንገዳችንን ተጠቃሚ እናደርግሃለን ይሉታል። የከንቲባው ፅ/ቤት እቅዱን የገለፀበት መንገድ ራሱ ስድብ ነው። ፕሮጀክቱ #በዋነኝነትየታሰበው ለእከሌ ነው ግን አርሶ አደሩም እግረ መንገዱን ተጠቃሚ ይሆናል ነው እያለ ያለው። የፊንፊኔ ዙሪያ አርሶ አደሮች ግን መቼ ነው በዋናነት እነሱን ማእከል ያደረገ ፕሮጀክት የሚነደፍላቸው? በዛ ላይ እግረ መንገዳችንን ተጠቃሚ እናደርጋችዃለን ይበሉ እንጂ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ አርሶ አደሩን ዞር ብሎ የሚያየው የለም። ወደ አዲስ አበባ የሚሄደው የውሃ ማስተላለፊያ pipe በደጁ ተዘርግቶ የወንዝ ውሃ መጠጣቱን ይቀጥላል። ከሁሉም በላይ ግን በየትኛው የህግ አግባብ ነው የከተማ መስተዳደሩ በኦሮሚያ resource ተጠቃሚ ለመሆን የብዙ ቢሊዮን ብሮች ፕሮጀክት የሚፈራረመው? ስራውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሰርቶት የከተማው መስተዳድር ወሃውን የአዲስ አበባ ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆን ከፈለገ ከንቲባ ታከለ ኡማ ከሽመልስ አብዲሳ ጋር ተደራድሮ ስምምነት ላይ ሲደርስ ነው ውሃውን ለከተማው ማሰራጨት ያለበት።