“ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የግብፅ ፓርቲ ብልፅግና ነው፡፡

መከላከያን የማፍረስ ሂደትም በይፋ ተጀመረ ማለት ይሆን…?
#abiy_must_be_removed.

“ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የግብፅ ፓርቲ ብልፅግና ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ልንገርህ፡፡ ዋሽንግተን ላይ ሲደረግ የነበረው ክርክር በስንት አመት እንሙላው የሚል ነው፡፡ በ20 ዓመት ይሞላ ወይስ በ7 ዓመት ይሞላ ነው፡፡ የቴክኒክና የኦፕሬሽን ድርድር ነው የነበረው፡፡ በመሀል ለግብፅ 40 ቢልዮን ኩዩቢክ ሊትር ውሃ እንስጥ 31 ቢልዮን እንስጥ የሚለውን ጉዳይ ማን አንሱ አላቸው? ይህንን ጉዳይ እንዲያነሱ የገፋፋቸው ማን ነው? ያውም በዋሽንግተን! አሜሪካ አደራዳሪ መሆን በሌለባት፤ የአፍሪካ ጉዳይ በአፍሪካውያን መፍታት ሲገባው፤ የናይል ጉዳይ በናይል ተፋሰስ ሀገራት መፈታት ሲገባው ጉዳዩን ወደ ዋሽንግተን የላከው ማን ነው? ለግብፅ 40 ቢልዮን ኩዩቢክ ሊትር እሰጣለሁ ብሎ ተስፋ የሰጠው ማን ነው? የውጭ ሀገራት መንግስታት 7 ቢልዮን ብር ሊሰጡን ነው፤ እርሱን ካጣን ብልፅግናችን ይቀረብናል ብለው ነው ወደዚህ ችግር የገቡት፡፡ አሁን ስለ መሸጥ እናውራ? ባንዳነት እናውራ? ስለሱ ማውራት ካለብን 7 ቢልዮን ብር ካልመጣልን ብልፅግናችን ይደናቀፋል ብሎ፣ ብልፅግና የሚባለው ፓርቲ ምናባዊውን ብልፅግና ለማምጣት ሲል ግድቡን የሸጠው የብልፅግና ፓርቲ መሪ ነው፡፡ ስለዚህ ማንም በማንም ላይ ጣት መቀሰር አይችልም፡፡ የብልፅግናው መሪ በማንም ላይ ጣት መቀሰር አይችልም፡፡ አንደኛ የተበላ ነው፤ ሁለተኛ በሚገባ የተመዘገበ ነው፡፡”

~ፕሮፌሰር ህዝቅኤል ገቢሳ ለTMH ከሰጡት ትንታኔ የተወሰደ።