ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስትና ወታደር ተለያይተዋል?በመላዉ የአለማችን ክፍል መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸዉ። Secular government ይሉታል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስትና ወታደር ተለያይተዋል?

በመላዉ የአለማችን ክፍል መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸዉ። Secular government ይሉታል። ኢትዮጵያ ዉስጥም ለስሙ እንደዚያ ይባል እንጂ መንግስትና ሃይማኖት ጥንትም ሆነ ዛሬ እጅ እና ጓንት ናቸዉ። መንግስትና ወታደር ሲለያዩ ግን ምን ይባላል?

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከጥቂት አመታት ወዲህ መንግስትና ወታደሩ የተለያዩ ይመስላል። HD ሕገ መንግስቱ በሚያዝለት መሰረት የጦሩ የበላይ አዛዥ /Commander-in- chief/ ሆኖ ሳያዉቅ ራሱን አሰናበተ። ከHD በኋላ ለዉጦች ቢኖሩም የዚህ የመንግስትና ወታደር የመለያየት ምልክቶች /symptoms/ አሁንም እየታዩ ነዉ።

በሰለጠነዉ አለም አንድ የታጠቀ የመንግስት ወታደር ያለምክንያት የሰዉ ሕይወት ካጠፋ የአእምሮ በሽተኛ ካልሆነ በስተቀር የአገር ደህንነት ሓላፊዉ ወይም የመከላከያ ሚኒስትሩ በገዛ ፈቃዱ ሥልጣኑን ይለቃል። ሕገ ወጥ ታጣቂዎች እንኳን በጅምላ የሰዉ ሕይወት ካጠፉ የአገር ደህንነት ኃላፊዉ ሥልጣኑን ይለቃል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከወደ መቀሌ የሚሰማዉ ዜና ግን በጣም አስገራሚ ነዉ። ለብዙ ሺህ ዜጎች ሕይወት መጥፋት በወንጀል የሚፈለገዉ እንደ ጌታቸዉ አሰፋ ዓይነት ሰዉ የህወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኖ ተሹሞና ተሸልሞ እንደገና ነፍስ እንደዘራ ይነገራል።

ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉት ወደ አንድ ሚሊዮን ለሚጠጋ ዜጋ መፈናቀል ምክንያት የሆኑት የኮንትሮባንድስት ጄኔራሎች ተጠያቂ እንደመሆን ፈንታ ባለ አራት ኮከብ ጄኔራል ሆነዉ ይሾማሉ።

አሁን ደግሞ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ በታጠቁ ኃይሎች ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ የኦሮሞና የአማራ ዜጎች ሲፈናቀሉ መንግስት ዝምታን መርጦ ለእነዚህ ዜጎች በወቅቱ አልደረሰም። የፈፀመዉ ወታደሩ ወይም ታጣቂ ኃይሉ ስለሆነ እኔን አይመለከተኝም ዓይነት ዝምታ።

ከሥር የሚታየዉ ፎቶ በመንግስት ዝምታ የተበሳጩ የአከባቢዉ ቄሮዎች ተፈናቃዮቹን ለመርዳት ወደ ቦታዉ ሲንቀሳቀሱ ያሳያል። መንግስት ሁልጊዜ ምላሽ የሚሰጠዉ ወሬዉ ከአለም ከጫፍ እስከ ጫፍ ከተሰማ በኋላ፣ በማስ ሜድያ ተወርቶ ካለቀ በኋላና በጥያቄም ሲጣደፉ ብቻ ነዉ። ይህ ደግሞ የለዉጥ ኃይሉ መምራት አልቻለምና ወደ ቦታችን እንመለስ ለሚሉት አምባገነኖች በር እንደመክፈት ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ መንግስትና ወታደር የተለያዩ ናቸዉ ወይ ያሰኛል።

Dandana Bafkane