27 ዓመት የመንግሥት ሥልጣን ይዛችሁ ቆይታችኋል። ኢትዮጵያ ከናንተ በጣም ብዙ ..

27 ዓመት የመንግሥት ሥልጣን ይዛችሁ ቆይታችኋል። ኢትዮጵያ ከናንተ በጣም ብዙ በተሻለ ሀገር መምራት የሚችሉ ዜጎች አሏት። ብዙዎቻችሁ የመቃብራችሁን አፈር በቅርብ ርቀት እያሸተታችሁ ባላችሁበት በዚህ ወቅት እንኳን ሥልጣን ላለመልቀቅ እየተንገታገታችሁ መሆኑን ስናይ በጣም ያሳፍራል ፣ ያሳዝናልም። የቀረችዋን እድሜያችሁን እረፍት ወስዳችሁ በእፎይታ አሳልፏት። እረፍት ካልፈለጋችሁም ከመንግሥት ሥልጣን ውጭ ሌላ ሥራ ለመስራት ሞክሩ

በናንተ የተነሳ ኢትዮጵያ የማያባራ ግጭት ውስጥ መግባት የለባትም። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም መደፍረስ የለበትም። በናንተ የተነሳ እርስ በርስ መተላለቅ የለብንም። በሕዝባዊ አመጽ ሥልጣን እንድትለቁ ሲደረግ አርቃችሁ የሰራችሁት እስር ቤት መኖሪያችሁ ሊሆን እንደሚችል መዘንጋት አይገባችሁም። “ሥልጣን እስከምሞት” ከሚለው የአፍሪካ መሪዎች ልማድ ራሳችሁን ማላቀቅ ይገባችሗል።

ወጣቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በነፃነት ይስራበት ዞር በሉለት። ዶክተር አብይን የተሻለ ሊያግዙት የሚችሉ የኦሮሞ የአማራ የተጋሩ የጉራጌ የሲዳማ ወዘተ የተማሩ ወጣቶች እንዳሸን አሉ። እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የመፍትሔው አካል ለመሆን ደፈር በሉ። እናንተ ባይሰለቻችሁም እኛ ሰለቻችሁን።
Dhábasá Wakjira Gemelal

More evidences for violating Oromia regional state’s constitution.
Fact: The official language of Oromia state is Afaan Oromo.

Violating Oromia regional state constitution-
Fact: the state official language is Afaan Oromo