ኢትዮጵያዊነት በቴዲ አፍሮ የታሪክ-መነጽር!!

ኢትዮጵያዊነት በቴዲ አፍሮ የታሪክ-መነጽር!!

ዮሴፍ ሙሉጌታ ባባ, PH.D.

ከሁለት ቀን በፊት ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ‹‹ቴዲ ለምን ይወደዳል?–ኢትዮጵያዊነት በአንጻረ ጎሰኝነት›› በተሰኘ መጣጥፋቸው ውስጥ የሚከተለውን ሐሳብ አስፍረው ነበሩ፡-

[ቴዎድሮስ ካሳሁንን እና ሙዚቃውን ለምን ህዝብ ይወዳቸዋል?” ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስእሱ እና ሙዚቃው ኢትዮጵያዊነትን ስለሚዘምሩ ነው፤የሚል ነው። በሌላ አነጋገር፥ ጎሰኝነትን ስለማያራምዱ ነው።]

ይህ የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መልስ ውሃ አይቋጥርም። ጥያቄው መሆን የነበረበት ‹‹የቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ሥራ ለምን  በሁሉም ኢትየጵያውያን ዘንድ እኩል ተቀባይነት የለውም?›› የሚል ሲሆን፣ ትክክለኛው መልስ መሆን የነበረበት ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ የሚንረዳበት እና የሚንተነትንበት መንገድ የተለያየ የልቡና ውቅር እንድኖረን ስላደረገ ነው›› የሚል ይሆናል። ‹‹የኢትዮሮፒያንስ የአስተሳሰብ ቅሬ›› በተሰኘ የፍልስፍና ሥራዬ ውስጥ ይህንን ሐቅ እንደሚከተለው አስፈረው ነበር፡-

‹‹ጥቁር ሰው›› የተሰኘ የታዋቅው የሀገራችን ፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ የቴዲ አፍሮ አልበም በሁሉም ኢትየጵያውያን ዘንድ እኩል ተቀባይነት አላገኘም። የዝህ ችግር ዋና ምንጭ ደግሞ የሀገራችንን ታሪክ የሚንተረጉምበት መንገድ ሲሆን፣ ቴዲ አፍሮ አፄ ሚኒልክን የተመለከተበት የታሪክ-መነጽር ትክክል እንዳልሆነ ያረጋገጡ ብዙ ሰዎች በዘፈንና በጹሑፍ አጸፋዊ-ምላሽ ሰጥተዋል። ከቴዲ ዘፈን ጋር በተያያዘ አንዳንድ የቅርብ ጓደኞቼ ‹‹አፄ ሚኒልክ ጅግና ወይስ ጨካኝና አረመኔ?›› የሚል ግልጽ ጥያቄ አቅርበውልኝ ነበር—በእኔ ምላሽ ውስጥ ከተካተቱ አንኳር አንኳር ነጥቦች መከካል…!

‹‹በመጀመጀመሪያ ደረጃ፣ ለሰው ልጅ ታሪክ አንድ ወጥ ትርጉምና ትንተና ብቻ መስጠት የአንድን ሀገር ወይም ሕዝብ ታሪካዊ እውነታ ማዛባት ይሆናል። በተለይ፣ ስለ አንድ ሰው ጀግንነት ወይም ጨካኝነት የሚወስነው የእኛ የሥነ-ልቦና ውቅር እና ቅድሜ-ግንዛቤ መሆኑ ልብ ማለት ያሻል። ለምሳሌ፡- አንድ ቋንቋ እና ባሕል (ማንነት) የሚጋሩ የሸዋ እና የአርሲ (ሐራርጌ) ኦሮሞዎች የኢትዮጵያን ታሪክ የሚተነትኑበት መንገድ አንድ ሊሆን አይችልም። እዝ ላይ ዶ/ር መረራ ጉዲና የሸዋ ኦሮሞ ታሪክን፣ ፕ/ር መሐመድ ሐሰን ደግሞ የሐራርጌ (የአርሲ) ኦሮሞ ታሪክን ልወክሉ ይችላሉ! እነኝህ ሁለት ምሁራኖች ስለ አፄ ሚኒልክ ያላቸው አመለካከት አንድ የሚሆንበት መንገድ የለም፤ ምንም እንኳ የሚስማሙበትአንድ አንድ የታሪክ እውነታዎች ብኖሩም!

የዝ የታሪክ አረዳድ ልዩነት ምንጭ ምንድን ነው? መልሱ በጣም ቀላል ነው፡- አፄ ሚኒልክ የዛሬይቷን ኢትዮጵያ በፈጠሩበት ወክት ከሸዋ ኦሮሞ እና ከአርሲ ኦሮሞ ጋር የነበራቸው የታሪክ ግንኙነት አንድ አልነበረም። የበለጠ ግልጽ ለማድረግ፣ አብዛኛው የሸዋ ኦሮሞ (ጐባና ዳጨን ልብ ይሏል) የዛሬይቱን ኢትዮጵያ መንግስታዊ ግዛት በመፍጠር በኩል ከአፄ ሚኒልክ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሰርቷል። የአርሲ ኦሮሞ ታሪክ ግን ከዝ ይለያል። የአርሲ ሕዝብ የኢትዮጵያ አካል የሆነው በፍላጎቱ ሳይሆን በአፄ ሚኒልክ ሾተል ነበር። ይህ መካድ የማንችለው የታሪክ ሐቅ ነው።

ይህ ታሪካዊ ክስተት ነው እንግድህ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ አፄ ሚኒልክ የተለያየ የልቡና ውቅር እንድኖረን ያደረገው። በተለይ፣ የብሔር ጥያቄ ጡዘት ላይ በደረሰበት በአሁኑ ወክት አፄ ሚኒልክን የሚንረዳበትና የሚንተርጉምበት መንገድ በጣም ግልጽ እየሆነ መቷል። ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህንን ጉዳይ በማያሻማ ቋንቋ እንድ ስል አስፍሮ ነበር፡- ‹‹የዛሬይቷን ኢትዮጵያ መንግስታዊ ግዛት ፈጠሩ የሚባሉ ምንልክን፣ አንዳንዶች ያለምንም ጭንቀት ዘላለማዊ ጀግና አድርገው ሲያቀርቡ. ለእንዳንዶች ደግሞ ጨካኝ ቅኝ ገዥ ናቸው።የበለጠ ግልፅ ለማድርግ፤ በአማራ ልሂቃን ዘንድ በአድናቆት እንደ ዘላለማዊ ጀግና ሲታዩ፣ በኦሮሞና የሱማሌ ክልል ልሂቃን አረመኔ ቅኝ ገዥ ሆነው ይታያሉ። በትግራይ ልይቃን (ኤርትራዊያንን ጨምሮ) አካባቢም ኤርትራን ለጣሊያን የሸጡና ትግራይን ለብሔር ጭቆና የዳረጉ ግፈኛ መሪ ተብለው ይወሰዳሉ።›› (መረራ ጉዲና፣ የኢትዮጵያ የታሪክ ፈተናዎች እና የሚጋጩ ህልሞች፣ ገጽ. 13)

ከዝ አንፃር ካየነው ‹ጥቁር-ሰው› የተሰኘ የቴዲ አፍሮ ዘፈን አንዱን ወገን ብያስከፋና ሌላውን ደግሞ ቢያስፈነጥዝ አይገርምም። ለዝ ነው ዶ/ር መረራ ራሱ ‹‹በነዝህ አመለካከቶች ላይ ስምምነት መፈለግ ሲያንስ አስቸጋሪ ሥራ ነው፣ ሲበዛ ደግሞ የፖሊቲካ የዋህነት ይመስለኛል›› የሚለን!

ይህ በእንድ እንዳለ ‹‹ያኖሌ ጡት ቆረጣ አልነበረም›› በማለት የሚከራከሩ አንዳንድ ሰዎች አልጠፉም። ለምሳሌ፡ በ-በእውቀቱ ሥዩም ‹‹ከአሜን ባሻገር›› ሥራ ውስጥ እንድ የሚል ሐሳብ ሰፍሮ ይገኛል፡-

«ባጠቃላይ በሚኒልክ ተፈጸመ የተባለው ያኖሌ ጡት ቆረጣ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሰነዶች ላይ ያልተመሰረተ ለመሆኑ ይህ በቂ ማስረጃ ይመስለኛል። በአርሲ ታሪክ ዋና ባለሙያ የሆነው ፕሮፌስር አባስ ገነሞ በመጽሀፉ ውስጥ ጡት ቆረጣ መፈጸሙን የሚያሳይ አንድም የታሪክ ሰነድ ማቅረብ አልቻለም»

አፈንዲ ሙጠቂ ግን በ“በጨለንቆ ጦርነት አልተካሄደም” ስለሚባለው ጉዳይ እንድ ስል ይሞግታል፡-

‹‹እምዬ ምኒልክ ለናንተ መሲሕ ሊሆን ይችላል፡፡ እኛ የምናውቀው ምኒልክ ግን ሌላ ነው፡፡ ብዙ መናገር አያስፈልግም፡፡ ምኒልክ በጨለንቆ ጦርነት ያሻውን ከሰራ በኋላ የጻፈውን ደብዳቤ እንድታነቡት ጋብዘናችኋል፡፡ ደብዳቤው የተጻፈው ለእውቁ ሀገር አሳሽና ነጋዴ ለካፒቴን ጁልስ ቦሬሊ ነው፡ ደብዳቤው በሌሎች መጻሕፍት ውስጥም ይገኛል። ደብዳቤው “ሰውን ሁሉ ፈጀሁት” ነው የሚለው፡፡ የምሥራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦችም (ኦሮሞ፣ ሀረሪ፣ ሶማሊ፣ አርጎባ ወዘተ..) በጦርነቱ የተሳተፈ ሰው በደህና እንዳልተመለሰ ነው የሚገልጹት፡፡ “በጨለንቆ ጦርነት አልተካሄደም” የሚሉ ሰዎች አሉ (ከነዚህ ሰዎች አንዱ ኤዱዋርዶ ባይኖሮ መሆኑ ያስገርማል )፡፡ እነዚህ ሰዎች ሐቁን ለማወቅ የሚሹ ከሆነ ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሤ የጻፉትን “ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ” ማንበብ ይኖርባቸዋል፡፡ መጽሐፉን ካላገኛችሁት እውቁ ደራሲ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ የጻፉትን “አፄ ዮሐንስ እና የኢትዮጵያ አንድነት” የተሰኘ መጽሐፍ ከገጽ 291 እስከ 294 አንብቡት፡፡ ከባድ ጦርነት ተካሂዶ እንደነበረ በግልጽ ጽፈዋል፡፡ ምኒልክ ከጦርነቱ በኋላ በምሥራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የፈጸሙትን ደግሞ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ካውክ እና ፕሮፌሰር ሙሐመድ ሐሰን በሰፊው ጽፈውታል፡፡ በወቅቱ በሀረር ከተማ ይኖር የነበረው አርተር ራምቦም ለታሪክ ባስቀረው ዝነኛ ደብዳቤው ያየውንና የሰማውን ጽፏል።››

እነኝህ ሁለት ወጣቶች የተለያየ የታሪክ አረዳድና ትንተና ብኖራቸውም ቅሉ፣ ለአሁኑ ትውልድ ግን ተመሳሳይ መልዕክት አላቸው፡-

«የሁላችንም አባቶች የሁላችንም ጌቶች በፈረቃ ግፍ መፈጸማቸው በታሪክ ተመዝግቧል። በዘመናችን የምሬትንና የቂም በቀል ፉከራን ርግፍ አድርገን ትተን በሚያቀራርቡ በሚያስተባብሩ ሀሳቦች ላይ ከተጠመድን ከአባቶቻችን የተሻለ አለም እንደምንፈጥር ጥርጥር የለኝም» —በእውቀቱ ሥዩም

‹‹አሁን ሁሉም አልፏል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ታሪክ የተፈጸመው እኛ ከመወለዳችን በፊት ነው፡፡ እኛ የዚህ ዘመን ልጆች እንደመሆናችን ከሌሎች ጋር በፍቅርና በሰላም ኖረናል፡፡ በዚህ ዘመን ከኢትዮጵያ ተገንጥለን ነፃ መንግሥት እንመሰርታለን ብለን አናስብም፡፡ የሚሻለው ነገር ሁሉም ተባብሮ የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠር ነው፡፡ የሁሉም ህዝቦች ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋ፣ ኢኮኖሚ ወዘተ ተከብሮ ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባትን ኢትዮጵያን ለማየት እንፈልጋለን፡፡ ከሌሎች ጋር የምንኖረውም በዚህ እምነትና ተስፋ ነው፡፡››—አፈንዲ ሙጠቂ

አብዛኞቻችን የአንድ ዘመን ትውልድ ልጆች ቢንሆንም፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያለን አመለካከት አራምባና ቆቦ እየሆነ መቷል። ሀገራችን ስላለችበት ተጨባጭ ሁኔታ የጋራ ግንዛቤ ያላቸው እንደ አፈንዲ እና በእውቀቱ ያሉ ወጣቶች በየቦታ መኖራቸው፣ ሀገራችን ኢትዮጵያን ከእጅ-አዙር-ቅኝ-አገዛዝ ይታደጋታል የሚል ተስፋ አለኝ።

ዋቃዮ ብሔራዊ መግባባት ላይ መድረስ እንድንችል ይርዳን!

ኢትዮጵያ እና ብሔር ለዘለዓለም ይኑሩ!

2 thoughts on “ኢትዮጵያዊነት በቴዲ አፍሮ የታሪክ-መነጽር!!

  1. There are diverse criticisms of Teddy Afro’s new songs. Some claim that the quality of his songs are declining, and few have given their reservations with expert opinions.

    Others claim that Teddy Afro’s music is untimely. It feeds into the propaganda of the TPLF/EPRDF regime by adding to an empty bravado that defy the reality of Ethiopia, where innocent people are massacred, tortured, and abused in every corner of the country 24/7. They expected big and transformative music like Bob Marley of Ethiopia “Get up Stand up” that have been a theme for people who struggle for justice and freedom around the world to challenge the barbaric regimes. In short, Teddy’s new music is a move back to the Dergue era in its political set-ups and propaganda about Ethiopia-nothing new-we heard it before. The claim that his music pose a challenge to the TPLF/EPRDF regime by propagating unity is far-fetched-even untrue. The praising group of the new music forget that TPLF leaders are conducting same rhetoric to whitewash their killings and tortures in Oromia, Ogaden, Amhara, Gambela, etc. regions. Teddy’s songs don’t defy the regime’s trend. It kow-tows its agenda of whitewashing the ugly side of Ethiopia. It’s not a revolutionary message at all.

    Blessed be artist Yihune Belay, who put in crystal clear terms about the tragedy of Ethiopians, who kill each other like rabid dogs. Ethiopia can better grow by addressing the ugly side of Ethiopia’s political culture than feeding us empty bravado. Ethiopia has become the mare of savagery and famine. Admit it to change it.

  2. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when 5-6 yearold kids are killed by Ethiopian savages ordered by Ethiopians. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when 8 month pregnant mothers are killed by Ethiopians. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when thousands of young men are tortured and castrated by Ethiopians. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when the pile of rubbish bury hundreds of Ethiopians alive. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when millions of Ethiopians are evicted from their ancesteral lands and become homeless beggars. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when millions of Ethiopians starve and rely on other countries to exist. I cannot dance to the greatness of Ethiopia when thousands of Ethiopians run away from Ethiopia and perish in Arabian and African deserts and waters. Many more tragedies! I am real and choose to live in the real world of Ethiopia. I cannot join your myths of Ethiopia. You cannot perscribe me your egos and pride on falsehood. I cry for Ethiopia and Ethiopians. I feel ashamed and extremely sad. ? I am in No mood for the dance to the tunes of the greatness of Ethiopia and Ethiopians. I am tired of lying. I am tired of our dishonesty.

Comments are closed.