Ethiopia: ኢትዮጵያና ሕዝቧ በወታደራዊ ጄኔራሎችና በደህንነት ሹሞች እጅ ወድቀዋል።

Ethiopia: ኢትዮጵያና ሕዝቧ በወታደራዊ ጄኔራሎችና በደህንነት ሹሞች እጅ ወድቀዋል።

የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት ሕገወጥነቱን ላለመነጠቅ የሚታገለው የጀኔራሎችና የደህንነት ሹሞች ቡድን ሃገሪቷን ከገደል አፋፍ አቁሞ በኣፈጢሟ ሊደፋት እየተሯሯጠ ነው። በኢትዮጵያ የሲቪል አስተዳደር ለሚዲያ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር ከበፊቱ የታመመው አሁን ሞቷል።

በሃገሪቱ መደረግ ያለበት መገደል ያለበትን መታፈን ያለበትን መወረር ያለበትን ቀጥታ መመሪያ ሰጥተው የሚያስደበድቡ የሚያሳፍኑና የሚያስገድሉ ወታደራዊና ደህንነታዊ መዋቅሮች የኮማንድ ፖስት ተብሎ የተጠፈጠፈውን አፋኝ ቡድናቸውን ለስራቸው ሲጠቀሙበት አግዓዚ የተባለውን ባለ ቀይ ኮፍያ ሲሻቸው የፌዴራል ካሻቸው የክልል ፖሊሶችን ከፈለጉም የራሱን ዩኒፎርም አስለብሰው ዜጎችን በገዛ ምድራቸው በጥይት እየፈጇቸው ነው።

ስለመብቱና ነጻነቱ የሚታገለውን የኦሮሞን ሕዝብ ለመበቀል ሆን ብለው ባበጁት መንገድ በሶማሌ ክልል ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል የፈጸሙት ወታደራዊ ጄኔራሎችና የደህንነት ሹሞች ሃያ አምስት ሺህ የሚጠጉ የሕወሃት አባላት በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ እንዲሰማሉ በሶማሌ ክልል ለማስፈር ዝግጅታቸውን እያካሄዱ ነው።

የሃገሪቷ ኢኮኖሚ በባለስልጣናት ከመመዝበሩም አልፎ ሕገወጥ ስራዎችን በማበረታታት በኢኮኖሚ ላይ ባለስልጣናት ሽብር እየፈጠሩ ይገኛሉ። እጅግ አደገኛ መስመር የሚከተሉትና ቅኝ ገዢ ነጮች የማይሰሩትን ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኙት ወታደራዊ ጄኔራሎችና ደህንነቶች ስራቸው ስለተባነነበት ወደ መፈንቅለ መንግስት እንደሚያመሩ የታወቀ ጉዳይ ነው። ይህንን እና መሰል መንግስታዊ ሽብር እያስተናገዱ የሚገኙት ሃገር እና ሕዝብ የተረገሙ ክፉዎችን በጀርባው ማዘል ስለደከመው ትግሉን ተያይዞታል። እኛም በጠንካራው አለንልህ ልንለው ይገባል።

Via: MinilikSalsawi