ኢሕአዴግ ስብሰባና ከፍፍል !

ኢሕአዴግ ስብሰባና ከፍፍል :የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በግንባሩ አባል ፓርቲዎች መካከል ያለዉን ልዩነት የሚያጠብ፤ ፖለቲካዊ ቀዉሶችን የሚያረግብ እና ሠላም የሚያረጋግጥ እርምጃዎች መዉሰድ እንደሚገባዉ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ አዋቂዎች አሳሰቡ።

ኢሕአዴግ በይፋ አምደ መረቡ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዉ ስብሰባ ትናንት እንደሚጀመር አስታዉቆ ነበር። እስከ ዛሬ ቀትር ድርስ ግን ሥብሰባዉ አለመጀመሩን በስልክ ያነጋገርናቸዉ የስብሰባዉ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል። የገዢዉ ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ የሚደረገዉ ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በግጭት፤ ዘረፋ እና ሁከት በተመሰቃቀለችበት፣ በኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል አለመተማመንና ልዩነት በጎላበት ወቅት ነዉ። ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እንዳሉት ተሰብሳቢዎች በሐገሪቱ ዉስጥ ያሉ ችግሮችን እና መንስኤዎቻቸዉን በግልፅ ተወያይተዉ መፍትሔዎችን ማስቀመጥ አለባቸዉ። በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ ረዳት ፕሮፌሰር አቶ የማነ ዘርዓይ በበኩላቸዉ የአሁኑ ስብሰባ በአባል ፓርቲዎች መካከል ክፍፍል እና አለመተማመን የሚታይበት ነዉ። በተለይ በሕወሐት እና በኦዴፓ፣ በሕወሐት እና በአዴፓ መካከል «የሚታየዉ ልዩነት» ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ ነዉ። አቶ የማነ እንደሚሉት ክፍፍሉ «ኢሕአዴግ አለ ወይ?» የሚል ጥያቄ እስከ ማስነሳት ደርሷል።
ምንጭ፦ DW Amhariዶ/ር ለማ መገርሳ ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ሄዱ – lemma megersa, Dr. abiy ahmed


Shukshukta (ሹክሹክታ) – የተቀበረው ዶሴ ውዝግብ | Workneh Gebeyehu | Dr Abiy Ahmed | TPLF