ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ጀመረ – Amharic VOA News

ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ጀመረ – Amharic VOA News

ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ጀመረ

(Amharic voa news) -ኢህአዴግ ከሌሎች ሃያ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ለማካሄድ በሚረዱ አሰራሮች ላይ ለመወሰን የሚያስችል ስምምነት ደረሰ።

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ የሥነምግባር ደምቡን ካልፈረሙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ሲወስን ከዓመታት ወዲህ ይህ የመጀመሪያ መሆኑ ነው።

ለቅድመ ድርድር ውይይቱ የተሳተፉ የአንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራር አባላት ድርድሩ ዛሬ በተጀመረበት አቅጣጫ የሚሆን ከምሆነ “ልዩ” ይሆናል ብለዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የገዥው ፓርቲ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በኢትዮጵያ ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተደራጅተው በሕጋዊ መንገድ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ፓርቲያቸው ለመደራደር ዝግጁ እንደሆነ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርገዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።