አፋን ኦሮሞን የፌዴራል የስራ ቋንቋ ለማድረግ ጥቅም:….

አፋን ኦሮሞን የፌዴራል የስራ ቋንቋ ለማድረግ ጥቅም

አዲስ አበባ ውስጥ በየትኛውም ትምርት ቤት የአፈን ኦሮሞ ትምርት መስጠት አለበት

~ የኦሮሞ ህዝብ ብሄራዊ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ(Afaan Oromoo) ነው የኦሮሞ ብሄር አንድ #የወል ቋንቋ ተናጋሪና #የጋራ የሆነ ባህል ያለው ህዝብ ነው

~ አፋን ኦሮሞ ምድቡ ከምስራቃዊ #የኩሽ ቋንቋዎች ሲሆን ካሉት #የአፍሪካ ቋንቋዎች እጅግ የተስፋፋና ወደር የሌለው ነው።

~ አፋን ኦሮሞ #ከኮንሶ ቋንቋ ጋር 50% ይቀራረባል #ከሶማልኛ ቋንቋም ጋር ሲዛመድ #ከአፋርና #ሳሆቋንቋዎችም ጋር ራቅ ያለ ቀረቤታ አለው #በአፍሪካ ካሉት ከአንድ #ሺህ በላይ ቋንቋዎች ውስጥ እጅግ በስፋት ተናጋሪ ካሉዋቸው #አምስት ቋንቋዎች መካከል አፋን ኦሮሞ እንደ አንድ ሆኖ ይቆጠራል።

~ የተናጋሪውን ቁጥርና የሚሸፍነውን መልክኣ ምድር የወሰድን እንደሆነ አፋን ኦሮሞ በአፍሪካ ውስጥ አገርኛ(indigenous) ከሆነው ከሀውሳ ቋንቋ ቀጥሎ #ሁለተኛ ደረጃ የያዘ ቋንቋ ነው ተብሎ ይገመታል

~ በኢትዬጵያ ግዛትና በአከባቢው ለሚኖሩ ቁጥራቸው #60ሚልየን የሚሆን ህዝብ የመጀመርያ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ነው ምናልባት ከዚህ ቁጥር #ከአምስት ሚልየን በላይ ኦሮሞ ያልሆኑ አፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች አሉ።

~ አፋን ኦሮሞ ከሰሜናዊው ክፍል በስተቀር በአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንደ መግባብያ አፍ(lingue franca) ሆኖ የሚያገልግል ቋንቋ ነው።
#ገዳ ስርአትና የተደበቀው የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ