አጋልጥ: ዛሬ ባህላዊን ከዘመናዊ ጋር በማጣመር መድኃኒት አገኙ የተባሉት- ሀኪም አበበች ሽፈራው

አጋልጥ: ዛሬ ባህላዊን ከዘመናዊ ጋር በማጣመር መድኃኒት አገኙ የተባሉት “ሀኪም” አበበች ሽፈራው ከጥቂት ቀናት በፊት “በዘመናዊውም ሆነ በባህላዊ መንገድ በሽታው መድሀኒት የለውም።

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶር ሊያ ታደሰ በዚ hoax በሆነ ጉዳይ ላይ በአካል ተገኝታ መታየቷ አሁንም ድረስ እየገረመኝ ነው። ከስራ ጫና የተነሳ ስለጉዳዩ ብዙም መረጃ ሳይኖራት ቀርቶ ወይስ መረጃው ኖሯት ስለ አዲስ መድሃኒት ግኝት ሂደት ያላት መረዳት በዚሁ ደረጃ ሆኖ?

#አጋልጥ
ዛሬ ባህላዊን ከዘመናዊ ጋር በማጣመር መድኃኒት አገኙ የተባሉት “ሀኪም” አበበች ሽፈራው ከጥቂት ቀናት በፊት
“በዘመናዊውም ሆነ በባህላዊ መንገድ በሽታው መድሀኒት የለውም። እኛም የባህል ሀኪሞች ቅጠል በጥሰን መድኃኒት እንድንፈልግ በየአካባቢው ረብሻ ስላለ በርሀ መውረድ እና መፈለግ አልቻልንም። ለዚም ተጠያቂው መንግስት ነው  ” ብለው ነበር። ሀኪም አበበች ጨምረውም
“ከዚህም በኋላ ሌላ የቁምጥና በሽታ ይመጣል ለሱኛውም መድሀኒት ስለሌለን መንግስት ጥንቃቄ ያድርግ” ብለው ነበር።
ታዲያ አሁን 15 ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ምን አዲስ ነገር ተገኝቶ ነው ለዜና የበቃ መድሀኒት ተገኘ የተባለው እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሊያ ታደሰ ጎን ቆመው መግለጫ የሰጡት?
ዶ/ር አማኑኤል “ለረጅም ጊዜ በጋራ ምርምር ስናካሂድ ቆይተናል” ብለው ከተናገሩት ጋርም ከላይ ከቀረበው የ”ሀኪም” አበበች ንግግር ጋር ይጋጫል
መንግስት ምን አስቦ ነው?

ለማንኛውም መድሀኒቱ ተገኝቷል የሚለው ወሬ ኮሮና ተመርመሩ ሲባል እየሮጡ የሚያመልጡትን ዜጎች ቁጥር ይቀንሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን 

Eyasped Tesfaye