አዳማ ላይ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ (Propaganda) አጠቃቀም ስልጠና ወስደው ከሳምንታት በፊት ተበትነዋል፡፡

አዳማ ላይ ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች በማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ (Propaganda) አጠቃቀም ስልጠና ወስደው ከሳምንታት በፊት ተበትነዋል፡፡ለዚህም ነው ሰሞኑን በጣም የሚቀፉ ተራ ፀረ-ኦነግ እና ፀረ-ዳውድ ኢብሳ ስድቦችን በfacebook ላይ እየተመለከትን ያለነው፡፡ 
———-
ለእናንተ ወንድሞቼ የማስተላልፈው መልዕክት አለኝ፦ ኦነግ የኦሮሞ ብሔርተኛነት አባት ነው፡፡ ዛሬ ODP የቆመበት መሠረት እንኳን ላለፉት 40 አመታት ኦነግ ባደረገው ፅኑ ትግል የተገነባ ነው፡፡ኦነግ ምንም ያህል ቢያጠፋ እንኳን አባታችን ነውና ገስፀን ማስተካከል ይገባናል እንጂ ምንም ያህል ገንዘብ ቢከፈላችሁ እንዲህ ዘግናኝ ስድቦችን ለመሳደብ ልባችሁ ሊተጋ አይገባም ነበር፡፡
——–
እውነት እናንተ ኦሮሞ ከሆናችሁ ልብ አድርጉ፡፡ ነገ ታሪክ ይወቅሳችኋል፡፡ ስለገንዘብ ብላችሁ ኦነግን እየሰደባችሁ ራሳችሁን ጨምሮ እንደ ህዝብ በሌሎችም “አፍ” እያሰደባችሁን ነው፡፡ የራስ ጎበናን አይነት ዝክረ-ታሪክ ሳይኖራችሁ በጊዜ ብትመለሱ እና በጋራ ኦነግን ልናድስ በምንችልበት ጉዳይ ላይ ብንሰራ መልካም ነው፡፡


የ ODP ችግር ምንድነው ?
————————————–
ኦህዴድ ቀድሞ ከነበረበት የተላላኪነት ባህሪ ተላቆ ከህዝቡ ጎን በመቆም ከህወሐት ጋር ህልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ በስተመጨረሻ የመሪነቱንም ወንበር ተረክቧል፡፡
————
ODP ከፍተኛ አመራሩ ተቀባይነት ያለው፣ በዕውቀት የታጀበ እና የአቃፊነት ባህሪን የተላበሰ ነው፡፡ አሁንም ግን የመካከለኛው እና የታችኛው አመራሮች ከጥንተ ባህሪያቸው የተላቀቁ አይደሉም፡፡
——–
ሁለተኛው ችግር ፓርቲው “ብአዴንን” እና የልሙጥ አንድነት አቀንቃኞችን ለማስደሰት ሲደክም መሠረታዊ የኦሮሞ ጥያቄዎችን ለመመለስ ድፍረቱን አጥቷል፡፡ ይህ ደግሞ በሂደት የህዝብ ፊት እንዲዞርበት ያደርገዋል፡፡
———
ሶስተኛ ችግር የፓርቲው ደጋፊዎች በሞቅታ እንጂ በፖለቲካ ዕውቀት የታጀቡ አይደሉም፡፡ፓርቲው ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ካልሰራ በቀጣይ የግጭት መንስኤ መሆናቸው አይቀርም፡፡ እየሆኑም ነው፡፡
———
አራተኛው ችግር ፓርቲው ወጥ የሆነ የህዝብ ግንኙነት ወኪል የለውም፡፡ ከዶ/ር አለሙ ስሜ እስከ አዲሱ አረጋ፣ ከታዬ ደንደአ እስከ ሚልኬሳ ሚዳጋ ሁሉም ፓርቲውን ወክለው መግለጫ የሚሰጡ ሆነዋል፡፡ ይህ ወጥነት የጎደለው መግለጫ ከኦነግ ጋር ላለው መካረር ዋነኛ መንስኤ ሆኖአል፡፡
———-
በስተመጨረሻም የፓርቲው አዳዲስ ካድሬዎች ታማኝ መሆናቸውን ለማሳየት ከሰሞኑ የሚያስተላልፉት ግጭት ቀስቃሽ እና መሰረተ ቢስ ክሶች የኦሮሚያን ሰላም እና መረጋጋት አደጋ ውስጥ እየከተተው ነው፡፡
———-
ፓርቲው በቀጣይ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የእርምት እርምጃ ቢወስድ መልካም ነው እላለሁ፡፡

Haweni Dhabessa