አዲሰ አበባ በልጆችዋ አጥንትና ደም ላይ የተገነባችና ዛሬም እየተገነባች ያለች ከተማ

አዲሰ አበባ በልጆችዋ አጥንትና ደም ላይ የተገነባችና ዛሬም እየተገነባች ያለች ከተማ

By: Kuusaa Galgaloo

ላይ
Addis Ababa in 1900: A “collection of villages” that was capital of an empire

የዚህ አጭር ጽሁፍ አላማ ፕሮፌሰር መኩሪያ ቡልቻ የዛሬ 10 አመት በፊት የመጫና ቱለማ ማህበር የኢህአደግ መንግስት ኦሮሞን ከገዛ ቄዬው ለማፈናቀል በአዲስ አበባ (ፍንፍኔ) ከተማ  ላይ እያካሄደ  የነበረውን ፖሊሲ በመቃወም ለዓለምአቀፍ ህብረተሰብ በጻፈው አቤቱታ ላይ “Greaater Addis Ababa in the Making: Stop them or Keep Quit and Perish” በሚል ርእስ ያቀረበውን አስተያየት አሁንም ወቅታዊ በመሆኑ የኦሮሞ ህዝብም ሆነ ሌላውም ህብረተሰብ አንዲያውቀው ወደ አማሪኛ በመተርጎም ለማቅረብ ነው።

ፕሮፌሰር መኩሪያ በሶስት ክፍሎች ከፍለው ያቀረቡትን ጽሁፍ ሲገልጹ “ይህ ታሪክ የአዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን በተወስነ ደረጃም ቢሆን የኦሮሞን ህዝብ ታሪክ የሚያሳይ ነው” ካሉ በሃላ የኦሮሞ ጠላቶች ኦሮሞን ከገዛ ሀገሩና መሬቱ ለማጥፋት አያካሄዱበት ያለውን ዘመቻ ለማስቆም ጠላቶቹ በህዝቡ ላይ የፈጻሙትን ግፍ ክማውራት ባለፈ ከማንኛውም ጊዜ በላይ ጠንክረን መታገል አለብን በማለት ጽሁፋቸውን ይቀጥላሉ። ጠላት ሲያጠቃንና ከገዛ መሬታችን ሲያፈናቅለን በቁርጠኝነት መፋለም ካቆምንና ዝም ካልን ጠላት በአብሪትና በንቀት ተሞልቶ የበለጠ ጥቃት ይፈጽምብናል። ይህ ነው በዛሬ ጊዜ በፍንፍኔና በአጠቃላይ በኦሮሚያ እየተፈጸመ ያለው። ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ አቤቱታ ማቅረብ እኛን ለማጥፋትና ለማዋረድ መቼም ቢሆን የማይታክተውን ጠላት አያስቆምም። ይልቁንም የእኛን ውርደት ያባብሳል እንጂ። እራስን መከላከል የፍጥረታት አንጋፋ ህግ ነው ይባላል። ይሄው የተፈጥሮ ህግ “ራሱን ማኖር የቻለ ይኖራል” በሚልም ይተረጎማል። ለማለት የፈለኩት ይላሉ ፕሮፌሰር መኩሪያ “ለማለት የፈለኩት እየተፈጸመብን ያለውን ግልጽ የሰብአዊ መብት ጥሰት ለማስቆም አስፈላጊውን መስዋእት መክፈል ይጠበቅብናል። አሊያም ዝም ብለን እንደ ህዝብ መጥፋት ነው።

በጸረ ባሪያነት አቋሙ የታወቀው አፍሪካዊ አሜሪካ ፍሬድሪክ ዶግለስ በ1857 ዓ/ም ባደረገው ንግግሩ “ነጻነትን እንደሚመኙ የሚናገሩ ነገር ግን ከፍርሃት የተነሳ በቁም የሚያልቁ አነርሱ መሬት ሳያርሱ እህልን የሚመኙ ናቸው። እነርሱ የመብረቅ ድምጽ ሳይሰማና መብረቅ ሳይወርድ ዝናብን የሚመኙ ናቸው ፡ ባህር የሚያስፈራውን ድምጽ ሳያሰማ እንዲኖር የሚመኙ ናቸው” ብሎአል።

ትግል የሞራል ወይም የአካል ወይም የሁለቱም ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ትግሉ መኖር አለበት። ስልጣን ያለ ትግል እውነትን አይቀበልም፡ አድርጎም አያውቅም: ለወደፊትም አያደርግም። ህዝቦች አሜን ብለው የተቀበሉትን ሲቃይ ሲታይ በዚያው መጠን የሚጫንባቸው ኢፍትሃዊነትና መጥፎ ድርጊቶች ተባብሰው ታያለህ። ሲቃዩም ህዝቡ በጉልበትም ሆነ በድምጽ ወይም በሁለቱም እስኪቃወሙ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል። የጨካኝ ገዢዎች የጭካኔ መጠን የሚወሰነው ተገዥዎች በሚያሳዩት ጭካኔ የመሸከም አቅምና ዝንባሌ ነው። የፍሬድሬክ ዶገለሰ አባባሎች የአኦሮሞ ህዝብ አሁን ላለበት ሁኔታ በብዙ መልኩ ተገቢነት አላቸው። ብዙዎቻችን ስለነጻነት ብዙ ጊዜ እንናጋራለን። ነገር ግን ነጻነቱን እውን ለማድረግ በተግባር ምንም ሲናደርግ አንታይም። መሬት ሳናርስ እህል ወደ ጎተራችን ለማስገባት የምንሻ ሰዎች ነን።

ክፍል 1 – ፍንፍኔ በ1843

ብዙዎቻችን እንደምናውቀው  አማሪኛ ተናጋሪ የመንዝ ሀዝብ ካለበት ተራራማ ስፍራ መስፋፋት የጀመረው በመጀመሪያዎቹ የ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሲሆን ንጉሳዊ አገዝዝ መስርተው ክ1813 – 1847 በሳህለ ስላሴ መተዳደር የጀመሩበት ጊዜ ነበር። ንጉስ ሳህለ ሰላሴም እስከ እለተሞቱ ድረስ በየዓመቱ 2 ወይም 3 ጊዜ በአጎራባች በሚኖሩ የአቢቹ፡ የገላን፡ የሱሉልታና ሌሎች የኦሮሞ ጎሳዎች ላይ ወራራ በማካሄድ አረመኔያዊ ጭፍጨፋና ዘረፋ ያካሄድ ነበር። ከብሪታኒያ ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ ንጉሱ ዘንድ የመጣው ሻለቃ ሃሪስ በ18 ወራት ቆይታው ንጉሱ በአጎራባች ኦሮሞዎች ላይ ያካሄድ የነበረውን ወረራ ክንጉሱ ጋር በመሄድ ይዘግብ የነበረ ሲሆን “የኢትዮጵያ ደጋማ ቦታዎች” በሚል ርዕስ  በሶስት ተከታታይ እትሞች በጻፈው መጽሃፉ  በሁለተኛው እትም በምእራፍ 23 የሚከተለውን ዘግቧል። ሻለቃ ሃሪስ በዚህ መጽሃፉ ያቀረበውን ሚሲዮናዊው ክራፍ እና እስንበርግ በወቅቱ ንጉሱን ከጎበኙ በሃላ ባቀረቡት ሪፖርት ተደግፎአል።

ድንገተኛ የወራራና የዘረፋ ዘመቻ

የከብቶች መንጋ ሰላም በሚመስለውና በአበቦች ባሽበረቀው የግጦሽ ሜዳ ላይ ተሰማርተዋል። አደጋ ይኖራል ብሎ ያልጠበቀውና ምንም የመከላከያ መሳሪያ የሌለው የከብቶቹ እረኛ እንደ ልማዱ ከብቶቹን በመጠበቅ ላይ ነበር።  ባለቤቱና ልጆቹም በሰላምና ያለስጋት የገና ባህላዊ መዝሙር እየዘመሩ የቤት ውስጥ ስራቸውን እያካሄዱ ነበር። የጠዋት ጸሃይም ብርሃንዋን በምድሩ ላይ ፈንጥቃለች። ሆኖም ጸሃይዋ ሳታዘቀዝቅ ያ ውብ መሬት በአሞራዎችና በተኩላዎች መንጋ ተሞላ።

የመንዙ ንጉሰ ሳህለ ስላሴ የቅርብ ክትትል ከሚያደርግላቸው የነፍስ አባታቸው ቄስ ጋር ከተመካከሩ በሁዋላ የቅዱስ ሚካኤል ጽላትን በማስቀደም በጉጉት ወደሚጠብቋቸው ወታደሮቻቸው ዞረው አስፈሪውንና የተለመደውን ጦር መስበቅንና በኑዋሪው ቤቶች ላይ እሳት ማቀጣጠልን መጀመር የሚያበስር ማስታወቂያ እንዲህ በማለት አሰሟቸው። “የቅድመ አባቶቼ አምላክ ብርታቱንና ምህረቱን ይስጠኝ”

እንደ ባህር ማእበል በድንገት መንደሩን ያጥለቀልቀው የአማራ መንጋ ጦር የተሰበሰውንና ገና ያልተሰበሰበውን በቆሎ ከመሬት እያደባለቀ በድንገተኛው ወረራ ተደናብረው የሚሽሹትን ነዋሪዎች ያለርህራሄ መጨፍጨፉን ተያያዘው። ከሩቅ ሲመለከቱት እያንዳንዱ የመንደሩ ቤት  ሲቃጠል የሚድቦለቦለው እሳትና የሚወጣው ጭስ በቄኝ በኩል በአበጋዝ ማረቸ በሚመራውና በአይቶ ሺሽጎ በሚደገፈው የንጉሱ ወራሪ ጦር በመንደሩ ላይ የደረሰውን የውድመት መጠን በግልጽ ያመለክታል።

ወረራዎቹ ወደ ፍንፍኔ ወረዱ

የጨካኙ ንጉስ ሳህለ ስላሴ ወታደሮቻቸው ያደረሱትን ውድመት ከቢሪታኒያው ልኡካን ባገኙት ቴሌስኮፕ ሲመለከቱ ውስጣቸው በደስታ እንደተሞላ ክፊታቸው ይነበባል። ወራሪዎቹም ከአንድ ሳአት ላልበለጠ ጊዜ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በፍጥነት በተጓዙ ጊዜ ከዚህ ቀደም አይተውት የማያውቁት በጣም ውብ የፍንፍኔ ሜዳ ደረሱ። የፍንፍኔ ሜዳ ምቹና ውብ መንደር ሆና ለእርሻ ተስማሚና በተፈጥሮአዊ ሀብትና አቀማመጥ የታደለች ሜዳ ነበረች። የሳሩ ልምላሜና የተለያዩ አበቦች እንዲሁም  ከመሬት ውስጥ እየተንተፈተፈ አካባቢውን የሚረጨው ፍል ውሃ፡ በሀገር በቀል ጥድ የተሞላውና አቀበቱን የሸፈነ ደን ለብዙ ዘመናት ከጨካኞች አይን ተደብቀው በሰላም የኖሩ የመንደሩ ነዋሪዎች ጎጆዎችና በጎጆዎቹ ዙሪያ የተኮለኮሉ የእርሻ መሳሪያዎች መንደሩን ልዩ ውበት አላብሰዋል። ይህቺ መንደር ንጉሱ በኦሮሞዎች ላይ ወረራና ዘረፋውን ለማካሄድ ማእከል ሆና ተመረጠች። ወራሪው ጦርም  ንጉሱ በቅርባቸው መስፈሩ የልብ ልብ ስለሰጣቸው ያለርህራሄ በነዋሪው ላይ በሚያካሄዱት ጭፍጨፋና መንደሮችን የማቃጠል ተግባር እንዲሁም በወራሪው ጦር ትርምስና በነፍስ ለመዳን የመንደሩ ነዋሪዎችና ከብቶች በሚያደርጉት ንቅናቄ ሰማዩ ጥቁር የጭስ ደመና ለበሰ።

ቀን የጣላቸው የመንደሩ ነዋሪዎች ሳያስቡት ከተፈጸመባቸው ወረራ ራሳቸውን ማዳን አልቻሉም። ጨካኞች ነዋሪዎቹ ከተደበቁበት ጫካ ድረስ እያሳደዱ ጨፈጨፏቸው። ሴቶችና ልጃገረዶች ተይዘው ለመጠቀሚያነትና በባሪያነት ለመሸጥ በጠላት ተወሰዱ። አረጋውያንና ጎልማሶች ያለልዩነት ታረዱ። የመንደሩ ቤቶችም በውስጣቸው ያለ ንብረት ከተዘረፈ በሃላ እሳት ተለኮሰባቸው። እያንዳንዱ ቤተሰብ በወራሪው ጦር ተከቦ ያለርህራሄ በጦር ተⶸፈጨፈ። ከእሳት ለማምለጥ ክቤት የወጡት እንደ አውሬ እየታደኑ ተገደሉ። ወላጆቻቸው ከጭፍጨፋ እንዲያመልጡ ጫካ ውስጥ የደበቋቸው የሶስትና የአራት አመት እድሜ ህጻናት ሳይቀሩ በያሉበት ተጨፈጨፉ። ከሁለት ሳአት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ወራሪው ጦር የነዋሪዎቹን መንደሮች ሬሳ በሬሳ አደረገው። ጨካኞቹ ወራሪ ወታደሮች በኡኡታና ሲቃይ የደከሙ ሴቶችና ብልታቸው የተቆረጡ ህጻናት (ምኒልክ ባልቻ ሳፎን በያዘ ጊዜ ይህንን ድርጊት ፈጽሞበታል) እንዲሁም በጭካኔ ከገደሏቸው ወንዶⶭ የተቆረጡ ብልቶችን ይዘው መንደሩን ለቀው ሄዱ።

የአሞራዎች ጫጫታና እየተቃጠለ ከሚወርደው የመንደሩ ጎጆዎⶭ ጣራ የሚወጣው ድምጽ እንዲሁም ወደ መቃብር ስፍራነት የተለወጠው ያ ውብና ማራኪ የነበረ መንደር አስፈሪ ዝምታ በደስታ ብዛት የፈነደቁትን ወራሪ ወታደሮች አስፈራቸው። በወራሪው እጅ ለወደቁና በሞትና በህይወት መካከል ላሉ ቀን የጣላቸው የኦሮሞ ሴቶችና ህጻናት እየተቃጠሉ ካሉ ጎጆዎቻቸው ወደ ሰማይ ከየአቅጣጫው የሚወጣው ጥቁር ጭስ እግዚያብሄር በብልጽግናና ውበት የቸረው ይህ መንደር በጥቂት ሳዓታት ውሰጥ በአረመኔዎችና በሃላቀር ወራሪዎች አቅም የሚቻለው ሁሉ ተፈጽሞበት ህይወት በሙሉ ወደ ሙታን ተቀየረ፤ወደመ በማለት አወጀ።

ወታደሮቹ ፍንፍኔን ከዘረፉና ካወደሙ በሃላ ወደ የካ (የዛሬው የፍንፍኔ አካል) የተለመደውን ድንገተኛ ወረራ ለመፈጸም ተጓዙ። የሀበሻ የጦር ስርአት በድንገተኛ ጥቃት፤ ያለልዩነት በመፍጀትና በማረድ ላይ የተመሰረተ ነው። በፊት ለፊት የጦር ግጥሚያና በሚዘናዊ ትግል ላይ የተመሰረተ አይደለም።

ንጉሱ በፍጥነት ወደ ፊት መጓዙን ቀጠለ፡ ኦሮሞዎች ብዙ ጊዜ ስላሸነፉት ፊትለፊት መግጠም አይፈልግም፤ በማለት ሻለቃ ሃሪስ ስለ የካው ወረራ የሚከተለውን ዘግቧል። ወራሪዎቹ ክፍንፍኔ ሜዳ ሁለት ማይል ያህል ተዘርግቶ ከሚገኘው ጫካ ወጥተው በቀጠሮዋቸው ቦታ ተገናኙ። ከዚያም በሆታና በከበሮ በመታጀብ ድንገተኛ አረመኔያዊ ጭፍጨፋቸውን በየካ ነዋሪዎች ላይ ጀመሩ። ከብቶች በገፍ ታርደው ለምግብነት ቀረቡ። እያንዳንዱ ወታደር የሚችለውን ያህል ሴቶችና ልጃገረዶች በምርኮ ይዞ ተመለሰ፤ በገፍ ከተገደሉ ወንዶች የተቆረጡ ብልቶች ጭምር። የጭፍጨፋውን መጠን በቃል ለመግለጽ ይታክታል። ህጻናትና አቅም የሌላቸው አረጋውያን ሳይቀሩ በየቦታው የታረዱ የነዋሪዎች ሬሳዎች ተደራርቦ ተኝⶆአል። ገዳዮቹ የድርግታቸውን አረመኔያዊነት በፍጹም ሳይገነዘቡ ያደረጉትንና የፈጸሙትን ሁሉ ለንጉሱ በደስታ ማውራት ጀመሩ። ንጉሱም በደስታ እየፈነደቀ ያደንቃቸው ጀመር።

ከጥቂት ሳአታት በሃላ ወራሪው ወደ የኤካ ኦሮሞዎች አገር ጉዞ ቀጠለ። አስራ አራት ሳአታት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከአስራ አምስት ማይልስ በላይ የሚሸፍን የኦሮሞ መንደሮችን ከወረሩ በሃላ በድካም ኤካ ሸለቆ ላይ ቆሙ። በቅሎዎችና ፈረሶች ልጓማቸው ተፈታላቸው። ከየመንደሩ ተነድተው የተወሰዱ ከብቶችም በጉዞ ድካም ሞቱ። ንጉሱም ወደ ማረፊያው ሄደ።

ሌሊቱ በገፍ በሚታረዱ ከብቶችና በጎች፤ በጨካኞቹ ወራሪ ወታደሮች በምርኮ የተያዙ ሴቶችና ልጃገረዶች የሚፈጸምባቸውን ማስገደድና ኢሰብአዊ ድርጊት መቋቋም አቅⶆአቸው በሚያሰሙት ዋይታና የስቃይ ድምጾች ታጅቦ አደረ። በንጹሃን ደም የተጨማለቁ አረመኔ ወታደሮች በገፍ ባረዷቸው ክብቶች ጥሬ ስጋ ፌሽታና በምርኮዎቹ ላይ በሚፈጽሙት ድርግታቸው እየፈነደቁና የጀግንነታቸውን መጠን በሽለላና በፉከራ እያስተጋቡ ሌሊቱን አሳለፉ።

ፕሮፌሰር መኩሪያ ስለሁኔታው ማስታወሻ በሚል ሲያስቀምጡ እንደሚከተልው ገልጸውታል፤

የአማራ ወራሪ ወታደሮች በንጹሃን የኦሮሞ ዜጎች ላይ ለዘመናት በኖሩበት ቄዬአቸው ባደረሱት ጭፍጨፋና ውድመት በጀግንነት ሲመጻደቁና ፌሽታ አድርገው ፉከራና ሽለላ ሲያሰሙ አስተውሉ፡፤ በሌላ በኩል ደግሞ በድንገተኛው ወረራና ውድመት ተደናብረውና መግቢያ አጥተው የተበታተኑትን  በሺዎች የሚቆጠሩ ከብቶችን፤ በወራሪው ወታደሮች እጆች ላይ የወደቁትን ሴቶችና ልጃገረዶች ሲቃይና ዋዋታ፤ የነዋሪዎቹ ቤቶች የቃጠሎ ድምጾች ከወራሪው ሽለላና ፉከራ ጋር ተቀላቅሎ የሚፈጥረውን ድምጽ አስቡት። ይህ በፍንፍኔ ብቻ ተወስኖ የቀረና በሳህለ ስላሴ ብቻ የተደረገ ሳይሆን በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ቦታዎች ለብዙ ዓመታት ከእሱ በሃላ በተነሱና  የኦሮሞን አገር መውረር በቀጠሉ የአማራ ንጉሶች ወታደሮች ተፈጽⶁአል።

ከዚህ በሃላ ንጉሱ ወረራውንና ዘረፋውን አቁመው ከነወታደሮቻቸው ሸዋን ለቀው ሄዱ።

በፕሮፌሰር መኩሪያ መስታወሻ እንደተገለጸው ንጉሱ ወረራውን አቁሞ በመመለስ ላይ እያለ ሻለቃ ሃሪስና ቄስ ዶ/ር ጆን ክራፍ የተማረኩትን ሴቶችና ህጻናት እንዲለቋቸው ንጉሱን ተማጸኗቸው። ንጉሱም ለጊዜው እሺ ብለው ለቀቋቸው። ነገር ግን ወዲያው ተመልሰው ሌላ ወረራ በመፈጸም የተረፉትን ኦሮሞዎች በሙሉ ጨረሷቸው።

ምንም ሳይቆይ ለሁለተኛ ጊዜ በፍንፍኔ ላይ ወረራ አካሄዱ

ሻለቃ ሃሪስ ወዲያው ስለተፈጸመው ወረራ የሚከተለውን ጽፎአል።

በህይወት የተረፉ የኤካና የፍንፍኔ አሮሞ ጎሳዎች ያ ክፉ ቀን አልፎአል ብለው በማመን የተረፉትን ከብቶቻቸውን ይዘው ህይወታቸውን እንደገና ለማቋቋም ጥረት እንደጀመሩ አማሮች እንደገና በድንገት አጥለቀለቋቸው። ስድስት መቶ ኦሮሞዎችን በዘግናኝ ሁኔታ ጨፈጨፉ፤ ከብቶቻቸውንም ዘረፉ። በዚህን ጊዜ በመጀመሪያው ዙር ወረራ ተማርከው በሁለቱ የውጭ ዜጎች ተማጽኖ የተለቀቁትም ሊተርፉ አልቻሉም።

ክፍል 3 – አማሮች በፍንፍኔ ላይ 1880 አጋማሽ ላይ ያካሄዱት ወረራ

ሳሀለ ስላሴ በ1847 ሞተ። የሳህለ ሰላሴ ልጅ ሃይለ መለኮት ቀደም ሲል በአባቱ የተካሄደ ወረራ ከተደረገ ከአራት አመት በሃላ በኦሮሞዎች ላይ የሚደረገውን ወረራና ዘረፋ እንዲሁም ጭፍጭፋ ቀጠለበት። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ በ1885 ዓ/ም ሞተ። ክ10 አመት በሃላ የእሱ ልጅ ምኒልክ የሽዋ ንጉስ ሆኖ ነገሰ። ሳህለ ስላሴ ተደጋጋሚ ወረራዎችን በሸዋ ኦሮሞዎች ላይ በመፈጸም ዘረፋና ጭፍጨፋ ቢያካሄድም  የኦሮሞዎችን ሀገር(ኦሮሚያን)መያዝ አልቻለም። የሳህለ ስላሴ ወታደሮች የጦር መሳሪያ የታጠቁ ቢሆኑም የኦሮሞ ፈረሰኛ ተዋጊዎችን ፊትለፊት በመግጠም እራሳቸውን መከላከል አልቻሉም።  ምኒልክ በአንጻሩ ሳህለ ሰላሴ ማድረግ ያልቻለውን አደረገ። ኦሮሞን መውረር ብቻ ሳይሆን የኦሮሞን ሀገር በቋሚነት መያዝ ቻለ። በተለያዩ ጊዜያት ኦሮሞዎችን በመውረር የተዘረፉ ንብረቶችን በዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች በመቀየር ዘመቻውን አፋፋመ። ምኒልክ በ1881 ወረራውን በኦሮሞዎች ላይ ለማካሄድ በመጀመሪያ መቀመጫውን እንጦጦ ላይ በማድረግ ማራኪውን የፍንፍኔ ሜዳ ከጋራው ላይ ሆኖ መቆጣጠር ጀመረ። እንጦጦ ያልተያዙ የአክባቢውን እሮሞዎች ለመውረርና ለመቆጣጠር በምኒልክ ስትራቴጂክ ስፍራ ሆኖ ተመረጠ። በ1880ዎቹ አጋማሽ በፍንፍኔ ዙሪያ ያሉትን ኦሮሞዎች እንደ ጎበና ዳጪ ባሉ ከሃዲ ኦሮሞዎች በመታገዝ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር በማስገባት ከእንጦጦ ጋራ ወደ ፍንፍኔ ሜዳ በመውረድ የዛሬን አዲስ አበባ መሰረተ። በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችን ከቄዬአቸውና ከመሬታቸው በማፈናቀል የኦሮሞን መሬት ለአማራ የጦር መሪዎችና ወታደሮቹ መሸንሸንን ተያያዘ። ከቄዬአቸው የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች ከፍሎቹ ወደ ደቡብ ከፍሎቹም ወደ ምዕራብ ሄዱ። መሬታቸውን ተቀምተው አከባቢውን የለቀቁ ኦሮሞዎች የመሬታቸውን መነጠቅ በግጥም እንዲህ በማለት ገለጹት።

ቀረ መመልከት ቀረ
እንጦጦ ላይ ቆሞ ወደ ታች መመልከት
ከብቶቹንና የግጦሽ ሜዳውን ማየት
ቀረ ማሰማራት ቀረ
ከብቶቹን በአባቶቻችን ሜዳ ላይ ማሰማራት
ቀረ መሰብሰብ ቀረ
ዳለቲ ላይ የጉለለ ገዳ መሰብሰብ
ጠላቶቻችን መጡብን
ከብቶችችንን ወሰዱብን
መሻሻ* ሲመጣ
መሬታችን፤ ነጻነታችን ታጣ                          *መሸሻ ከምኒልክ የጦር አበጋዞች አንዱ ነው።

ግጥሙ በአሮሞ የገዳ ስርአት እንዲሁም የኦሮሞ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ተፈጥሮአዊ ሀብቶች ላይ በወራሪዎች (ቅኝ ገዥዎች) የተፈጸመውን ውድመት በአሳዛኝ  መልክ የሚገልጽ ነው። ከዚህም ባሻገር ወራሪዎቹ የኦሮሞን ሀገርና ማንነት በማጥፋት በኦሮሞ ደምና ላብ “አዲስ አበባ” ብለው የሰየሙትን ከተማ መገንባትን ተያያዙት። ከዚሁ አዲስ አበባ በመነሳት የተቀረውን የኦሮሞን ሀገር በመቆጣጠር ህዝቡን መበዝበዝና ማሳቀየታቸውን ቀጠሉ።

ክፍል ሶስትኢህአዴግ ገባ

ከ1991 ዓ/ም ጀምሮ መሰረታቸው ከአድዋና መቀሌ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሮሞ ፍንፍኔ ላይ መኖር አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን የመወሰን ተራ ተረከቡ። በትግራይ ተወላጆች የሚመራው ኢህአዴግ የኦሮሞ ምሁራንና የመብት ተሟጋቾችን በማስወገድና ኦሮሞን ጸጥ አድርጎ በተራው ለመግዛት የሚችለውን ሁሉ ማድረጉን ተያያዘ። የኦሮሞ ምሁራን፤ጸሃፊዎች፤ አርቲስቶችና ጋዜጠኞችን በእስር ቤት አጎሩ፤ የተቀሩትም ተሰደዱ። የኦሮሞ ጋዜጦችና የባህል ማእከላት ተዘጉ።  የኦሮሞ ባለሀብቶችና ነጋዴዎችን ማሸበርና ሀብታቸውን ማውደም ተያያዙ። የመጫና ቱለማ ማህበር የፈራውን የኦሮሞን ዘር የማጥፋት ዘመቻ በኦህዴድ የሚመራውን የክልሉን “መንግስት” ክፍንፍኔ ጠራርጎ በማውጣት ተጀመረ።

ክዚህ በመቀጠል ፕሮፌሰር መኩሪያ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የጻፉት/የተነበዩትና ባሁኑ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እየተፈጸመ ያለውን እናያለን።

ኦሮሞን ከቄዬውና ከገዛ ሀገሩ ማፈናቀል በፍንፍኔ ብቻ የሚወሰን አይሆንም።አዲስ አበባ ከደቡብ እስክ ቡሾፍቱ፤በደቡብ ምዕራብ እስከ ሰበታና ከዚያ ባሻገር፤ በሰሜን ምስራቅ እስከ ሰንዳፋ፤ሸኖና ከዚያ ባሻገር ፤ በምእራበ እስክ ሆለታና አምቦ እንዲሁም ከዚያ ባሻገር የሚቀጥል ይሆናል። አላማውም ኦሮሞን ከማእከላዊ ቦታዎች ማውጣትና ሀገሩን መቆጣጣር ነው። በመጨረሻም ይህንን ማእከላዊ ስፍራ የአማርኛ ተናጋሪዎችና የፌዴራል መንግስት መቀመጫ የሆነች “ታላቋ አዲስ አበባ” ብሎ መሰየም ነው። ኦሮሞዎች ተበታትነው በሀገሪቱ የገጠር ጫፎች እንዲቀሩና በቀላሉ ከዚህ ከ”ታላቋ አዲስ አበባ” በመነሳት ለመቆጣጠር ነው። ይህ አሁን የምጽፈው ነገር ልበወለድ አይደለም፤ የሚሆን ነገር ነው። ነገር ግን ይህንን ለማስቆም ጊዜው አልመሸም ይላሉ ፕሮፌሰሩ።

ይህ እሳቸው በወቅቱ ያሉት በሙሉ የተፈጸመና አሁንም በመፈጸም ላይ ያለ ጸሓይ የሞቀው ዕውነት ነው፡፤ ፐሮፌሰሩ እንዳሉት ይህንን ለማስቆም ጊዜው አልመሸም። ለዚህም ነው ዛሬ ኦሮሞዎች የዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ጋጋታ፤ እንዲሁም ወራሪ ወታደሮችና ሰላዮችን ሳይፈሩ እየታገሉና በሺህዎች እየሞቱ፤ በገፍ እየታሰሩና በእስር ቤት ስቃይ እየደረሰባቸው ያሉት። ወራሪዎችም በበኩላቸው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ናቸው፡፤ ህዝቡን በጠብመንጃ ለመቆጣጠር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የቀድሞ አባቶቻቸው በኦሮሞ ላይ ሲያካሄዱ የነበረውን የዘር ማጥፋት በኦፌሴላዊ አሰራር ቀጥለውብታል።

ፕሮፌሰር መኩሪያ ይህንን ኦሮሞን በማፈናቀል ታላቋን አዲስ አበባ የመገንባት አላማ ለማስቆም ኦሮሞ ማድረግ የሚገባውን ሁሉ በወቅቱ አስቀምጠዋል። እንዳሉትም ባለፉት 10 አመታት ኦሮሞዎች በተለያዩ ጊዜያት የማስፋፋት እቅዱን በይፋ ተቃውመዋል። የተቃውሞው ጫፍ የደረሰው ግን በተጠናቀቀው 2015 ዓ/ም ሲሆን ወራሪዎችም የህዝቡን ትግል ለመቀልበስ 100% አቅማቸውን በመጠቀም ላይ ናቸው። ፕሮፌሰሩ በወቅቱ ለወራሪው የኢህአዴግ መንግስት ፍንፍኔን በሚመለከት ማድረግ አለበት ብለው ያቀረቡት ሀሳብ ግን አሁን ከደረስንብት ሁኔታ አኳያ ጊዜው ያለፈበት በመሆኑና ካሁን በሃላ ከዚህ ወራሪ ሃይል ምንም መጠበቅ ስለማይቻል የነጻነት ትግልን ማፋፋም አማራጭ የለሌው ጉዳይ መሆኑን አምናለሁ።

Kuusaa Galgalloo, Winnipeg, Canada