የሳህራ በረሃዋ ሊቢያ የአፍሪካዊያን ቂሊንጦ።አንድ ኢትዬጽያዊ 400 ዶላር

የሳህራ በረሃዋ ሊቢያ የአፍሪካዊያን ቂሊንጦ።  አንድ ኢትዬጽያዊ 400 ዶላር ለባርነት በሊቢያ እየትሸጠ ነው:: እርርር

Via: Tilaye Tarekegn ZE Ethiopiaia

ጨረታዉ በስምንት መቶ ዲናር ይጀምራል ከዚያ አንድ ሺ አንድ መቶ ይደርሳል በመጨረሻም በ 1200 ዲናር የጨረታዉ አሸናፊ ይዞት ይሄዳል ይህ የዲናር መጠን በዶላር 800 መቶ ሲሆን በዩሮ 680 ይደርሳል ሽያጩ የእቃ ሽያጭ አይደለም ገበያም አይደለም ይህ በሊቢያ ምድር በምድረ ሰሃራ አንድ አፍሪካዊ ወጣት የሚሸጥበት የባሪያ ግዢ ዋጋ ነዉ።

በ21ኛዉ ክ/ዘን ላይ የሊቢያ ምድር ሳህራ በረሃ አፍሪካዊያንን ይበልታቸዉ ይሸነሽናቸዉ ይቸረችራቸው ዘንድ ማን አለበት ይልሃል የአሜሪካዉ ዜና ስርጭት መሪዉ ሲ ኤን ኤን . . . .
የአፍሪካ ህብረት ከሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር አርብ እለት በ16/11/2017 የሊቢያ መንግስትን አስጠነቀቀ ድርጅቱ የአፍሪካ ወጣት ትዉልድን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲሰቃዩ የሚያሳዩ ምስሎችን በአለም አቀፍ የዜና አዉታሮች በመመልከቱ የተነሳ መታገስ አልቻለም እጅግ ፈጣን ግን ምንም መፍጠር የማይችል የደካማዉ ህብረት ጨህት እንዲህ አለ ” ታጋቾች ባስቸኳይ ይለቀቁ “።

ሲ ኤን ኤን እጅግ ዘግናኝ የሆነዉን ተንቀሳቃሽ ምስል ከለቀቀ ወዲህ አፍሪካዊያን በሊቢያ ላይ ማጉረምረምን ተያይዘዉታል የአፍሪካ ህብረት ተጠሪዉ የጊኒዉ ፕሬዘዳንት አልፋ ኩንዴ በምድረ በረሃዋ ሊቢያ ዉስጥ ለባርነት ሽያጭ የቀረቡ አፍሪካዊያን ባስቸኳይ እንዲለቀቁ እና የሊቢያ መንግስት አስቸኳይ እርምጃ በመዉስድ ይህን ተግባር የፈጸሙ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።
Apr 20, 2015, የ30 ኢትዮጵያዊያንን ደም የጠጣችዉ የሊቢያ ምድር አሁን መላዉ አፍሪካዊያንን ለሽያጭ አቅርባለች ያኔ ኢትዮጵያዊያን ሲታረዱስ አንዳችም ያልፈየዱት የአፍሪካ ህብረት ሐገሮች ዛሬ እየተንጫጩ ነዉ።
ሊቢያ የሰዉነት አካል በቀላሉ የሚቀየርባት አፍሪካዊቷ ሲኦል ሆናለች።

UN migration agency የተባበሩት መንግስታቱ የስደተኞች ጉዳይ እንዳስታወቀዉ የሊቢያ መሪ የነበሩት ሙሃመር ጋዳፊ ከስልጣን ከተወገዱ ወዲህ የአፍሪካዊያን ወጣቶች ለሽያጭ ማቅረቡ በሊቢያ መደበኛ አገልግሎት እየሆነ መምጣቱን ከማመላከቱ ባሻገር አይ.ኤም.ኦ የተባለዉ የተባበሩት መንግስታት አጋር ድርጅት በሚያዚያ ወር 2017 ከአፈናዉ ያመለጡ የተለያየ አፍሪካ ሐገር ስደተኞችን ቃለ መጠይቅ ካደረገ ወዲህ ወደ ሐገራቸዉ መዉሰዱንና ተመላሾቹም አስከፊ ሁኔታዎችን ማሳለፋቸዉን በመግለጽ አለም ወደ ሊቢያ እንዲመለከት ዉስጣዊ ጥሪ አሳተላልፏል።

በሊቢያ በኩል ወደ ጣሊያን ለመግባት ከሚሞክሩ አፍሪካዊያን መካከል ኢትዮጵያዊያንም የሚገኙበት ሲሆን ደማቸዉ በባህር እስከሚፈስ ድረስ የሞቱን መንገድ እድሜ ለእነ እንቶኔ ተግተነዋል።

( ጉድሽ ወያኔ )


አንድ ኢትዬጽያዊ 400 ዶላር ለባርነት በሊቢያ እየትሸጠ ነው:: እርርር

Ethiopia : ሩዋንዳ ከዛ ሁሉ የዘረኝነት እርስ በእርስ ፍጅት ወጥታ ከራሷ አልፈ ለሌላው ሀገር ዜጎች ደረሰች ወያነ በስደት ላይ ለሚሰቃየው ኢትዮጵያዊ ሊደርስ ይቅርና ሀገር ውስጥ ያለውን ህዝብ እያሰረና በጥያት እየጨረሰ ነው:: አናሳዝንም ወይ??

Rwanda : Thanks for Rwanda and Paul kagame to stand-up and willing to take some of slavery refugees from Libya. Every country in Africa Should do the same. ሩዋንዳ ማንኝውንም አፋሪካውያን ሩዋንዳ ሀገር እንዲጠለሉ እና እንደምታጎግዝ ፍቅዳለች። ከሰላሳ ሺ በላይ አፍሪካዊያን ከሊቢያ ወደ ሩዋንዳ ይገባሉ እየገቡም ነው:: የኢትዮጵይ ፓለቲከኛ ቤተ አማራ ኦሮሞ ፋርስት እያላቹ ጊዚያቹን አትታባክኑ አንድ ኢትዬጽያዊ 400 ዶላር ለባርነት በሊቢያ እየትሸጠ ነው::  ካለ ስሙ !

Via: Natnael Mokonnen