አቶ ኩራባቸው ፍቅሩ የኢትዮ-ቻይና ሰራተኞች ማህበር ጊዜያዊ ኮሚቴ ፈዴሬሽን ፕሬዝዳንት ነበሩ።

አቶ ኩራባቸው ፍቅሩ የኢትዮ-ቻይና ሰራተኞች ማህበር ጊዜያዊ ኮሚቴ ፈዴሬሽን ፕሬዝዳንት ነበሩ። ቻይና አሰሪዎች በኢትዮጵያዊያን ሰራተኞች ላይ የሚፈፅሙትን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት

በማጋለጣቸው የሕወሃት የደህንነት ሃይሎች ባደረሱባቸው የግድያ ዛቻ ሀገር ለቀው ተሰደዋል። ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ከ 1,400 በላይ ሴቶች በቻይናዎች ተደፍረዋል። ከ4000 በላይ ሰራትኞች ዘላቂ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ከ200 በላይ ሰራተኞች በቻይናዎች ካምፕ እስር ቤት ውስጥ ደብደባ ተፈፅሞባቸዋል፤ ከ20 በላይ ሰራተኞች በቻይናዎች ተገለዋል። በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ ለማስቆም የሰራተኛ ማህበሩ ጥረት ቢያደርግም የገዢው ፓርቲ የፀጥታ ሃይሎች ከቻይና ማናጀሮች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያዊያን ላይ ያደረሱት በደል እጃቸው ላይ ካለ መረጃ በመነሳት ከጠያቂነት እንደማያመልጡ አስጠንቅቀዋል። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንም ጉዳዩን ለዓለም ማህበረሰብ በማሳወቅ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ በተጠቁት ኢትዮጵያዊያን ስም ተማፅነዋል።

ESAT HR – Over 1000 Women’s Abuse and Rape Made by Ethio-Chinese Company Workers. 01 Jan 2018