አቶ አዲሱ አረጋ “ዓላማችን እውነተኛ ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም መገንባት ነው”

አቶ አዲሱ አረጋ “ዓላማችን እውነተኛ ህብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም መገንባት ነው”
 
የሚል ፍሬ ሀሳብ ያለው ጹሁፍ በፌቡ ገፁ ላይ አውጥቷል።
በተጠየቅ ፊት ረብ በሌለው በዚህ ሀሰተኛ ቃል እንዳትሳሳቱ።
 
1ኛ ብልፅግና ፓርቲ የቆመበት “መደመር” የሚባለው ግራ ገብ አስተሳሰብ በግለሰብ መብት ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ በ“መደመር’’ መፅሀፍ ውስጥ በግልፅ ተጠቅሷል፤ ብልፅግና የቡድን መብትና ጥቅም የሚያስቀድም የህብረ—ብሔር ፌዴሬሽን አራማጅ ሊሆን አይችልም።
 
2ኛ አዲሱ አረጋ የግሌ አቋም ነው ብለን ኖሮ በግማሽ ልብ እንሰማው ነበር።
ይህንን የግል የአቋም መግለጫ መስጠት የሚችለውም ብልጽግናን ከለቀቀ ብቻ ነው። ከፓርቲውና ፓርቲውን ከሚመራው ግለሰብ መሰረታዊ የሆነ የአቋም ልዩነት ይዞ አብሮ መቀጠል አይችልም።
 
3ኛ ህበረ ብሄር ፌዴሬሽን የብልፅግና ፓርቲ ግብ ቢሆን ኖሮ በፓርቲው መመስረቻ ሰነድ ላይ ሰፍሮ እናገኘው ነበር። ፓርቲው በሚታወቀለት ግለሰብና ዜግነት’ ተኮር ርዮተ ዓለሙ ላይ የተደረገ ለውጥ ካለም በፓርቲው የህዝብ ግኑኝነት በኩል ኦፊሴላዊ መግለጫ ይሰጥ ነበር እንጂ በአዲሱ አረጋ የግል የፌስ ቡክ አካወንት ላይ አይወጣም።
 
እንደዚህ ያለ አንድ ፓርቲ የቆመበት መሰረተ ነገር ላይ ማሻሻያ የሚደረገውም በፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ ብቻ ነው።
ብልፅግና ደግሞ እስከዛሬ ጠቅላላ ጉባኤ አላደረገም። በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውም ይህን የህግ መስፈርት ሳያሟላ ነው።
4ኛ ብልፅግና ተመስርቶ ህልውናውን ካወጀ ጀምሮ በህብረ ብሄር ፌዴሬሽን ጉዳይ በፓርቲውና በመሪው ላይ የመረረ ትችትና ስሞታ ሲቀርብባቸው ነው የቆየው። አንድም ጊዜ ወግ ባለው መንገድ ማስተባበያ አልሰጡም። እንዲያውም ዐቢይ አህመድ ፀረ ህበረ ህብራዊ ፈዴሬሽን ነው እየተባለ የሚቀርብበትን ክስ የሚያጠናክር ንግግርና ድርግት ሲፈፅም ነው የሚታወቅ
 
5ኛ አቶ አዲሱ አረጋ አባል የሆነበት የብልፅግና ፓርቲ እነ አቶ ዮሀንስ ቧ ያለው፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ አቶ ላቀው አያሌው ጭምር የሚገኙበት አንድ ውህድ ፓርቲ ነው። በህብረ ብሄር ፌዴሬሽንና በህገ መንግስቱ ላይ እነዚህ ሰዎችና የአማራ ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሚያራምዱት ተቃውሞ በግልፅ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ “ህብረ ብሄራዊ ፌዴሬሽን የብልፅግና ፓርቲ ዓላማ ነው” በማለት አሳምናለሁ ብሎ የሚያስብ ሰው ለአንባቢዎቹም ሆነ ለራሱ ክብር የሌለው ተራ አጭበርባር ስለመሆኑ ሌላው ማሳያ ነው
 
6ኛ ህብረ ብሄራዊ ፌዴሬሽን የዐቢይ አህመድና የሚመራው ፓርቲ የፖለትካ እምነት ቢሆን ኖሮ ይህንኑ መብት በጠየቁት በሲዳማና በወላይታ ብሄሮች ላይ ጦር ያዝምትባቸው ነበር ወይ?
★ሲደመደም የአዲሱ አረጋ ቃል ከእወነት የራቀ ስለመሆኑ አይጠረጠርም ፤ መጠየቅ ያለበት ይህን ሀሰተኛ ነገር አሁን ማሰራጨት ለምን አስፈለገው የሚለው ነው።
 
አዲሱ አረጋ ይህን ለማለት የመጀመሪያ ሰው አይደለም። ልብ አልተባለ እንደሆን እንጂ ሰሞኑን የኦሮሞ ብልፅግና ካድሬዎች “ዐቢይ እኮ ፌዴራሊስት ነው” የሚል ስብከት በፌስ ቡክ ላይ እየደጋገሙ ነበር።
አቶ ሽመልስ አቢዲሳም የፌዴራሊዝም አወዳሽና ቡራኬ ሰጪ ሆኖ የተከሰተውም በዚሁ ሳምንት ነው።
ሁሉም የአንድ ገቢር የተለያዩ ትይንቶች ናቸው።
የአዲሱ አረጋ ፁሁፍም የዚሁ ትሬንድ አካል ነው።
 
♠ዓላማውም አንድም የኦሮሞ ብሄርተኞችን በማጭበርበር ከተቃዋሚነት ወደ ደጋፊነት ለመቀየር ሲሆን ሌላው ደግሞ የአማራ ብልፅግናዎችንና ብሄርተኞችን በማስፈራራት በዐቢይ ላይ ያላቸውን ተቃዋሚነት ለማለዘብ ነው። በአንድ ደንጋይ ሁለት ወፍ ይሏችኋል እንዲህ ነው።
የአማራ ብልፅግና ካድሬዎችና ደጋፊዎች
 
ሰሞኑን በርስት ጉዳይ በዐቢይ ላይ እያጎረመረሙ ነው።
ብሄርተኞቻቸው ደግሞ “የዐቢይ አህመድ ኢትዮጲያ ከሽመልስ አብዲሳ ኢትዮጲያ የተለየች ናት” በሚል ሽመልስ ፌዴራሊዝምን አወደሰ ብለው ሲዘልፉት እንደነበረ ልብ በሉ!
 
♥ሀኬተኛው፣ አታላዩና ከመርህ ጋር የማይተዋወቀው ዐቢይ አህመድ የአማራ ብልፅግናዎች ጋር አልመግባባት ውስጥ ሲገባ ለማስፈራራት ወይም የኦሮሞ ብሄርተኞችን ለማጭበርበር ሲፈልግ እንደ አዲሱና ሺመልስ ያሉ ተላላኪዎቹን ያሰማራል። አሁን ለጊዜው የፈለገው ነገር ይሳካ እንጂ ግለሰቦቹ የሚዘባርቁት ነገ ሆኖ ባይገኝ እርሱ አይወቀስበትም፤ የሚነቀፉትና የሚዘለፉት እነርሱ ናቸው። መዘለፍ ደግሞ ለእነ አዲሱ ብርቃቸውም ችግራቸውም አይደለም። ለየትኛው ክብራቸውና ሰውነታቸው ይጨነቃሉ?
ኦህዴዶች ናቸው እኮ!
 
እኛ በእንደዚህ አይነት ወጥመድ ውስጥ እናዳንወድቅ እያስተዋልንና እያመዛዘን እንራመድ። የዐቢይ አህመድ ያልተገራ የአንባገነንነት ፍላጎት በጉልህ እየታወቀ በካድሬዎች መታለል የለብንም።