አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

Above Single Post

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 15 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድርነት በእጩነት የቀረቡትን የአቶ ተመስገን ጥሩነህን ሹመት አፅድቋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር የአማራ ክልል ህዝቦች ከመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር በአብሮነትና መተሳሰብ መንፈስና ለዘመናት ሲኖሩ የቆዩ መሆኑን አስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ ስንከተለው በነበረው የተዛባ የፖለቲካ አስተምህሮ ምክንያት ዛሬ ላይ አንድነታችንና ሰላማችን አደጋ ተደቅኖበታል ብለዋል።

ይህንን ለሁለት አስርት አመታት ሲሰበክ የነበረውን የተዛባ የፖለቲካ አስተምህሮ ለማስተካከል እና በአማራ ክልል ህዝብ ላይ የሚሰራን ማንኛውንም የፖለቲካ ሴራ ለማስወገድ ከክልሉ ህዝብ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ ውስጥ በርካታ ወቅታዊ ተግዳሮቶች መኖራቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ እነዚህን ፈተናዎች በብቃት ለመወጣት ቁርጠኛ አቋም ያላቸው መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ለዚህም በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ የተለያዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለማስወገድ የፀጥታ ሃይሉን አቅም የማሳደግና የመገንባት ስራ ይሰራል ነው ያሉት።

የክልሉ ህዝብ ከሌሎች የአገሪቱ ዜጎች ጋር በአብሮነት እስከሰራ ድረስ ምንም አይነት ፈተና ቢመጣ የማንወጣው ነገር የለም ሲሉም ተናግረዋል።

የአማራ ክልል በርካታ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት ነው ያሉት አቶ ተመስገን፥ ክልሉን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለስኬታማነቱም የክልሉ ሕዝብ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ በሠላም፣ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ መስኮች ግንባታ የበኩሉን ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪም የወሰንና የማንነት ጥያቄዎች ለግጭት ምክንያት ሳይሆኑ በሕግ አግባብ እንዲመለሱ ለማድረግ የሚሰራ መሆኑን ነው የገለጹት።

ከዚህ ባለፈም በክልሉ ያለውን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል፣ የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና አዳዲስ የቱሪስት ማስህቦችን ለማስተዋወቅ በርካታ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒውተር ሳይንስ እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በተቋም የለውጥ አመራር ያገኙ ሲሆን፥ በተለያዩ የፌዴራልና የክልል መስሪያ ቤቶች በሃላፊነት አገልግለዋል።

በዚህ መሰረትም የአማራ ክልል የርዕሰ-መስተዳድሩ የፀጥታ እና ቴክኖሎጂ አማካሪ፣ የአማራ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪና የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በመሆን አገልግለዋል።

ከዚህ ባለፈም የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር፣ የኢትዮቴሌኮም ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣በሃገር መከላከያ ሰራዊት መረጃ ዋና መምሪያ፣ኤሌክትሮኒክስ መምሪያ፣ቴክኒካል መረጃ መምሪያ እንዲሁም በሚኒስትር ማእረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ሆነው ሰርተዋል።

በአልዓዛር ታደለ

FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)


የሶማሊ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙስጠፋ ኡመር ባህር ዳር ሄዶ ተናገረ በሚል እዚህ ኢንተርኔት ላይ የሚዘዋወሩትን ጥቅሶች በርግጥም ሰውየው ተናግሮአቸው ከሆነ፣ በተለይም ከሶማሊ ክልል ፖለቲካ አንጻር ሲታይ ምናልባትም የሰውየው ፖሊቲካ ህይወት ገመድ በቅርቡ ሊበጠስ እንደሚችል ያመላከተ ነው ለማለት ያስደፍራል።

ሰውየው ኢትዮጵያ ባቅጣጫ ስሞች በሚጠሩ ክልሎች መዋቀር አለባት አለ አሉ። በርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን ለሶማሊ ህዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሶማሊዎችን ሁላ ባንድ ዩኒት ባቀፈ የፌዴራሉ መንግስት አባል ክልል ውስጥ መተዳደር ሊቀበሉት የሚችሉት የመጨረሻው compromise ነው።

ከዚ አንጻር ስናየው ሙስጠፋ አለ የተባለው እውነት ከሆነ፣ ሰውዬው ከሚመራው ክልል ህዝቦች ግልጽ ፍላጎት አንጻር constituency አልባ መሪ ወይም ዝም ብሎ ባየር ላይ ተንሳፋፊ የህልም ፖለቲከኛ ነው ለማለት ያስደፍራል።

I wish he didn’t say all these BS stuff for a mere appeasement but if he did, he might have to pay a price, unfortunately.

Girma Gutema


ከወደ ሰሜን ምነው ለቅሶ በረከተ? ሁላችንም ኦነግን!

“ከወደ አሜሪካ እሷ ጫልቱ ናት ብሎ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መሪ መፈክር አድገው የጫልቱ ስም ስቀወሙ ዋሉ” የድንቁርና ጫፍ ይሉሃል ይሄ ነው።

በኦነግ ስም ኦሮሞን የሚያሸመቅቁበት ለይመለስ ሄዷል። ኦነግ የታገለው ለፍትህ ለእኩልነትና ለእውነተኛው ፌዴራልዝም ነው። አብይና ለማ ኦነግ ነው ማለታችው የጸረ ጭቆና ልጆችና ባላ ራአይ ማለታችው መሆኑን አትዘነንጉት።
#አሁን ወቅቱ የሚጠይቃው፡
1 መጀመሪያ ራስህ ሆነህ ለጋራ ማሰብ
2 ኢትዮጵያ እኔም እሱም እሷም ያለንበት የብሄር ብሄረሰቦች ድምር ውጤት መሆኗ አምኖ ከልብ መቀበል
3 አሁን ያለውን የፌዴራል ሥርአት የበለጠ እውነተኛ ከማድረግ ውጭ አሃዳዊ መንግስት ያከተመለትና ላይመለስ ያለቀለት መሆኑ ራስህን ማሰመን
4 ከተረት ተረት የኢትዮጵያ ታሪክ ወጥቶ እውነተኛውን የኢትዮጵያ ህዝቦች የራሳቸውና የጋራ ታሪካቸውን መቀበል ወይም ለመቀበል መዘጋጀት
5 የመንግስት ስልጠን ልጅ አባቱን ገድለው ሳይሆን ሰላማዊ በሆነ ምርጫ ብቻ የሚገኝ መሆኑ ማመን የስፈልጋል


የአማራ አክቲቪስት የቀን ተቀን ውሏቸውን፦
-ስድብ -ንቀት -ማንቋሸሽ -ማዋረድ
-ከሌ እንደዚህ አለ-ከሌ እንደዚህ ብሎ ነበረ
-ከሌ ምርጥ ነው -ከሌ ባንዳ ነው -ከሌ ተላላኪ ነው -ከሌ የብአዴን አክቲቪስት ነው -ከሌ ተከፍሎት ነው -ከሌ ነጋዴ ነው-ከሌ….ወዘተ ሲሉ ነው የሚውሉት አሁንም አማራ ክልል ላይ አሳሳቢው ጉዳይ ነው::
ተመስገን ጥሩነህ ይኼን የዞረበትንና የተበላሸውን የአማራ ፖለቲካ ማስተካከል ከቻለ ትልቅ ስራ ሰርቷል። ያው እነ አክቲቪስት ጥቂት ግዜ ከሰጡት ማለት ነው!!

Below Single Post