አብይ ትግራይን የማስተዳደር መብት የለውም!

አብይ ትግራይን የማስተዳደር መብት የለውም!

ማንኛውም ማህበረሰብ ራሱን በራሱ የማስተዳደርና የራሱን ዕድል በራሱ የመወሰን ተፈጥሯዊ መብት አለው። የዲሞክራሲ መሰረታዊ መርህም ይሄ ነው። ከዚህ ውጭ አንድን ማህበረሰብ በጉልበት ለማስተዳደር መሞከር ህገወጥ ሲሆን ወጤታማ ሊሆንም አይችልም።
ወደ ኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ ፖለቲካዊ ፍልስፍናው የተሳሳተ ቢሆንም ከ1983 ጀምሮ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለብሔሮች የተሰጠና በህግ የፀደቀ ሲሆን አብዛኛው የብሔር ልሂቃንም አስተሳሰቡ በዚህ ሀሳብ ተቀርፆ ጎልብቷል። እናም በየብሔሩ ውስጥ ያለው ገዢ ፖለቲካዊ እሳቤ ይሄ ነው። የብሔር ልሂቃኑ “አሁን ያለችው ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የፈጠርናት እኛ ብሔርተኞቹ ወደንና ፈቅደን እንደ አክሲዮን ድርሻ አዋጥተን ነው” ብለው ያምናሉ። በአንፃሩ ስለኢትዮጵያ አንድነትና ታሪክ ሲወሳባቸው የአፄ ርዝራዥ፣ ጨፍላቂ፣ አሃዳዊ እያሉ ያጣጥላሉ። ስለዚህ ነባሯ ኢትዮጵያ ፈርሳለች።
 
ከዚህ በመነሳት የአብይ መንግስት ትግራይ ውስጥ የሚያካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ ባስቸኳይ ማቆም አለበት። ምክኒያቱም አሁን ባለው በራሱ በመንግስት ፖለቲካዊ እሳቤ መሰረት መንግስት ራሱ ወራሪ ነው። በፖለቲካ ልሂቁ ዘንድም እንደወራሪ ነው የሚታየው። ምክኒያቱም የማዕከላዊ መንግስቱን አቅም ተጠቅሞ ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ የተፈቀደላቸውን ብሔሮች መውረር አይቻልም። እናም የትግራይ ህዝብ ተፈጥሮም ህገመንግስቱም የሰጠውን መብት ተጠቅሞ የራሱን ዕድል በራሱ ይወስናል።
 
የትግራይ ህዝብ በፈለገው አካልና በተመቸው ሁኔታ ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት አለው። ይህን ሁኔታ መቀየርም አይቻልም። ለዚህም ነው ጦርነቱ በአሁኑ ሰዓት ህዝቡንም ዒላማ እያደረገ ያለው።
ህገመንግስቱና የብሔር ፌደራሊዝሙ በራሱ አንድን ብሔር ተለይቶ ሊጠቃ የሚችልበትን በር የከፈተና መንገድ ያመቻቸ ነው። ሌሎች የብሔር ቡድኖች ግንባር ፈጥረው አንዱን ብሔር እንዲያጠቁ ዕድል ይሰጣል። በዚህም ምክኒያት ብሔሮች ሀገራዊ ዋስትና የላቸውም። ስለዚህ የአንድ ብሔር ዋስትና በራሱ ጥንካሬ፣ ከሌሎች ጋር በሚፈጥረው መስተጋብርና በሌሎች ብሔሮች መልካም ፈቃድና ሀዘኔታ ላይ የተንጠለጠለ ነው። በመሆኑም የብሔር ክልሎች ራሳቸውን በማስታጠቅና ወታደራዊ እሽቅድምድም ላይ እንዲጠመዱ ምክኒያት ሆኗቸዋል። ድሮስ ለመጣላት የተነሱ የብሔር ኃይሎች እንዴት አብረው በሰላም ይኖራሉ?
 
ኢትዮጵያ መሰረታዊ የፖለቲካ መናጋት ገጥሟታል። የዚህ ዋና ምክኒያት ደግሞ ላለፉት 50 ዓመታት ብሔርተኞቹ ያቀነቀኑትና አሁን ስልጣን ላይ ያለው አካል የሚከተለው የተዛባና ኋላቀር የፖለቲካ እሳቤ ነው። ሀገር እንደሀገር ለመቀጠል መሰረታዊ ውይይት ያስፈልጋል። አሁን ላለው ችግር በጦርነትም በምርጫም ዘለቄታዊ መፍትሔ ማምጣት አይቻልም።
ለመዳን መራራውን ክኒን መዋጥ ግድ ነው
ከዝንጀሮ ፖለቲካ ውጡ
Dan Dimension

1 thought on “አብይ ትግራይን የማስተዳደር መብት የለውም!

  1. TDF will set free Abiy and his team let alone genocide prisoners from amhara and rest of ethiopia .

    TDF is worried for these prisoners and hell bent on searching food from abroad. These prisoners were killing children and elders.

Comments are closed.