አስቸኳይና አስፈላጊ መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ!!


አስቸኳይና አስፈላጊ መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

Kana booda Sakandiin, Daqiiqaan, Sa’atiin, Guyyaan #Abiy hinsaaxilamne hinjiraatu. Sa’atii ammaatti Warri Holland Mana Murtee Yakkaa Addunyaa fuuladuratti itti muddaa jiru.

Hiriira Oromoo @Netherlands
Den Haag
The Heague

Abdo Qaadi Abajabal


አስቸኳይና አስፈላጊ መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ

ዛሬ በኢትዮጵያ እየተከሰቱ ያለዉ ክስተቶች ለአንዳንዶቻችን ድንገት የተክሰቱ ጉዳዮች /ክስተቶች ቢመስሉንም እዉነታዉ ግን አቶ ኢሳያስ አዲስ አባባ እግሩ ከረገጠበት ጊዜ ጀምሮ የተጠነሰሱና በጥንቃቄ የተቀረፁ ዕቅዶች ትግበራ ነዉ። አቶ ኢሳያስ አዲስ አባባ በእግሩ ከረገጠ በኋላ የአብይን ልብ ለማንበብና የሚፈልገዉን ለመስራት ይችል ዘንድ ቀደም ብሎ የጠበቀ ግኑኝነት ባይኖራቸዉም ፅንሰ ሀሳቡን ለመቅረፅ የአዲስ አባባዉ ጉዞ መልካም አጋጣሚ ነበር።
ከዚያች ጊዜ የጀመረዉ ግኑኝነት ቀስ በቀስ ከላይ ላይ ወደ ዉስጣዊና ሚስጥራዊ አደገኛ ይዞታ መሸጋገር ጀመረ። ብሎም ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ወዳለችበት አሸጋገራት።

“ለመሆኑ ከሁለቶቹ ግኑኝነቶች ምን ተገኘ?” ብዬ ብተነትን በጣም ስለሚሰፋ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ብቻ ላተኩር። ይህን እንፎርሜሽንና ትንተና የምሰጥ ሰዉ ማንነቴን መግለፅ ለተዓማንነት አስፈላጊ ቢሆንም ዛሬ ላይ ይህን ሚስጥር አውጥተዉ ላካፈሉኝ ኃላፊዎችና ለራሴም ደህንነት ስል ለጊዜዉ የኔን ማንነት መግለፁን ትቼ ወደ ዝርዝር ጉዳዬ እገባለሁ። ምክንያቱም ዛሬ የበለጠ አስፈላጊዉ “ጉዳዩ” እንጂ “ማን አመጣዉ?” አይደለምና። ጥርጣሬን ለማጥፋት “ማን አመጣዉ?” ለሚለዉም ጊዜዉና ሁኔታዉ ሲፈቅድ ማንነቴንም ለመግለፅ ቃል እገባለሁ። እስከዚያዉ መልዕቴ ይኸዉላችሁ።
የኢሳያስና የአብይ ጉዳይ ለሀገራችንና ለቀጠናዉም አስጊ እየሆነ መጥቷል። የአስጊነቱ ልክ ደሞ በሁለቱ ግኑኝነቶችና በአጋሮቻቸው የግልና የማይቋጭ ስግብግብነት ላይ የተመሰረተ በመሆኑና ከዚህ ዉጪ ያለውን ሁሉ ማግለል ብቻ ሳይሆን በማጥፋት ፅንሰ ሀሳብ ላይ የተመሰረተም በመሆኑ ነዉ።
አንድ ሰዉ ስለ ግሉ፣ ስለፓርቲዉና ስለመንግስቱ አበክሮ ማስላትና መሰራት ያለና የሚደገፍ ቢሆንም ፅንሰ ሀሳብን ለማስረግ ሌሎችን መስዋዕት በማድረግ ላይ የተመሰረተ ርዮተ ዓለም “እራስን በገነት ለማኖር ለሌሎች ገሃነም” የሚደገስላቸዉ ከሆነ የፅንሰ ሀሳቡ አራማጅ ከሰዉ ስብዕና ወጥቶ ወደ ሴይጣናዊ ማንነት መሸጋገሩን ያረጋግጣል።
የኢሳያስና የአብይ ግኑኝነት በበጎ እሳቤ ላይ የተመርሰረተ ቢኖን ኖሮ፤ አይደለም ለኢትዮጵያና ለኤርትራ በቀጠናችንና በአፍሪካ ቀንድም ሰላምና መረጋጋትን ያስገኛል ብዬ አስብ ነበር። እንደምታውቁት ሀገራችን ኤርትራ ከነበረችበት መልካም ይዞታዋ ወርዳ ወደ ችግር ብሎም ወደ ባሰ ሲኦል እየሄደች ትገኛለች። ይህ ደሞ በአጋጣሚና በድንገት የተከሰተ ክስተት ሳይሆን ኢሳያስ ሀገሪቷንና ህዝቧን ለማጥፋት አቅዶ ሲሰራበት የነበረ ተንኮል መሆኑን የኤርትራ ህዝብ በሙሉ የሚያውቀዉና የማይቃረንበት እውነታ ነዉ።
ይህ የኢሳያስ መሰሪ ተንኮል በኤርትራና በህዝቧ ላይ ሳያበቃ ይኸዉ የጎረቤት ህዝቦችንና ሀገራትንም በመናጥና በማናወጥ ላይ ይገኛል። ይህ ከሱዳን ጀምሮ በጂቡቲ፣ በየመን፣ በሶማሊያና አሁን ደሞ በኢትዮጵያ ተንኮሉ እያተራመሰ ይገኛል። የኢሳያስ በኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት ዛሬ በአብይ ዘመን የጀመረ አይደለም። ቀደም ሲልም የነበረ ነበር። ይሁን እንጂ በርካታ እንቅፋቶች ነበሩበት። የአሁኑ ጣልቃ ገብነት ግን እንዳቀዱት ሊሄድ የቻለዉ በጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ትብብር እየተኬደበት ያለ በመሆኑ ነዉ። የሁለቶቹ ግኑኝነት ሲጀመር አብይ ኢሳያስን ሲቀርበው በበጎና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የአሁኑ ግኑኝነታቸዉ ግን ከልክ በላይ ከማለፉም በላይ ሁለቱም በመረዳዳት በተንኮላዊ ተልዕኮ ላይ በመተጋጋዝ መስራታቸዉ ነዉ።
ትብብራቸዉ በበርካታ ዘርፎች ላይ የተሳሰረ ሲሆን በዚህ ዝግጅት በኢትዮጵያ ፀጥታ ላይ ባንዣበበዉ ጉዳይ ላይ ብቻ ማተኮር እፈልጋለዉ። በዚህ ረገድ፤
1. ኢሳያስ አፈውርቂ የኮረና ነውጥ ሀገር እየናጠ በነበረበት ወቅትና ሀገራት ድንበሮቻቸዉን በዘጉበት ቅፅበት ሜይ 3 ቀን 2020 “የኢንዱስትሪ ፓርክ ለማስመረቅ” በሚል ሽፋን አዲስ አባባ የሄደው ለተባለዉ አጀንዳ ሳይሆን ጠ/ሚ/ር አብይ “ይፈታተኑኛል፤ እንዴት ላልፋቸዉ እችላለሁ?” ብሎ ላማከረዉ ወሳኝ ጥያቄዎች ያዘጋጀለትን ጥናት ከእነ ጀዋር ጀምሮ ያሉትን ተቀናቃኝ ፓርቲዎችና አክቲቪስቶች ደረጃ በደረጃ በራሱ መንገድ እንዴት እንደሚያጠፋቸዉ ሊያስረዳዉና የጥናቱን ፕሮጀክት ሊያስረክብዉ ነበር አዲስ አባባ የሄደዉ።
2. ይህ ጥናት ቀደም ብሎ የጀመረ ሲሆን መጀመሪያ ከኢትዮ ኤርትራ የሰላም ስምምነት በኋላ በ26-09-2019 አራት የኤርትራ የፀጥታ ኤክስፐርቶች፡
2.1.ሀድጎ ስዩም
2.2.ሚካኤል ኃይሌ
2.3.ሰመረ ባህታ
2.4.ዳኔል ክፍሉ የሚባሉ በትግራይ በኩል እንደ ሲቪል ተጓዦች ለልዩ ተልዕኮ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ተደርጓል።
3. ቀጥሎም በ117 አባላት በላይ ያሉት ቡድን ለልዩ ተልዕኮ በሁለቱ መሪዎች እቅድ እንዲገባ ተደርጓል።
4. ከነዚህም በኋላ በርካታ የሴኪዩሪቲ አባላት ተከታትለዉ አዲስ አባባ እንዲከትሙ ተደርጓል።
እዚህ ላይ ሊነሱ ከሚችሉ አበይት ጥያቄዎች፤
1. እነዚህ የፀጥታ አባላት ከኤርትራ ኢትዮጵያ የገቡት ምን ልያደርጉ ነዉ?
2. በማን ፈቃድ ነዉ እነዚህ አካላት የተሰማሩት?
3. የኢትዮጵያ የፀጥታ ኤጀንሲ ያዉቃቸዋል ወይ?
4. እየተከሰቱ ካሉ ክስተቶችስ እጆቻቸዉ ነፃ ናቸዉ ወይ?
በመጀመሪያ እነዚህ አካላት ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በዶ/ር አብይ ጥያቄና እዉቅና ነበር። የመጀመሪያዉ ተልዕኳቸዉ የኤርትራ ተቃዋሚ ኃይሎች ላይ የማጥፋት እርምጃ እንዲወስዱባቸዉ ሲሆን እግረመንገዳቸውንም እንደነጆሀር ያሉትን ተቃዋሚ ፖለትከኞችና አክቲቭስቶችን ከእይታ በማጥፋት ለዶ/ር አብይ ገፀ በረከት ማቅረብ ነዉ።
ታስታዉሱ እንደሆነ ከዘጠኝ ወር በፊት በ23/10/2019 የመጀመሪያ የግድያ ሙከራ በጆሀር ተደርጎበት በነበረ ወቅት በመኖሪያ ቤቱ የነበሩትን የግል ጠባቂዎች እንዲነሱ በማድረግ “በማይታወቁ ኃይሎች” (በዚህ ፅሁፍ ዉስጥ የተጠቀሱቱ አራት የኤርትራ የፀጥታ ኃይሎች) የጆሀር ጠባቂዎች በድንገት እኩለ ለሊት ላይ እንዲነሱ በተደረገበት ወቅት ቢሄዱ ኖሮ በሚከሰተው ክፍተት እነዚህ አራቶቹ የፀጥታ ኃይሎች ምንም አይነት ምልክት ለይተዉ ገለዉት እንዲሰወሩ የተቀናበረ ስልት ነበር የከሸፈዉ።
ይህም በመሆኑ ጠባቂዎቹ፣ እራሱ ጆሀርና የኦሮሞዉ ወጣት በወሰዱት ፈጣን እርምጃ በዚያ ለሊት የጆሀር በህይወት ተርፎ፤ ወደ ዉጭ ሀገርም ወጥቶ ተመልሶም ለሁለተኛ ጊዜ በተጠነሰሰለት መርሃ ግብር እስኪያዝ ድረስ የሰራቸዉን ስራዎች ለመስራት በቅቷል። ይህም በመሆኑና አቶ ጆሀር ወደ ደጅ ወጥቶ ከተመለሰ በኋላ በስፋት በመንቀሳቅውሱና ህዝባዊ ተቀባይነቱም በጣም እየጎላ በመምጣቱ የሁለቶቹ መሪዎች የጥምረት ዕቅዳቸዉ ጥያቄ ዉስጥ እየገባ በመምጣቱ ሁለቶቹ መሪዎች በተከታታይ በሚስጢር እየተገናኙ ጆሀርን ወይ በግድያ ካልሆነም በእስር ከጨዋታ ሜዳ ከማጥፋት በታች ሌላ አማራጭ አልታያቸዉም። በመሆኑም ወደሚቀጥለዉ እርምጃቸዉ ተሸጋገሩ። ከተኬደባቸዉም ሚስጥራዊ ሴራዎች መካከል፤
1. በኢትዮ ኤርትራ አምባሳደርና ቀንደኛዉ የክፋት አማካሪ አቶ ሠመረ ርዕሶም ሁለት ጊዜ በሚስጥር ከጠ/ሚ/ር አብይ ጋር ለብቻቸዉ በመገናኘት
2. የአቶ ኢሳያስ ኦፊሴላዊ አማካሪ የሆነዉ የማነ መንኪን በመጨመር ለ3ኛ ጊዜ የሚስጢር ስብሰባ በማድረግ
3. በመጨረሻም የዕቅዳቸዉን አተገባበር በጋራ ለመከወን ኮሮና ስጋት ሆኖ በኢትዮጵያ በጎላበት ወቅት በ03/05/2020 ኢሳያስ አፈወርቂን ወደ አዲስ አባባ በማምጣት ከላይ ከተጠቀሱት ግለሰቦች ጋር ጠ/ሚ/ር አብይን ጨምሮ ለአራት በመሆን የጁን 29 ቀን 2020 ክስተት ያለበትን አንኳር እቅዶች ቀርፀዉ ተለያዩ።
በዚህ እቅድ ዶ/ር አብይ አህመድ ያላንዳች ፈታኝ ተግዳሮት ላለሙት የጊዜ ቀመር ተመራጭና ብቸኛ ተወዳዳሪና አሸናፊ መሪ ሆነዉ እንዲቀጥሉ የአሁኑን ወሳኝ ጊዜ ለመሸጋገር፤
1. የምርጫ ጊዜን ላልትወሰነ ጊዜ ማራዘም
2. በዚህ ዉሳኔ የሚነሱትን ችግሮች እንዴት ማለፍ እንደሚገባ
3. ጆሀርን ጨምሮ ተቃዋሚዎች የሚለቀሙበትና እንቅፋት ከመሆን የሚፀዱበት ሴናሪዮ መፍጠር (ጁን 29 ቀን 2020)
4. ከዚህ በኋላ ለምትቀጥለዋ ኢትዮጵያ አብይ በአሸናፊነት እንደሚቀጥል መክረዉ የቤት ሥራዉን ለአብይና ለህቡኡ የፀጥታ ኃይል ሰጥተዉ ተለያዩ።
እኔንም ይህን መልዕክት ለመፃፍ ያነሳሳኝ ለዚህ እቅዳችሀዉ ማስፈፀሚያ ሆኖ የተገደለዉ ንፁህ ሃጫሉ ሁንዴሳና የጆሀር መታሰር ነዉ። ጆሀርን የማሰርና ከፖለቲካ ምህዳር ለማዉጣት መዘጋጀት የነበረበት ወጥመድ ነበርና ይህንኑ አዘጋጅቶ ማጥመድ ነበር። ይህም እንዲደረግ የተፈለገበት ምክንያት የጆሀር ተሰሚነትና በህዝቡ ዉስጥ ያለዉ ተቀባይነት በቀጥታ እርምጃ ቢወሰድበት የሚያስከትለዉን ህዝባዊ አመፅ አስቀርቶ እሱን ምክኒያታዊ በሆነ ዘዴ ማግለል ተከወነ።
ጆሀርን ከግድያ ጋር በተያያዘ ወንጀል ለመያዝ ሲባል ብዙ ለግድያ የቀረቡ እጩዎች ነበሩ። ሃጫሉ የተመረጠዉ ከነበርዉ ኪነጥበባዊ ዝናና ተወዳጅነት ሊኖረዉ የሚችለዉን ህዝባዊ ተቃዉሞ ከግንዛቤ በማስገባት ህዝብ በሱ ሞት ተረብሾ በሚናወጥበት ቅፅበት ዉስጥ የሚፈለገዉን ጆሀርን መያዝ በሁለተኛዉ ሰዉ ሳቢያ የሚከተለዉን ህዝባዊ አመፅ ለመቀነስ ነዉ።

The fight for justice in Ethiopia