አሳፋሪ አካሄድ: “አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአሜሪካ የተካሔደው የኢዜማ ውይይት ላይ ከምርጫ በፊት በዘር የተደራጁ ኃይሎች በህግ መታደግ አለባቸው፣

Above Single Post

አሳፋሪ አካሄድ

“አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአሜሪካ የተካሔደው የኢዜማ ውይይት ላይ ከምርጫ በፊት በዘር የተደራጁ ኃይሎች በህግ መታደግ አለባቸው፣ የክልል ልዩ ኃይል መፍረስ አለበት፣ ክልሎች እንዳዲስ መዋቀር አለባቸው ከዚያ በፊት ምርጫ መደረግ የለበትም፤ ኢትዮጵያ በክልሎች ካሳራ መጠናከር አለባት፣ ለዚህም ሰነዱ አዘጋጅተናል፤ የመንግስት ሰዎች እያነበቡት ነው፤ ዝርዝር ይዘቱን አልነግራችሁም ጠላት እንዳይጠቀምበት አሉ። ከላይ ከነገሩን በላይ ምን ሚስጥር ይኖረዋል?!
እንግዲህ አንድ ተረት አለ፤ በድመቷ አንገት ላይ ቃጭሏን የሚያስረው ማነው? የሚል! እነርሱ ዶ/ር ዓብይን ያጩት!
ይህ ምክር እኮ ጦርነት አሁኑኑ እንጀምር የማለት ያህል ነው፤ ኢዜማ ስልጣን በአቋራጭ ከአብይ ተጠግቶ ለማግኘት እንጂ ተወዳድሮ በምርጫ ለማሸነፍ የፈለገ አይመስልም፤ የሚቀናቀኑትን የብሄር ድርጅቶች ቀድሞ በህግ እንዲታገዱለት ይፈልጋል። ይሄ አሳፋሪ አካሄድ ነው።”

Wow! The Dictator advice! another Mengistu H/Mariam

Ethiopia -ESAT የኢዜማ ፖርቲ አመራር ተወካዮች የፖርቲውን ዓላማና ፕሮግራም ለማስረዳትና ውይይት ለማካሄድ በአትላንታ ጆርጂያ July 2019


የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ጋጋታ ለልባዊ ሕዝባዊ ድጋፍ ማረጋገጫ አይሆንም

ግንቦት 8 1981/May 16, 1989 በኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር ጄኔራል መኮንኖች የተመራ መፈንቅለ መንግስት በኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም መንግስት ላይ ተሞክሮ መክሸፉ ይታወሳል፤ ከመፈንቅለ መንግስቱ ጋር በተያያዘ የኮሎኔል መንግሥቱ መንግሥት አባላትና ደጋፊዎቹ የኮሎኔሉን መንግስት በመደገፍና መፈንቅለ መንግስቱን የመሩትን ጄኔራል መኮንኖች በመኮነንና በማዉገዝ ሕዝቡን ያለፍላጎቱ በጉልበት፣ በካድሬና በቀበሌ ቅስቀሳ በማስገደድ መንግስትን ለመደገፍ ከሁለት ሳምንታት በላይ ለፈጀ ጊዜ ያልተቋረጠ ሰላማዊ ሰልፍ በመላ አገሪቱ ሲያስወጡ ነበር፣ የሰላማዊ ሰልፉ ጋጋታ ግን የኮሎኔል መንግስቱ መንግስት በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነትን እንዲያተርፍ ሊረዳ አልቻለም፣ በመሆኑም ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም በጣም የሚወዱትን የአራት ኪሎዉን ቤተመንግስትና ብዙ ሲደሰኩሩለት የነበሩትን እናት ኢትዮጵያን ትተዉ ከመፈንቅለ መንግስቱ በኋላ ልክ በሁለት ዓመቱ, ግንቦት 14 1983/May 22 1991 ወደ ስደት ፈርጥጠዋል።

ከአሰቃቂ የሕዝባዊ መብት ጥሰት፣ ከግድያ፣ ከእስር፣ ከመፈንቅለ መንግስትና ከአመጽ ሊለይ ያልቻለ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አሁንም በጽንፈኛ ሃይሎች የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደርጎ ከፍተኛ የአገሪቱ የጦር መኮንኖችና የክልል ከፍተኛ መሪዎችን ሕይወት መቅጠፉን ሥልጣን ላይ ባለዉ መንግስት እየተነገረ ነዉ፤ ከዚሀም መፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘና መፈንቅለ መንግስቱን በማሳበብ የመንግስት አባላትና ደጋፊዎች ለኮሎኔል አብይ መንግስት የድጋፍ ሰልፍ ለማስወጣት በመላ አገሪቱና በዉጭ አገሮችም ጭምር ከፍተኛ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። 

የሕዝቦችን ትክክለኛ ልባዊ ድጋፍ ማግኘት እንዲቻል ወሳኙ ለሕዝቦች ብሶትና ጥያቄዎች ትኩረት ሰጥቶ አግባብ ያለዉ ምላሽ መስጠትና፣ በተለይ ደግሞ ባሁኑ ወቅት እየተከሠቱ ባሉ ግጭቶችና ቅራኔዎች ዙሪያ ሰዎችን ማሰር ፣ማንገላታትና መግደል ሳይሆን በዉይይት ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠትና መስጠት ብቻ ነዉ። የተፎካካሪ ፖለቲካ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎች እያሰሩና እያንገላቱ፣ በብዙ ቦታዎች በተለይ ኦሮሚያ ዉስጥ የሕግ የበላይነት ለማስከበር በሚል ሰበብ ባገሪቱ የመከላካያ ሰራዊትና የጸጥታ ክፍል ሃይሎች የተፎካካሪ ድርጅት አባላትና ደጋፊዎችን ማስፈራራት በሰፊዉ ቀጥሎ በሚካሄድበት ሁኔታ ሥር ለመንግስት ድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራት ተላላነት ነዉ።

በግልጽ በቅራኔና በግጭት የተወጠረን ሕዝብ ወደ ስምምነት መድረክ ማምጣት ሳይቻል እንዲያዉም ያሉት ልዩነቶች እየሰፉ እንዲሄዱ እየተደረገ፣ በተራ የፖለቲካ ብልጣብልጥነት ጨዋታ ብቻ የተረጋጋ ሰላም ማስፈንና ብሎም የአገር ግንባታ የማይታሰብ ጉዳይ ነዉ በተመሳሳይ ሕዝቡ ያለፍላጎቱ ሰልፍ እንዲወጣ ተጸእኖ ማድረግና ፕሮፓጋንዳ ማካሄድ ከንቱ መሆኑን የኮሎኔል መንግስቱና የሕወአት መራሹ የኢሕአዲግ መንግስት ተመክሮ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነዉ

Dábessá Gemelal

AJAA’IBA Daaw’adhaa! Hidhaa Booda Adeemsa Asaamminoo Tsiggee

Adeemsa Asaamminoo Tsiggee gabaabumatti waan ibsu

Below Single Post

1 Comment

  1. 1ኛ. ለ27 ዓመታት ከፊንፊኔ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮችና ነባር የፊንፊኔ ነዋሪ ኦሮሞ ወደ ቄያቸው ተመልሰው ሳይቋቋሙ፣
    2ኛ. የፊንፊኔ ከተማና ፊንፊኔ ዙሪያ ዞን ድንበር መሬት ላይ ሳይቀመጥ፣
    3ኛ. የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ህገ መንግሥታዊ መብት አዋጅ ወጥቶ ተግባራዊ ሳይደረግ የፊንፊኔ ምርጫ የማይታሰብ ነው። ጊዜያዊው የታከለ ኡማ አስተዳደር 10 አመት ለምን አይሆንም በዚሁ ይቀጥላል እንጂ እነዚህ ቅድሚያ ሁኔታዎች ሳይሟሉ የፊንፊኔ ምርጫን ማሰብ አይቻልም። ሀገር አቀፍ ምርጫ ጊዜውን ጠብቆ ቢካሄድም የፊንፊኔ ምርጫ ለማድረግ እነዚህ የቤት ሥራዎች አሉበት።

Comments are closed.