አራት ኢትዮጵያውያን የWHO የመን ጽ/ቤት ሰራተኞች ለዶ/ር ቴውድሮስ ..

አራት ኢትዮጵያውያን የWHO የመን ጽ/ቤት ሰራተኞች ለዶ/ር ቴውድሮስ ደህንነት ተብሎ ከስራ ተባረው ታሰሩ

በወንድወሰን ተክሉ

(አባይ ሚዲያ) — የWHO ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴውድሮስ አድሃኖም ለደህንነቴ ያሰጉኛል ያላቸውን አራት በየመን የድርጅቱ ሰራተኛ ኢትዮጵያውያን ከስራ እንዲባረሩና እንዲታሰሩም ማድረጋቸው እንታወቀ።

አራት ኢትዮጵያውያን የWHO የመን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አባልነታቸው ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲሰሩ እንደነበረ ተገልጾ ዶ/ር ተውድሮስ ጽ/ቤቱን በጎበኙበት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ በየመን ባደረጉት ጉብኝት ከኢትዮጵያውያኑ ለደህንነቴ የሚያሰጋ እንቅስቃሴ አይቻለሁ በማለት በየመን ባለስልጣናት አራቱን ኢትዮጵያውያን እንዳሳሰሩ ለማወቅ ተችላል።

የታሰሩት አራቱ ኢትዮጵያውያን የእኛ ጥፋት ሆኖ የተገኘው ኦሮሞነታችን እንጂ ዶ/ሩን ቀርበን ለማጥቃትም ሆነ ለማስፈራራት ያደረግነው ምንም ዓይነት እርምጃ የለም ሲሉ የዶ/ር ቴውድሮስን ክስ ውድቅ አድርገዋል

አራቱ ኢትዮጵያውያን ሙሳ ጀማል ሁሴን፣ሀሰን ፈይሶ ቡልቱም፣ጀማል አህመድ እና ካሚል ዱል ወርወርሶ እንደሚባሉ ታውቃል።

ዶ/ር ቴውድሮስ አድሃኖም ለWHO ዳይሬክተርነት ሲወዳደሩ ከኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን ስራቸውን ከጀመሩም በሃላ በኢትዮጵያውያንን ፍርሃት ተሞልተው በደህንነት ሃይል እየተንቀሳቀሱ ያሉ መሆናቸው ታውቃል