አሜሪካ የቪዛ ጠያቂዎችን የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ መጠየቅ ልትጀምር ነው

አሜሪካ የቪዛ ጠያቂዎችን የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ መጠየቅ ልትጀምር ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ የቪዛ ጠያቂዎችን የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎችውን እንዲያቀርቡ ልታደርግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአሜሪካ መንግስት እንዳስታወቀው የቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያ አድርሻቸውን፣ የአምስት አመት የኢሜል መልዕክቶችን እና ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስገቡ ይደረጋል ብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት የዚህ አሰራር አቅድ ይፋ ሲሆን ባለስልጣናት በየአመቱ 14 ነጥብ 7 ሚሊየን ሰዎች በአሰራ ምክንያት ተፅዕኖ ይደርስባቸዋል ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር፡፡

ዲፕሎማቶችን እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዚህ አሰራር ማለፍ እንደማይጠበቅባቸው ነው የተነገረው፡፡

ነገር ግን ለትምህርትና እና ለስራ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ሰዎች መረጃዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ተወስኗል፡፡

ህጋዊ ጉዞን ለመደገፍና ለአሜሪካውያንን ዜጎች ጥበቃ ለማድረግ ወደ አሜሪካ የሚገቡ ሰዎችን መረጃ የማጣራት ሂደት ለማሻሻል አየተሰራ ነው ሲል መንግስት ገልጿል፡፡

ምንጭ፡FBC

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.