አማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተዘጋጀ አጭር የስራ መቁጠሪያ ቼክሊስት

አማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተዘጋጀ አጭር የስራ መቁጠሪያ ቼክሊስት

ሐምሌ/2012 ዓ.ም: ባህርዳር

በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የተዘጋጀ አጭር የስራ መቁጠሪያ ቼክሊት

1. የፓርቲ ግንባታ ስራችን ማጠናከር፡

1.1 አደረጃጀቶችን ማጠናከር

 • ያለ ጠንካራ አደረጃጀት ጠንካራ  ፓርቲ  ስለማይገነባ  በየደረጃው  ያሉ  አደረጃጀቶችን  ማጠናከር ፡-አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ድርጅት ስራ አመራር፣ (በሁሉም ማህበራዊ  መሰረት  ያሉ  ህዋስ  እና መሰረታዊ ድርጅቶችን፣ ወጣትና ሴት ሊጎችን)
 • በተጨባጭ ከክልል በሚወርዱ አጀንዳዎች እና በራሳቸው አጀንዳ እየቀረጹ የሚወያዩ መ/ድርጅቶችና ህዋሳትን ማረጋገጥ
 • የተጓደለ አመራር ያላቸውን መሰረታዊ ድርጅቶችና ህዋሳት መሪ እንዲኖራቸው ማድረግ

1.2 የአመራሩንና አባላት አቅም ግንባታ ስራን ማጠናከር

 • መደበኛ የአቅም መገንቢያ የመሰረታዊና ህዋስ ውይይቶች ሳይቆራረጡ እንዲሄዱ ማድረግ
 • ያለንበት ወቅታዊ  ሁኔታና  ልንወስዳቸው  በሚገቡ  ጥንቃቄዎች  በሚለው  ሰነድና  በቀጣይ  ሁለት ወራት እቅድ  ላይ  ሁሉም  መ/ድርጅቶችና  ህዋሳት  ሙሉ  አባሎቻቸውን  ይዘው  እንዲወያዩ ማድረግ፣ በተመረጡ መ/ድርጅቶችና ህዋሳት የውይይቱን አጠቃላይ ሁኔታ ማየት
 • የአመራሩንና አባላትን አቅም በሚወርዱ ሰነዶች ላይ ተመስርቶ በሚደረግ ውይይትና በተግባር ስምሪት እያበቁ መሄድ፣
 • ወቅታዊ የፖለቲካና ጸጥታ ስራዎችንና የክረምት የልማት ስራዎችን ከመምራት አኳያ  የዞንና  ወረዳ አመራሩ ያሉበትን ጉድለቶች ለይቶ መሙላት

2. በወቅታዊ ጉዳዮችና በቀጣይ ሁለት ወራት እቅድ ላይ የሚካሄዱ ውይይቶች በአግባቡ እንዲካሄዱ ማድረግ

 • ከዞን እስከ ህዝቡ ድረስ አመራሩ፣ አባላት፣ ጠቅላላ  መንግስት  ሰራተኛ፣  የጸጥታ  ኃይሎችና  መላ ህዝቡ የሚሳተፉበት መድረክ  በበቂ  ቅድመ  ዝግጅት  በተሟላ  የሰው  ኃይል  በማስፈጸሚያ እቅዱ መሰረት በተቀመጠላቸው ጊዜ እንዲካሄድ ማድረግ
 • መድረኮቹን የተሻሉ አመራሮች እንዲመሯቸው ማድረግ
 • የጠላት ኃይልን ሀገር ማተራመሻ ስልት እና ልንወስዳቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎችን በግልጽ ማስረዳት
 • በመድረኮቹ ህዝቡን ስናደራጅ ከመንግስት ተቋማት በተቃርኖ እንዳይሄድ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡የምንደራጀው ራሳችን ለመከላከል እንጂ ማንንም የማጥቃት ፍላጎት የለንም፡፡

3. አዳዲስ አባላትን በማፍራት የድርጅታችን መሰረት ማስፋት

 • በአስተሳሰባቸው የተሻሉና በተግባር አፈጻጸማቸው ግንባር ቀደሞችን በመለየት አዳዲስ አባላትን ወደ ድርጅታችን ማቀላቀል፣ ወጣቶችና ሙህራን ላይ ትኩረት አድርገን አባል

ወቅታዊ ሁኔታችንና ልንወስደው የሚገባ ጥንቃቄ በሚል መነሻ ሀሳብ  የተዘጋጀ  ሰነድእና  ቀጣይ ሁለት ወራት እቅድ ላይ የሚካሄድ ውይይት ማስፈጸሚያ እቅድ

መግቢያ

እንደሚታወቀው ከሰኔ መጨረሻ ሳምንት ጀምሮ ክልላዊና ሀገራዊ  ወቅታዊ  የፖለቲካና  የሰላምና ደህንነት ሁኔታችን የሚዳስስ ሰነድ ተዘጋጅቶ ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ በርካታ መድረኮችን አካሂደናል፡፡በመድረኮቹ ያለንበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለአመራሩ፣ አባላትና  መላ  ህዝባችን  መረጃ ለመስጠትና ለመግባባት ጥረት ተደርጓል፡፡ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ በጣም ተለዋዋጭና  ኢ  ተገማች  ስለሆነ  በየጊዜው  የሚስተዋሉ  አዝማሚያዎችንና  የሚከሰቱ  ድርጊቶችን  መሰረት   በማድረግ አጫጭር  ሰነድ  እያዘጋጁ  ተከታታይነት  ያለው  ውይይት  ማካሄድ  አስፈላጊ  ነው፡፡በተደጋጋሚ በግምገማ ሰነዶቻችን በግልጽ እንዳስቀመጥነው የለውጥ ሃይሉ በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ  የመጣና አሁንም በማስመዝገብ  ላይ  ያለ  ቢሆንም  የለውጥ  አደናቃፊ  ሃይሉ  /ጽንፈኛ  የህወሃት  ቡድን  ኢትዮጲያን  ለማፍረስ  ያለ  የሌለ  አቅሙን  ተጠቅሞ   ሌት   ተቀን   እየሰራ   ነው፡፡ስለሆነም  ይህን የተገነዘበ አመራር ማረጋገጥ ስለሚያስፈልግ ‹‹ወቅታዊ ሁኔታችንና ልንወስደው የሚገባ ጥንቃቄ›› በሚል መነሻ ሀሳብ ለአመራሩ፣ አባላትና  ህዝቡ  መወያያ  የሚሆን  ሰነድ  ተዘጋጅቶ ውይይት እየተደረገበት  መሆኑ  ይታወቃል፡፡የተጀመረው  ውይይት  የበለጠ  ጥልቀትና  ብስለት እንዲኖረው ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑና የቀጣይ ሁለት  ወራት  እቅዳችን  አስተሳስሮ  ማወያየት  ተገቢ በመሆኑ የሚኖሩን  መድረኮች  እንዴት  መመራት  እንዳለባቸው  የሚያመላክት  አጭር  ማስፈጸሚያ እቅድ እንደሚከተለው  የተዘጋጀ  ሲሆን  ዞኖችና  ከተሞች  የራሳችሁን  ነባራዊ  ሁኔታ መሰረት ያደረገ እቅድ በማዘጋጀት ውይይቶቹን በብቃት መምራት ይጠበቅባችኋል፡፡

1. የማስፈጸሚያ እቅዱ ዓላማ

የመዋቅራችን  የመፈጸም   አቅምና   ውጤታማነት   ማረጋገጥ፣በክልላችን   ዘላቂነት   ያለው   አስተማማኝ ሰላም በማስፈን የተረጋጋ ክልላዊ ሁኔታ በመፍጠር  ለአገራችን  ሰላምና  ደህንነት  የድርሻችንን  መወጣት፣  የጀመርናቸውን  የልማትና   መልካም   አስተዳደር   ስራዎች   የህዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ ሁኔታ ማከናወን

2. የማስፈጸሚያ እቅዱ ግቦች፡-

 • ያለንበትን ወቅታዊ  ሁኔታ  አመራሩ፣  አባላትና  ህዝቡ   በግልጽ   እንዲረዳ   ማድረግ በተለይም ለውጥ አደናቃፊው  የህወሃት  ቡድን  ይችን  ሀገር  ለማፍረስ  አማራ  ክልልን ማዕከል አድርጎ እየሰራቸው ያሉ የፖለቲካ ሸፍጦችንና  ሊሰራቸው  ያቀዳቸውን  የጥፋት  ድግሶች በውል ማስረዳት፣
 • የጠላት ሃይል በደገሰልን የጥፋት ድግስ ህዝባችን ለጥቃት እንዳይጋለጥ በዓላማ ጽናት፣በቁርጠኝነት እና በህዝባዊ ወገንተኝነት ስሜት ሌት ተቀን በጊዜ የለኝም ስሜትና በታታሪነት የሚሰራ አመራርና አባላት በተልዕኮ ላይ ተመስርቶ መገንባት፣
 • በየደረጃው ላለው አመራር፣አባላትና መላ ህዝባችን በቀጣይ ሁለት ወራት ልንሰራቸው ባቀድናቸው እቅዶች ላይ የተሟላ ግልጽነት እና ጠንካራ ንቅናቄ መፍጠር፣

3. መድረኮቹን ለማሳካት የሚከናወኑ ተግባራት

3.1  በቅድመ  ዝግጅት  የሚፈጸሙ  ተግባራትን  ለይቶ   በብቃት   መፈጸም፡-  የተሟላ የቅድመ ዝግጅት ስራ ከተሰራ በተግባር ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማ  ይሆናሉ፡፡  ስለሆነም በቅድመ ዝግጅት የሚከናወኑ ተግባራትን  የየአካባቢውን  ነባራዊ  ሁኔታ  መሰረት  በማድረግ በአግባቡ ለቅሞ ይዞ መፈጸም ይገባል፡፡

 • ሰነድ ማዘጋጀት፡–  የክልሉን   ሰነድ   መነሻ   በማድረግ   የየዞኑን/ከተሞችን   ነባራዊ   ሁኔታ  የሚገልጹ ሶስት ሰነዶች መዘጋጀት አለባቸው  ፡፡አንደኛ  ወቅታዊ  ሁኔታችንና  ልንወስደው  የሚገባ ጥንቃቄ በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ሰነድ  በየአካባቢው  ህወሃት  በተጨባጭ  እያደረገችው  ያለው  ድርጊቶች  ተጨምሮበት  ይዳብራል፡  ሁለተኛው  የቀጣይ  ሁለት  ወራት  እቅድ   እና  ሶስተኛው  መድረኮቹ  የሚመሩበት  ማስፈጻሚያ   እቅድ   ተዘጋጀቶ   በድርጅት   ስራ   አመራር ኮሚቴና አስተባባሪ ኮሚቴ መገምገም  አለበት፡፡ከተገመገመ  በኋላ  ለወረዳዎች/ከተሞች  እንዲወርድ ይደረጋል፡፡ወረዳዎችና ከተሞችም በተመሳሳይ ሰነድ ያዘጋጃሉ፡፡
 • በየመድረኩ የሚሳተፉ ተሳታፊዎችን በአግባቡ መለየት፣ቀድሞ ጥሪ ማስተላለፍ
 • መድረክ የሚመሩ ጠንካራ አመራሮችን መየለት እና ግልጽ ኦረንቴሽን መስጠት
 • የመወያያ ቦታዎችን ማዘጋጀት፡-የመወያያ  ቦታ  ዝግጅት  የኮሮና  ወረርሽኝ  መከላከል  አዋጅን ባከበረ መንገድ ሰፋፊ አዳራሾችን መጠቀም

3.2 መድረኮችን ማካሄድ

3.2.1 በክልል ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • ሁሉም የክልል  ቢሮ  ኃላፊዎች፣  ምክትል  ኃላፊዎች፣ኤጀንሲ  እና  የልማት   ድርጅት አመራሮች፣  የዞን  አስተዳዳሪ፣  ሶስቱ  የዞን  ብልጽግና   ኃላፊዎች  እና  የዞን  ወጣትና  ሴት   ሊግ ኃላፊዎች የሚሳተፉበት መድረክ ይካሄዳል
 • የማዕከላዊ ዞን የብልጽግና አባላት በየህዋሳቸው ይወያያሉ
 • የክልል ቢሮዎች፣ኤጀንሲዎች፣ ተጠሪ መ/ቤቶች እና ልማት ድርጅት ሰራተኞች በየመስሪያ ቤታቸው ይወያያሉ

3.2.2 በዞን ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • የዞን ጠቅላላ አመራር፣የወረዳ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት፣ወጣትና ሴት ሊግ ኃላፊዎች፣የኮሌጅ፣ የሆስፒታል አመራሮች የሚሳተፉበት መድረክ በዞን ማዕከል ይካሄዳል
 • የዞን መምሪያ አባላት በየመሰረታዊ ድርጅታቸው ይወያያሉ
 • የመምሪያ ጠቅላላ መንግስት ሰራተኞች በየመምሪያቸው ይወያያሉ

3.2.3   በወረዳ ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • የወረዳ ጠቅላላ አመራር፣የቀበሌ ዋና ዋና አመራሮች የሚሳተፉበት መድረክ  በወረዳ/ከተማ ማዕከል ይካሄዳል፡፡የዞን አመራርና የወረዳ አስተዳዳሪና  ፓርቲ  ጽ/ቤት  ኃላፊ ይመሩታል፡፡
 • የወረዳ ሴክተር  መንግስት  ሰራተኛ  አባላት  በመሰረታዊ  ድርጅት  ደረጃ፣ቁጥራቸው የሚበዛ ከሆነ በክላስተር፡፡የመሰረታዊ ድርጅት አመራሮች ይመሩታል፡፡
 • የወረዳ ጠቅላላ መንግስት ሰራተኛ በየክላስተራቸው/ማለትም ኢኮኖሚ ክላስተር፣ ማህበራዊ ክላስተር፣ መልካም አስተዳደር ክላስተር/ ጠንካራ አመራር ተመድቦላቸው ይወያያሉ

3.2.4 በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • የቀበሌ መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች፣ የህዋስ  መሪዎች፣የሚሊሻ  ኮማንደሮች፣  አባል  የሆኑ የገጠር  መንግስት  ሰራተኞች፣  ፖሊስ  ኦፊሰር፣የተቋማት  አመራሮች፣  የቀበሌ  ወጣትና ሴት ሊግ ስራ አስፈጻሚዎች የሚሳተፉበት መድረክ በቀበሌ ማዕከል ደረጃ ይካሄዳል፡፡የወረዳ አመራር ይመራዋል፡፡
 • የቀበሌ ሚሊሻዎችና የግል ታጣሚዎች የሚሳተፉበት መድረክ በቀበሌ ማዕከል ደረጃ ይካሄዳል፡፡ከወረዳ የተመደበ  አመራር  ከቀበሌ  የጸጥታ   አመራሮች   ጋር   መድረኩን   ይመራል፡፡
 • የሃይማኖት አባቶች፣ሀገር ሽማግሌዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መድረክ
 • የወጣቶች መድረክ

3.2.5 በቀጠና/ በህዋስ ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • የአ/አደር አባላት መድረክ በቀጠና ደረጃ ይካሄዳል ጠንካራ  የቀበሌ  አመራርና  አባል  ባለሞያ ተመድበው ይመሩታል፡፡ከወረዳ የተመደበ አመራር ቀበሌ ማዕከል  አካባቢ  የሚኖረውን መድረክ ይመራል፡፡ሌሎቹን የቀጠና መድረኮች ያስተባብራል፡፡
 • የጥቃቅን አባላት መድረክ በየመሰረታዊ ድርጅታቸው እንዲወያዩ ይደረጋል፡፡
 • የገጠር ህዝብ  መድረክ  በቀጠና  ደረጃ  ይካሄዳል፡፡የአባላትን  መድረክ   እንዲመሩ የተመደቡ አመራሮና ባለሞያዎች ይመሩታል፡፡
 • የከተማ ህዝብ መድረክ በብሎክ ደረጃ ይካሄዳል፡፡የከተማና የከተማ  ቀበሌ  አመራሮች  በጋራ መድረኩን ይመሩታል፡፡

4. በመድረኩ መጨበጥ ያለባቸው ጉዳዮች

 • የጸረ- ለውጥ ሃይሉን የህወሃት  ጠላትነትና  ሀገር  የማፍረስ  ተልዕኮ  በግልጽ ለአመራሩ፣ለአባላችን፣ ለህዝቡና ለመንግስት ሰራተኛው ማስጨበጥ፣ ሊወሰዱ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ላይ መግባባት፣ በጋራ ለመስራት መስማማት ይገባል፡፡በውይይቶቹ ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን  የትግራይን  ህዝብ  ከህወሃት  ጋር  ቀላቅሎና  አጃምሎ  መታየት የለበትም፡፡የትግራይ ህዝብ ልክ እንደሌሎቹ የኢትዪጲያ እህት ወንድሞቹ ለውጥ ፈላጊ ህዝብ ነው፡፡ችግር እየፈጠረና  የጥፋት  ተልዕኮ  እየፈጸመ  ያለው  የህወሃት  ዘረፊ  ቡድን  እንደሆነ፣ ለጥፋት ተልዕኮው ህገ ወጥ ጋብቻ ከእነ ኦነግ ሸኔ ጋር  እንደፈጠረ፣  ህወሃት  የምትፈልገውን  ተልዕኮ  እስካሳካላት  ድረስ  ማንኛውንም  የትግል  ስልት  እንደምትጠቀምና  ይህን  አውቆ  የውስጥ አንድነትን በማጠናከር ህዝባችን ከጥቃት መከላከል እንደሚገባ  ከልብ  መግባባት አለብን፡፡
 • የተጀመረው ህግ  የማስከበር  ስራ  ተጠናክሮ  እንዲቀጥል  በሁሉም  ቀበሌዎቻችን   እና በሚፈጠሩ መድረኮች አባላችንና ህዝቡ አቋም እንዲይዝና ውሳኔ ላይ እንዲደረስ ማድረግ አለብን፡፡ለህግ ማስከበር ስራ ቀጥተኛ ተሳታፊና ተባባሪ እንዲሆን መግባባት ይጠበቅብናል፡፡ ምክንያቱም ያለ መላ  አባላችንና  ህዝባችን  ተሳትፎ  በመንግስት  ብቻ  የህግ  የበላይነትን  ማረጋገጥ ስለማይቻል መንግስት ሚናውን ለመወጣት ግልጽ አቋም እንደያዘና በርካታ  እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሆነ በማስረዳት ህዝቡም መንግስትን እንዲያግዝና  ድርሻውን  እንዲወጣ ማድረግ ይገባል፡፡ ከመድረኮቹ ጎን  ለጎን  በግልጽ  ወንጀል  የሰራና  ህገ-ወጥ  እንቅስቃሴ የሚያደርግ አካል ከተገኜ በጠራ መረጃ ላይ ተመስርቶ በህግ ተጠያቂ ማድረግ
 • በየትኛውም የክልላችን አካባቢ ህገ-ወጦችና ጸረ-ሰላም ኃይሎች  ቦታ  እንዳይኖራቸው  በየደረጃው ያለው አመራርና የጸጥታ መዋቅር በቁርጠኝነት ህዝቡን  በማሳተፍ  መስራት እንደሚገባው አቋም ላይ እንዲደርስ ማድረግ አለብን፡፡ወቅቱ የክልላችን ህዝብ  ላይ  አደጋ  ለማድረስ ህገ-ወጦችና ጸረ-ሰላም ሃይሎች ሌት ተቀን እየሰሩ ያሉበት  ወቅት  ስለሆነ  በህገ- ወጥ ተግባር ውስጥ የገባ፣ የሚጠረጠርና የጸረ-ሰላም ሃይሎችን  አጀንዳ  ይዞ  የሚንቀሳቀስን  ሃይል አለመታገልና መደበቅ በየትኛውም መመዘኛ ተወስዶ ቢታይ ህዝባችን ለጥቃት አሳልፎ እንደመስጠት የሚታይ ስለሆነ መላው አባላችንና ህዝባችን  በተጀመረው  መንገድ  ተጠናክሮ  ለራሱና  ለአካባቢው  ሰላምና  ደህንነት  ሲል  ከእንደዚህ  ዓይነት  ድርጊት  መቆጠብ  እና  ሌላውንም መታገል አለበት፡፡
 • የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጀው የሚንቀሳቀሱትን ህወሃትና ኦነግን ከነፈጠራ ትርክታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ግብአተ መሬታቸው በቅርቡ እንደሚፈፀም  ህብረተሰቡን  ማሳወቅና  ለዚህ ስኬት የሚቻለውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ማስገንዘብ። አማራ ጠል የሆኑ ትርክቶችን የሚያሰራጩ  ፤  ለፍቶ  አዳሪ  ህዝባችንን  የሚያዋክቡና  የህዝባችን  ኩራትና  የላእላይነት ተምሳሌት የሆኑትን እምዬ ምኒሊክን ታላቅ ስምና ክብር የሚያጠለሹ ሃይሎችን ያለ ምህረት እንዲከስሙ ማድረግ። አብን  አዲሃን  እና  ኢዜማን  ጨምሮ  ማንኛውም  በክልልላችን የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ተፃራሪ አቋም መያዝ  ፈፅሞ  ተቀባይነት  የሌለው መሆኑን እንዲያውቁ ማድረግ። አፈንጋጭ አባላት ካሏቸው ውስጣቸውን በአስቸኳይ

እንዲያጠሩ ማስጠንቀቅና ተፈፃሚነቱ ታይቶ አስፈላጊ የሆነውን ህግ የማስከበር እርምጃ  ያለ  ርህራሄ መውሰድ።

 • ይህ ወቅት አንድ ሆነን የአማራን ህዝብ ህልውና የምናረጋግጥበት እና ለኢትዮጲያ አንድነት መረጋገጥ የበኩላችንን የላቀ ድርሻ የምንወጣበት ወሳኝ  ጊዜ  ነው፡፡  ማንኛውም  አይነት  አመለካከት ያለው ሃይል  በአማራ  ህዝብ  ደህንነት  ጉዳይ  ላይ  የተለየ  አቋም  ሊኖረው  አይገባም፡፡ በተባበረ ክንድ  ህዝባችን  ከጥቃት  ልንከላከል  ይገባል፡፡አማራንም  ወደ  ቀደመው ክብሩ የመመለስ ትልቅ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ከንግግር ባለፈ ከልብ መግባባት ይጠበቅብናል፡፡
 • የክረምት መደበኛ   የልማትና   መልካም   አስተዳደር   ስራዎቻችን   ሳይቆራረጡ   እንዲቀጥሉ  ማድረግ፣ አባላችንና  ህዝብ  በቀጣይ  ሁለት  ወራት  እንሰራቸዋለን  ብለን  ባቀድናቸው  የክረምት እቅዶች  ላይ  በንቃት  እንዲሳተፍ  ማድረግ  በተለይ  ይህ  ወቅት  የመኸር  ሰብል  ዘር  የሚዘራበት  ወቅት  ስለሆነ  የሰብል   ልማት   ተግባር   ላይ   ርብርብ   ማድረግ   ይገባል፡፡በተጨማሪም የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ማስቀጠል፣የወጣት  ስራ  እድል  ፈጠራ  ስራን  እና  የገቢ  አፈጻጸም ስራችን በላቀ የኃላፊነት ስሜት ለመስራት መተማመን

5. የአፈጻጸም አቅጣጫዎች፣

 • ሁሉንም መድረኮች በመግባባትና  በውጤታማነት   መፈጸም   ይገባናል፡፡የምናካሂዳቸው  መድረኮች የኮሮና በሽታን እየተከላከልን በአሁኑ ጊዜ  ያጋጠመንን  ክልላዊና  አገራዊ  ሁኔታ አመራሩ፣ አባላትና ህብረተሰቡ የተሟላ ግንዛቤ  እንዲፈጥር  ማድረግ  የምንከተለው  ወሳኝ አቅጣጫ ነው፡፡ከዚህ  አንጻር እስከ ኮንፈረንስ  ሊደርስ   የሚችል   መድረክ  ፈጥረን  ከመዋቅራችንና ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚኖረንን የመግባባት ደረጃ ማሳደግ ይገባናል፡፡
 • የአመራር መድረኮችን በክልል፣ በዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ደረጃ በማካሄድ አመራሩ  ከወቅታዊ ስራዎቻችን አንጻር ግልጽነት እንዲፈጥር ይደረጋል፡፡ዞን፣ወረዳና  ቀበሌ  የቀጣይ  ሁለት  ወራት  አጭር እቅድ አዘጋጅተው ለተግባራዊነቱ ይንቀሳቀሳሉ፡፡ የአመራሩ የትኩረት ማዕከል የውስጥ አንድነቱንና ጥንካሬውን  መጠበቅና  ማሻሻል፣  በየደረጃው  የሚገኘውን  የጸጥታ  መዋቅር የመፈጸም አቅምና ውጤታማነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣ የክረምት ወራት የልማት

ስራዎቻችን በትኩረት  መፈጸም  ወሳኝ  የርብርብ  ማዕከል  መሆኑን  አውቆ  መንቀሳቀስ ይኖርበታል፡፡

 • የቅድሚያ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት ለይቶ መንቀሳቀስ  የአመራሩ  መለኪያ ይሆናል፡፡በመሆኑም በየደረጃው ያለው  አመራር  በእንዲህ  ዓይነት  ወቅት  የበለጠ  አንድነቱን ጠብቆ ተልዕኮውን መፈጸም አለበት፡፡የሚከፈል መስዋዕትነት ቢኖርም ለመክፈል መዘጋጀት ይጠይቃል፡፡የላይኛው አመራር ለታችኛው የሚሰጠው ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ  የማስተባበር  ተልዕኮውን በአግባቡ መወጣት የሚያስችል አቅጣጫ መፈጸም ይገባል፡፡

6. የሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው

የሚያስገድድ         በመሆኑ       ያለምንም መዘናጋት በጥብቅ ዲሲፕሊን መድረኮቹን       መምራት
አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው፡፡
Ø  ተለዋዋጭ           ሁኔታ         ሲያጋጥም አመራሩ የትኩረት ማጣት ችግር         ሊያጋጥመው
ይችላል፡፡እንደዚህ          ዓይነት         ችግር ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሚያጋጥም            ችግር

 

 • በቅርብ ከክልል ጀምሮ እስከ መንደር ድረስ በወቅታዊ በጉዳዮች ላይ በርካታ  መድረኮችን ያካሄድን  በመሆኑ  መድረኩ  ድግግሞሽ  አለው፣  አወያይተናል  ብሎ   መዘናጋት   ችግር በአመራሩ ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡ያለንበት ወቅታዊ ሁኔታ ተለዋዋጭና  ኢተገማች ስለሆነ፣ምንም  እንኴ  በወቅታዊ  ሁኔታዎች  ላይ   ውይይት   የተካሄደ   ቢሆንም   አሁን  ለመወያያ የተዘጋጁት ሰነዶች ያደገ አዳዲስ ሀሳቦችን በውስጣቸው የያዙ ስለሆነና ወቅታዊ ሁኔታውም በየጊዜው እየተገናኜን ሁኔታችን እንድንገመግምና አንድነታችን እንድናጠናክር
  ነበር፡፡መፍትሄው የአመራሩን የመፈጸም/ የማድረግ አቅምና ስነ  ልቦና  ማሳደግ  ነው፡፡በአንድ  ጊዜ ብዙ ተግባርን የማከናወን መርህን (Many taska at atime principle) መከተል  አለብን፡፡ያለንበትን  ሁኔታ  በውል  ተረድቶ የክልል  አመራሩ  ወደ   ታች   እየቀረበ መደገፍ አለበት፡፡የሚሰጠው ድጋፍም ውጤታማና ክፍተትን የሚሞላ መሆን አለበት፡፡
 • የጸጥታ ሁኔታችን  አሁን  የተረጋጋ  ቢመስልም   ከውስጥም   ከውጭም   በሚሸረብ   ሴራ   ከሆነ  ቦታ  በሚፈጠር  ግጭት  ወይም  ሁከት  መላ  ክልሉ  ወደ  ግጭት  ቀጠናነት   ሊቀየር   ይችላል፡፡በዚህ ወቅት የአመራሩ  ጥንካሬ  ሊዛባ  ይችላል፣  አለመናበብ  ሊያጋጥም  ይችላል፡፤የገነባነው አመራር በምናስበው ልክ ሆኖ ላናገኘው እንችላለን፡፡ ይህ ችግር ከአሁን በፊትም አጋጥሞ የሚያውቅ ነው፡፡የአመራር አንድነትና የዓላማ ጽናት እንዲሁም ቁርጠኝነት የሚለካው በፈታኝ ወቅት ስለሆነ  የአመራር  ግንባታ  ስርዓታችን  ችግር  እንዳይከሰት  ቀድሞ  አርቆ አስቦ የሚሰራ፣ ችግር ቢፈጠር  እንኴ  በችግር  ጊዜ  የሚጸና  ፊት  ለፊት  የሚጋፈጥ አመራር መገንባት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል፡፡ለዚህ ደግሞ ክልላዊና አገራዊ ሁኔታውን በየጊዜው ማስገንዘብ፣ በተልዕኮ ውስጥ እያስገቡ አቅሙን መገንባት ያስፈልጋል፡፡
 • የስራዎች መደራረብ  የወቅቱ  ፈታኝ  ችግር  ሊሆን   ይችላል፡፡አሁን   ባለንበት   ሁኔታ   እጅግ ተደራራቢ  ስራዎችን  የምንፈጽምበት  ጊዜ  ላይ  እንገኛለን፡፡በርካታ   ፈተናዎችንም   ማለፍ ይጠይቃል፡፡   ወቅቱ   ቶሎ   ቶሎ   ማቀድን   እቅድ   መከለስን   የሚጠይቅ   ነው፡፡በመሆኑም  አመራሩ   የስራ   ክፍፍል   እያደረገ   በመናበብ   ተልዕኮዎችን   መፈጸም   ይጠበቅበታል፡፡ከጊዜው  ጋር የሚመጥን ፈጣን እንቅስቃሴ ማድረግ ይገባል፡፡

7. የድጋፍና ክትትል ስራችን በተመለከተ

 • የክልል አመራር ዞኖችን በአካል ወርዶ እስከ ወረዳ ይደግፋል፣ ዞን አመራር ወረዳ/ከተማን ይደግፋል፣ ወረዳ አመራር ቀበሌን፣ ቀበሌ አመራር ቀጠናን ይደግፋል፡፡
 • ድጋፉ ክፍትን ለይቶ የመሙላትና ችግር  ፈች  በሆነ  መንገድ  መፈጸም  አለበት፡፡ለይስሙላ  ደርሶ መመለስ የድጋፍ ስርዓት መከተል በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡
 • የክልል ብልጽግና ጽ/ቤት አመራሮች ዞኖችን በክላስተር ተከፋፍለን እናስተባብራለን፣ዞንና ወረዳዎችም በተመሳሳይ በተዋረድ ያሉ ተቋማትን እና የሚመደቡ አመራሮችን በክላስተር ተከፋፍለው ያስተባብራሉ፡፡
 • ሰሜን ወሎና ዋግህምራ ብሄረሰብ—–አቶ ፍስሃ ደሳለኝ
 • ደቡብ ወሎ ዞንና ደሴ ከተማ———–አቶ አብርሃም አለኸኝ
 • ኦሮሞ ብሄረሰብና ሰሜን ሸዋ————አቶ ደሳለ በላይ
 • ማዕከላዊ ጎንደር፣ምዕራብ  ጎንደርና  ሰሜን  ጎንደር—-አቶ  መስፍን  አበጀ
 • ደቡብ ጎንደርና  ጎንደር ከተማ———————–አቶ  አማኑኤል ፈረደ
 • ምስራቅ ጎጃም፣ምዕራብ  ጎጃም——-አቶ  ፍቃዴ ዳምጤ እና አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
 • ባህርዳር ከተማ እና ማዕከላዊ ዞን——አቶ ወርቅነህ እና አቶ ጥላሁን

8. የጊዜ ሰሌዳ

* በክልል ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • የክልል አጠቃላይ አመራርና የዞን ዋና ዋና አመራሮች መድረክ ከሃምሌ  17-18/2012 ዓ.ም
 • የማዕከላዊ ዞን አባላት መድረክ በየህዋሳቸው እስከ ሃምሌ 20 እስከ 16/2012ዓ.ም
 • የክልል ቢሮዎች ጠቅላላ መንግስት ሰራተኞች መድረክ ከሃምሌ 20-30/2012 ዓ.ም

*  በዞን ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • በዞን ደረጃ የሚካሄድ አመራር መድረክ ከሃምሌ 21-22/2012 ዓ.ም
 • የመምሪያ መንግስት ሰራተኛ አባላት መድረክ በየመ/ድርጅቱ ሀምሌ 23/2012 ዓ.ም
 • የዞን ጠቅላላ መንግስት ሰራተኞች መድረክ እስከ ሀምሌ 30/2012 ዓ.ም

*  በወረዳ ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • የአመራር መድረክ —ሃምሌ 25
 • የጠቅላላ ሰራተኛ መድረክ————- 28
 • የጠቅላላ መንግስት ሰራተኞች መድረክ—-ሃምሌ 30

*  በቀበሌ ደረጃ የሚካሄዱ መድረኮች

 • በቀበሌ ደረጃ የሚካሄድ የመሰረታዊ ድርጅትና ህዋስ አመራር መድረክ—ሃምሌ 29
 • የገጠር መንግስት ሰራተኞች መድረክ—–ሐምሌ 30
 • የህዝብ መድረክ————–ከነሃሴ 2-3/2012 ዓ.ም

  DW International አማርኛ ዜና ሰዓት 07:00፣ ሀምሌ 20/2012 ዓ.ም

አማርኛ ዜና – የቄሮ ኦሮምያ እና የኦፌኮ መግለጫ የዜጎች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እስኪከበር ድረስ እንደሚታገሉ አስታወቁ። ሀምሌ 17/2012 ዓ.ም