በኦሮሚያ ክልል በ4 ሺህ 460 ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል

በኦሮሚያ ክልል በ4 ሺህ 460 ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል

በኦሮሚያ ክልል በ4 ሺህ 460 ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል


(FANA BC) – አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል በመጀመሪያው ዙር በተደረገው ጥልቅ ተሃድሶ 4 ሺህ 460 ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።

እርምጃ የተወሰደባቸው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ከክልል እስከ ቀበሌ ባለው አደረጃጀት ውስጥ ይመሩ የነበሩ ሲሆን፥ የገጠር ቀበሌ ይመሩ የነበሩ 13 ሺህ 578 ዝቅተኛ አመራሮች ላይም በተመሳሳይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

አስተዳደራዊ እና ፖለቲካዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው አመራሮች በተጨማሪ 694 አመራሮች በብልሹ አሰራር ተገምግመው 260ዎቹ ላይ ክስ የተመስረተ ሲሆን፥ በቀሪዎቹ ላይ ማጣራት እየተደረገ ይገኛል።

ከክልል እስከ ቀበሌ ባለው አደረጃጀት እርምጃ ከተወሰደባቸው ውስጥ በአቅም ማነስ 2 ሺህ 587 አመራሮች፣ በኪራይ ሰብሳቢነት 964 አመራሮች፣ በስነ ምግባር ችግር 397 አመራሮች፣ በግል ችግር 512 አመራሮች መሆናቸውን የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ተናግረዋል።

በቀበሌ ደረጃ የሚገኙ 2 ሺህ 470 አመራሮችን ለህግ ለማቅረብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እና የማጣራት ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑንም ነው የገለጹት።

እንደ አቶ አዲሱ ገለጻ አመራሮቹ ጉዳያቸው ተጣርቶ ክስ እስኪመሰረትባቸው ድረስ የክልሉ የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተለያዩ የንብረት እና ገንዘብ እገዳ ጥሏል።

በዚህም ከ7 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ፣ አራት ተሸከርካሪዎች፣ ሁለት ህንጻዎችና 40 መኖሪያ ቤቶች ታግደዋል።

እንዲሁም 244 ሺህ 326 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት እና በደን የተሸፈነ 548 ሺህ 662 ካሬ ሜትር መሬት መታገዱንም ሀላፊው ገልፀዋል።

አቶ አዲሱ ህዝቡን በማሳተፍ በክልሉ ላለፉት ስድስት ወራት የተካሄደው ጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ ስኬታማ በመሆን ወደ ተግባር ተሽጋግሯል ሲሉም ተናግረዋል።

በመላው ኦሮሚያ በተካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄ መድረክ ከ6 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል።

በክልሉ በተካሄደው መልሶ የማደራጀት ሂደት 5 ሺህ 832 ምሁራን ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ባለው እርከን ወደ ኃላፊነት መምጣታቸውንም ሀላፊው አብራርተዋል።

በኪራይ ሰብሳቢነት ውስጥ የተዘፈቁ እንዲሁም የህዝብና የመንግስት ኃብትን የመዘበሩ ግለሰቦችን በማጋለጥና በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ የህዝብ እና የመንግስት ንብረት በማስመለሱ ሂደት ህብረተሰቡ አሁንም ከመንግስት ጎን እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።

በበላይ ተስፋዬ


While habeshawit [and in fact Christian] Ethiopian image plays the main character, the Oromo makes it to a marginal show up, this time around, in promoting the image of the country to the Arab world.
The scene was filmed presumably at TPLF’s embassy in Qatar, Doha.(Via Girma  Gutema)