አሃዳዊነት የት ቆሞ? የኢሳት ተንታኞች “በሚመጠው ሀገራዊ ምርጫ ‘የአንድነት ሀይሎች’ እና ፌዴራልስት ሀይሎች ይተናነቀሉ!” ይሉናል ።

አሃዳዊነት የት ቆሞ? (በቦና ገዳ)

የኢሳት ተንታኞች “በሚመጠው ሀገራዊ ምርጫ ‘የአንድነት ሀይሎች’ እና ፌዴራልስት ሀይሎች ይተናነቀሉ!” ይሉናል ።

የአብይ መንግሥት አሃዳዊ መሆኑንም ሲደጋግሙት ሰማን ፤ የሚያውቁት ምስጥር ብኖር ነው?! ይሁን አብይንም ከነመደመሩ ይውሠዱት ።
ግን ለመሆኑ አሃደዊነት ህብረ-ብሔሩን ፌዴራልዝም የሚገዳደረው የት ቆሞ ነው? እኩል የተካፈሉት የፍልሚያ ሜዳ አለ ወይ? ኢ/ያ እኮ ብያንስ ህገመንግሥቱ ያወቃቸው ዘጠኝ መንግሥታት አሏት ፤ አስራኛም ልደርስ ነው ። ከእነዚህ ውስጥ ማን ነው ወዶ እና ፈቅዶ መንግሥቱን የሚያፈርሰው? ለበለጠ ሉዓላዊነት እና ነፃነት ፍልሚያው በከረረበት ወቅት ፣የትኛውን ሜዳ ተማመኑ?
“አማራን ፣የደቡብ አናሳዎችን እና የኦሮሚያ ከተሞችን ከያዝን 70% እንሆነለን ።” ይላሉ ፣መቼም ህልም አይከለከልም ።
አማራ እኮ አፍለኛ ብሔርተኝነት ላይ ነው/አፍላ ዕድሜ( fire age)ላይ ያለ ወጣት ነው ፤ ማለቴ ሳይንቴውና ጋይቴው ። ሌላውማ (አዊ ፣ ቅማንት ፣ ዋግህምራና ላስታ የአገው state እያጠቁ ነው ። ወሎም ህብረት እያበጃጀ ነው ፣የጣዝማ በር መሸለኳያም እያሰፋች ነው ይላሉ ።)
ተስፋ የሚጣልባቸው የኦሮሚያ ከተሞች ስንት ብሆኑ ነው? ሳባት መንግስታት ለመሆን የሚጠይቀውን ደቡብ በአሃደዊነት መከጀል አይከብድም?
ወገን ተሰፋ ለስቆረጥህ ከዚህ ቦኋላ የክልል መንግታት ተመልሶ በአቅጣጫና በአውራጃ አይጠሩም! ያ ዘመን ላይመለስ ነጎደ ።
አሁን የመቻቻሉን ፀጋ ከበዛል ፣በ18 የኢ/ያ ፌዴሬሽን( USE) ሆን በኮንፌዴሽን ከልሆንም ከ3-4 ነፃ መንግሥታት መሆነችን አይቀሬ እየሆነ ነው!