“ንጉስ ኃይለ ስላሴ ስመ ጥር፣ እጅግ የተከበሩ የሀበሻ ምድር ንጉስ ናቸው።” ~ አብይ አህመድ

“ንጉስ ኃይለ ስላሴ ስመ ጥር፣ እጅግ የተከበሩ የሀበሻ ምድር ንጉስ ናቸው።” ~ አብይ አህመድ (By Taagal Daaqaa Waaqgaarii)

ይህ ሰው መሳይ አውሬ እነ ታደሰ ብሩን! ማሞ መዘምርን! በሕይወት ቢኖሩ ሰቅሎ ረሽኖ ከመግደል አይመለስም። ዛሬ እነሱ የተሰውለትን አላማ መፃይ የኦሮሞ ልጅን እጣ ፈንታ እያጨለመ እና በነሱ ራእይ እና መስዋእትነት ተኮትኩተው ያደጉ ውድ ብርቅዬ የ ኦሮሞ ልጆችን በዱር በገደሉ እያደነ፣ ከቤታቸው ደጃፍ እያስረሸናቸው ኃይለ ስላሴን ባያሞግስ ነበር የሚገርመው። ተልኮውስ ምንሆነና ጃል! ይህን ሁሉ ግፍ በ ወለጋ እና በ ጉጂ እየፈፀመ፣ የሱን በትረ ስልጣን ማስጠበቅ የኦሮሞን ስም መጠበቅ ኑው ምክንያቱም እኛነን እዛ ስልጣን ላይ ያለነው ለዚህ ዘብ ቁምለት ብትለኝ አልሰማህም። በመጀመሪያ አብይ መች ኦሮሞነኝ አለና። አብይ እኮ ኦሮሞ ነው ወደ ስልጣን ያመጣኝ አላለም። አንድም የኦሮሞ ኢንተረስትን በማስጠበቅ ላይም አይደለም ያለው። ከኦሮሞ ኢንተረስት በተቃራኒ በፀረ ኦሮሞ ተግባር እና ልሳን ተጠምዶ እሚውል ከሀዲ ነው። እሱ ያላለውን! ያላመነውን! በአንደበቱም በተግባሩም የካደውን ነገር እንዴት እሱን ሆንህ ልታስረዳኝ ይዳዳካል? ምነው እሚሞተው ሰው ኦሮሞ አይደለምን? ወይስ የኦሮሞን የሰውነት ዋጋ እስክትክድ ደርሰካል? ስለምንስ በምንስሐ ስሌት ኦሮሞ ለገዳዩ ዘብ ጠበቃ ይሁን ይባላል? የገዳዩን ስልጣን እንዲህ የተጨነክበት ሞራል ምነው ስለሚገደለው እያለቀ ስላለው ሕዝብ እንደ ሰው ለመቆርቆር ስብዕናህን ደፈነው ያስጨከነክ ምን ይሆን? እንጃ ይሄንን! ለኔ ግን ጤነኝነት አይደለም። ሰውኛም አይደለም።
Dábessá Gemelal