ትኩረት የሚያሻው አብይ ጉዳይ!!በOLF እና በODP-መር EPRDF

🌿ትኩረት የሚያሻው አብይ ጉዳይ

የዚህ አጭር ፅሁፍ ትኩረት የሚሆነው
OLF እና በODP-መር EPRDF መካከል እየተካሄደ ያለውን እርቀሰላም ተአማኒነትና ተስፋ-ጫሪነት ጉዳይ ነው

ዛሬ ከመቼውም በበለጠ የኦሮሞ ግድያና አፈና እንዲሁም ከቄየው መፈናቀል አይሎ ቀጥሏል:: ይህም እንግልት: ወከባና የሰብአዊ መብት ገፈፋ እየደረሰ ያለው በአብዛኛው በOLF ደጋፊነት በሚጠረጠሩ አብላጫ የክልሉ ዞኖችና (“#ኦነግ ዛሬ ከፖለቲካ ድርጅትነት አልፎ የኦሮሞ መንፈስ ሆኗል” ያሉትን የፖለቲካ ምሁር ልብ በሉ) ንፁሃን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ እርቀ-ሰላሙስ ቢሆን ዴሞክራሲያዊ ሂደትን ተከትሏል ወይ? የሚለውን ጥያቄ ይጭራል::

ለዚሁም አስረጅነት: –

🐦በእርቀ-ሰላሙ የቴክንክ ኮሚቴ የተካተቱ ግለሰቦች በአብዛኛው የእንድነት / የፌዴራልስት እይታ ያላቸው በመሆናቸው (በፓርቲ ማእቀፍ ታቅፈውና እንደግለሰብም) ከወገንተኝነት የፀዳ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ስለመከተላቸው አስቀድሞም ጥርጣሬ መኖሩ

🐦የእርቀሰላሙ አንድምታና ወዴትነት

ከእርቀሰላሙ በስተጀርባ የእንድነት ሃይሎች በሂደት የሚያደርጉት

-የእሚዬ ሚኒልክ ዓላማ አራማጅ ሃይሎችን የሚፃረር የኦሮሞ አለኝታ የሆነውን OLF ማዳከሙን እንደ አላማ

-ከሌሎች የአንድንት ሃይሎች ጋር መወገንን እንደ ታክቲክ

-እርቀሰላሙን እንደ ስትራቴጂ

ተጠቅመው በማያዳግም ምት OLFን እስወግደው የ#OROMIAFIRST! ትርክትን ከ#Media ና ከጠረጴዛ ዙሪያ ዉይይቶች አርቀው ለዚሁ እኩይ አላማቸውም ከ#ODP ጉያ ተወሽቀው በቀጣዩ የሽግግር ወቅት ህዝቡን እየሸነገሉና : “ህብረብሄርነቱ የተጫነብን የታሪክ ዕዳ ነው” የሚሉትን ወገኖች ማግለልና ማሳደድ ነው

ይህ ጉዳይ በ1992 እዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ OLF ተገፍቶ ከምርጫ ሲገለል ጦሩም በአደራዳሪዎቹ መሰሪነት ካምፕ እንዲገባ ተደርጎ ተኩስ ሲከፈትበት ያኔ በእርቀሰላም ስም የጠፋው ህይወት የባከነው ሀብትና ጊዜ ያን ተከትሎ የደረሰው ስነልቦዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ዛሬ ላይ ቁመን ስናስበው በቁጭት ነዉ። ሰለሆነም እያንዳንዷን የሽግግሩን ሂደትና የኦሮሞና ኦሮሚያን ጥቅም የሚነኩ ድርጊቶችን በአይነ ቁራኛ ለመከታተል በቂ ምክንያት አለን::

በ1992 በLuanda, Angola 🇦🇴 በ#dosSantos የሚመራው #MPLA በ#Savimbi በሚመራው #UNITA ላይ በጊዜው የተካሄደውን presidential & legislative elections ስኬታማና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲሆን ታስቦ በቅንነት የተደረሰ እርቀሰላም ድርድርን በማፍረስ የፈፀመው የጅምላ ፍጅት ወይም#HalloweenMassacre ከ40, 000 በላይ የUNITA ደጋፊዎችን በተለይም ደሞ የ#Ovimbundu ና #Bakongo ጎሳዎች ላይ ያስከተለው እልቂት በእርቀስላም ድርድር ሽፋን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የተደረገ እኩይ ምግባር ነበር::

ይህ በመሆኑ ብርቅዬ ልጆቻችንን ገብረን ያገኘነውን ድል በጩሉሌዎች ዳግም እንዳንቀማ በማሰብ ዛሬም ከ3 አስርት ዓመታት በሆዋላ በ#EPRDF እና በOLF መሃል (ለዚያውም ከ#TPLF ተለጥፎ #OROMOና #OROMIAን እንደ መዥገር ደም ሲመጥና ሲያሳድድ ከኖረ #OPDO ጋር) በድጋሚ ድርድር ሲካሄድ ሂደቱንና ውጤቱን በንቃት እንድንከታተል እንድምታውንም እንድንፈትሽ ከአለፈው ስህተታችን ተምረን ነገ ሊደርስ ያለውን ቀውስ እንዳይደገም ከደረሰም እንድንቋቋም ከወዲሁ በማሰብ ነው

ቸር ይግጠመን

🍃ኦሮሚያ ትቅደም!

Abba Ebba


Baayyinni WBO miliyoona 50 caala,maaltu galchee dandaya??❤️💚❤️. ragaan Baratoota Oromoo Oromia gaafadhaa


ትኩረት

#WBOn lafa seenaa Beegiitti haala kanaan simatamaa jira.
An Haa galu jenna


ትኩረት

Jaal Marroo Ajajaa WBO Zoonii Dhihaa Ijakiyyaanis hin agarre Bilbilaanis hin dubbisne Abbaa Gadaa Bayyanaa Sambatootu Radioni #BBC Afaan Oromoo Irratti Dubbate Dhaggeeyfadhaa!!

Tulluu Hiyyeessaa