ትራንስ ኢትዮጵያ በ372 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የዋና መሥሪያ ሕንፃ ሥራ ጀመረ

ትራንስ ኢትዮጵያ በ372 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የዋና መሥሪያ ሕንፃ ሥራ ጀመረ

Meanwhile in Adama, Oromia Development Association has inaugurated grand huge enormous market centre with cost of 3.3 million Birr. It has 18 4×5 rooms to sell tomato and onions. Local people call it ”gulit”.

Via Biyya Oromiyaa

ትራንስ ኢትዮጵያ

ትራንስ ኢትዮጵያ በ372 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የዋና መሥሪያ ሕንፃ ሥራ ጀመረ

ጎማ ማምረቻ የመገንባት ውጥን አለው

(Ethiopian reporter) — የትግራይ የመልሶ ማቋቋም ኢንዶውመንት ፈንድ (ኤፈርት) በትግርኛው ምኅፃረ ቃል ትዕምት፣ በሥሩ ከሚያስተዳድራቸው ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ትራንስ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገለገልበትን የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት አበቃ፡፡

ትራንስ ኢትዮጵያ ሐሙስ፣ ሐምሌ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ያስመረቀው ባለሰባት ወለል ሕንፃ፣ ሳሪስ አካባቢ የሚገኝና ከዚህ ቀደም ወይራ ትራንስፖርት ድርጅት እያስገነባ የነበረውን ጅምር ሕንፃ በጨረታ ገዝቶ ተጨማሪ ግንባታዎችን አክሎበት ለአገልግሎት ያበቃው ነው፡፡

ከ260 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዛው ይህ ሕንፃ፣ ከ112 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጪ ወጥቶበት እንደተጠናቀቀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚሁ ሕንፃ ምርቃት ጎን ለጎን በቃሊቲ ክራውን ሆቴል አካባቢ ፒሬሊ ከተሰኘው የተሽከርካሪ ጎማ አምራች ኩባንያ ጋር በመሆን ያስገነባውን የፒሬሊ የጎማ አገልግሎት መስጫ ማዕከልም በዚሁ ዕለት ለአገልግሎት በቅቷል፡፡

በሁለቱም የምረቃ ፕሮግራሞች ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የትዕምት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንደገለጹት፣ ለአገልግሎት የበቁት ግንባታዎች የትራንስ ኢትዮጵያን ዕድገት ማሳያ ሞዴሎች ናቸው፡፡

ከመነሻው ከተሰማራበት የጭነት አገልግሎት ዘርፍ በተጨማሪ ፒሬሊ ጎማና ጃፓን ስታር የመኪና ባትሪ ሽያጭ አገልግሎቶችን በማካተት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ትራንስ ኢትዮጵያ፣ በሎጂስቲክና በሌሎችም አዳዲስ የቢዝነስ መስኮች ውስጥ በመግባት ሥራውን እያስፋፋ ነው፡፡

የትራንስ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ ዘውዱ እንደገለጹትም፣ ትራንስ ኢትዮጵያ ቢዝነሶቹን ከማስፋፋት በተጨማሪ፣ የኩባንያውን ሀብት በማሳደግ አኳያም በዕለቱ የተመረቀውን ሕንፃ በጨረታ ገዝቶ፣ ግንባታውን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃቱ አንዱ መገለጫው ነው፡፡

ስለጎማ አገልግሎት ማዕከሉ አቶ ተፈሪ ሲናገሩ፣ የዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ቁጥር እያገደ ከመምጣቱ አንፃር ማዕከሉ መቋቋሙ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የማዕከሉ ዋና ዋና ጥቅሞቹ ብለው የገለጹት በአገሪቱ ውስጥ ዘመናዊ የጎማ ማኔጅመንት ባህል እንዲዳብር፤ ከጎማ ጥራት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አደጋዎች ለመቀነስ፣ ለመቆጣጠርና የመንገድ ደኅንነትን ለማረጋገጥ አጋዥ መሆኑ ነው፡፡

ከዚህም ሌላ እንዲህ ዓይነት ማዕከል መቋቋሙ የጎማ አገልግሎትን ለማራዘምና ለጎማ የሚደረገውን ወጪ ለመቀነስ የሚያስችል ስለሚሆን ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ለዚህ ማዕከል ግንባታና ለማሽነሪዎቹ ግዥ ከአሥር ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገ ጠቅሰዋል፡፡

ትራንስ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለስካኒያ ምርት የኢትዮጵያና የጂቡቲ ወኪል በመሆን የስካኒያ አውቶብስ፣ የጭነት ተሽከርካሪዎችና ሞተሮችን በማስመጣት በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት የድርጅቱ ኃላፊዎች፣ አሁንም ኩባንያውን የማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡

ወ/ሮ አዜብም ትራንስ ኢትዮጵያ አሁን በያዘው ሥራ ብቻ የሚቆም ሳይሆን፣ ተጨማሪ ሥራዎችን እንደሚሠራ ገልጸዋል፡፡ አሁን ከሚያንቀሳቅሰው ግዙፍ ኢንቨስትመንት በበለጠ በትራንስፖርትና መሰል አገልግሎቶች ላይ ለመሰማራት ዝግጀቱን ስለማጠናቀቁም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ትራንስ ኢትዮጵያ በትዕምት ሥር ካሉ ግዙፍ ኩባንያዎች በየጊዜው ፈጣን የሆነ ዕድገት እያሳየ ነው በማለት የገለጹት ወ/ሮ አዜብ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከታታይ ፈጣን ዕድገት በማሳየት በአገሪቱ የትራንስፖርት ዘርፍ በአሠራርና በአደረጃጀቱ ውጤታማ በመሆን ከቀዳሚዎቹ አንዱ ሆኗል ብለዋል፡፡

ትራንስ ኢትዮጵያ ከትዕምት በውጤታማነቱ ቀዳሚ ተጠቃሽ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ አዜብ፣ ኩባንያው ጥንካሬውን ይዞ እንደሚቀጥል በመግለጽ ‹‹ትራንስ ወርቅ ኩባንያችን ነው፤›› በማለት ኩባንያው በዕድገት ላይ መሆን ለማሳየት ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ይዞት የተነሳው የ100 ሚሊዮን ብር ካፒታል አሁን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ምስክር ነው ብለዋል፡፡

ከፒሬሊ ጎማ ጋር ያለውን የንግድ ትስስር በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡት ወ/ሮ አዜብ፣ ሁለቱ ኩባያዎች በአሁኑ ወቅት ካላቸው የቢዝነስ ግንኙነት የበለጠ ለመሥራት መታቀዱንና ይህም ጎማ ማምረቻ መገንባትን እንደሚያካትት ጠቁመዋል፡፡

ዳዊት ታዬ