ትላንትና በመንግስት ሴራ የከፈልነው ዋጋ ዛሬ መደገም የለበትም፡፡

ትላንትና በመንግስት ሴራ የከፈልነው ዋጋ ዛሬ መደገም የለበትም፡፡
‘ሪፈረንደም ይካሄድልን’ እያልን መንግስት ዝም ባለው 153 ንጹኃን እህት ወንድሞቻችን ሞተውብናል፣ በርካቶች ተሰደዋል፣ በሺ የምቆጠሩ ታስረዋል፤ ዛሬም ”የስልጣን ርክክቡ ይደረግልን” ፣ “ወንድሞቻችን ይፈቱልን” ስንል የሲዳማ አስተዳዳርዎች ከሌሎች ፀረ ሲዳማ የመንግስት መዋቅር አካላት ጋር ተመሳጥረው ህዝቡን እየዋሹ ዝም ያሉት፣ ለሌላ ነገር ሳይሆን አሁንም መልክ ቀይረው ህዝባችንን ዋጋ ለማስከፈል እንደሆነ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡

የስልጣን ርክክቡ ይደረግልን
ወንድሞቻችን ይፈቱልን፡፡

Netsanet Burka


መከራችን እንደቀጠለ ነዉ

የጎንደር አዘዞ ሙስሊሞችእራሳቸውን ፋኖብለው በሚጠሩ በአክራሪ አማራ ወጣቶች ምክንያት ሱቆቻቸው መቃጠሉ ታወቀ።

©ሙጂብ አሚኖ ዘ ኢስላም

ቅዳሜ ጥር 23/2012 ዓ.ል
🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸🕸

ጎንደር አዘዞ ላይ ህዳር 30/03/2012 ለሊት እራሳቸውን ፋኖ ብለው የሚጠሩ የአማራ ወጣቶች ሶስት የተለያዩ ወፍጮ ቤቶችና በውስጡ የሚገኙ 17 ቋት ሙፍጫዎች፣ መጋዘኖች፣ የተለያዩ ንብረቶችን መቃጠላቸውን ጨምሮ የቤት እንሰሳትም ተዘርፈዋል።

በአማራ ክልል የሙስሊም ጠል የድሮውን ሥርአት እንመልሳለን በሚሉ የጎበዝ አለቆች ፣ፋኖዋችና ሽፍቶች እንቅስቃሴ አገሪቱን ስጋት ውስጥ የከተተ ሲሆን ባለፉት ጊዜያት ብቻ በክልሉ የሕግ የበላይነት አዘቅጥ ውስጥ በመግባቱ 21 መሳጂዶች መማገዳቸው ይታወሳል። በቅርቡም ታህሳስ 10/ 2012 በአማራ ክልል ሞጣ በአንድ ጀንበር 4 መስጂዶች መውደማቸው፣ ከ300 በላይ ሱቆች እምነታቸው እየተለየ መዘረፋቸውና መቃጠላቸው ይታወቃል።

የክልሉ መንግስት ሽብርተኞቹን ለሕግ ከማቅረብ ይልቅ ከሽብርተኞች ጋር ወግኖ በመቆሙ በጎንደር አዘዞ በርካታ የሙስሊም ሱቆች እምነታቸው ተለይቶ ተማግዶ አድሯል።

በጎንደር አዘዞ ደብረ ሰላም ሎዛ ማሪያም ጥምቀት በ 21 እየተከበረ አምሽቶ ከምሽቱ 2:00 ላይ ከታቦት ማረፊያዊ በ 30 ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የገበያ ቦታ ወጣቶች በኃይል በመግባት ንብረቶችን አውድመዋል።

በገበያ ማዕከሉ ካሉ በርካታ ሱቆች መካከል 17 የልብስና የቤት እቃዎች የሚሸጡባቸው የሙስሊም መደብሮችና ምግብ ቤቶች ተለይተው በአክራሪ ወጣቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል።

በአጠቃላይ 21 ሱቆች ሲማገዱ በሙስሊም ሱቆች መካከል ከሙስሊሞች ተከራይተው የሚሰሩበት 4 የሌላ እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ሱቆችም ተቃጥለዋል።

በእለቱ የአዘዞ ፖሊስ ጥቃት ለማድረስ ያቀደ ኃይል እንዳለ በገበያው ቦታ በመገኘት ሱቆቻችሁን በጊዜ ዝጉ ሲል ስጋቱን ለማስመሰል ቢገልፅም ምሽት ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ማዳንና ከለላ ሰጥቶ መጠበቅ አልቻለም። የሱቁ በርካታ ባለቤቶችም ወደመኖሪያቸው ያቀኑበት ሰዓት በመሆኑ ንብረቶቻቸውን መከላከል አልቻሉም።

ከጎንደር ከተማ 13 ኪ.ሜ ላይ ወደምትገኘው አዘዞ ለበዓሉ በርካታ ወጣቶች ከተለያዩ ከተሞች መሔዳቸውን ለማወቅ ተችሏል

በቀጣይም የሱቆችን ዝርዝርና ባለቤቴቻቸውን እንገልፃለን።


KMN:- February 01/2020 #ጨለቂ
በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ስለ ህብር ብሔራዊ ፌድራሊስት ላይ ለመወያየት “February 08/2020” በሀገር አሜሪካ ስለተጠራዉ የፌድራሊስቶች ስብሰባ የተደርግ ዉይይት::


በምርጫና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ