ታላቅ ምስጋና ለአዳማ ከተማ ነዋሪዎችና ለአዳማ ከነማ ደጋፊዎች

ታላቅ ምስጋና ለአዳማ ከተማ ነዋሪዎችና ለአዳማ ከነማ ደጋፊዎች 

አዳማ አዳማ አዳማ የፍቅር ከተማ ፡ የአፄዎቹ ደጋፊዎች አደማ ሲገቡ በአይነቱ ለየት ያለ እጅግ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ፡፡ ደጋፊዎች ያዩትን ማመን አልቻሉም የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ቅ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው ጉዞ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበት የደጋፊዎች ጉዞ 2 አውቶቦስ 9 ዶልፊን 15 የቤት መኪና በአንድ ላይ በመጓዝ አዳማ ከተማ 5:30 ስንደር ” ፋሲል ኬኛ ” ብለው የኦሮሞን ባህል በሚያንፀባርቅ መልኩ ፡ በሞተረኛ ፖሊሶች ታጅበን ፣ እንደ ባለስልጣናት መንገድ ተዘግቶልን ፣ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው በድምቀት አንድነታቸውን ፍቅራቸውን ለገሱን ፡፡ ባለዕዳችሁ ነን ውለታችሁን መቼም ከፍለን አንጨርሰውም ፡፡ በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ ደጋፊ ለደጋፊ የተደረገ ደማቅ አቀባበል ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም በቦታው የታደመ መመስከር ይችላል፡፡
በድጋሚ ለአዳማዎች ላቅ ያለ ምስጋና በፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ስም እንዲሁም በደጋፊዎቻችን ስም ለማቅረብ እንወዳለን፡፡

Via: Fasil Kenema Football Club