ተከዜ ወንዝ ውስጥ የተገኙ 29 አስክሬኖችን በማስመልከት ሱዳን የኢትዮጵያን አምባሳደር መጥራቷ ተነገረ ።

ተከዜ ወንዝ ውስጥ የተገኙ 29 አስክሬኖችን በማስመልከት ሱዳን የኢትዮጵያን አምባሳደር መጥራቷ ተነገረ ።

KMN:- September 08/2021
 
ተከዜ ወንዝ ውስጥ የበርካታ ሰዎች አስክሬን መገኘቱን ተከትሎ ሱዳን በካርቱም የሚገኙትን የኢትዮጵያን አምባሳደርን ጠርታ ማናገሯ ተሰምቷል፡፡
ሬውተርስ የዜና ወኪል ሱዳን የኢትዮጵያን አምባሳደር ጠርታ ባነጋገረችበት ወቅት ለአምባሳደሩ በወንዝ ውስጥ የተገኙት 29 አስከሬኖች የትግራይ ተወላጆች ስለመሆናቸው አስረድታለች ሲል የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ጠቅሶ ዘግቧል።
ከሳምንታት በፊት በጥይት የተመቱ እና እጃቸው ወደኋላ የተጠፈሩ አስከሬኖች ወደ ሱዳን በሚፈሰው የተከዜ ወንዝ ውስጥ መገኘታቸው መነገሩ ይታወሳል።
 
በወቅቱ የአገሪቱ ፖሊስ በሱዳን ሰቲት በኢትዮጵያ ደግሞ ተከዜ ተብሎ በሚጠራው ወንዝ ውስጥ የ28 ሰዎች አስከሬን መውጣቱን አስታውቆ ነበር። ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የሰዎች አስክሬን በሱዳን በኩል ወንዝ ውስጥ የተገኘው ከሐምሌ 26 እና ነሐሴ 27 ባለው ጊዜ መካከል መሆኑን ለአምባሳደሩ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስከሬናቸው የተገኙ ሰዎች ሕይወታቸው በምን ምክንያት እንዳለፈ ያለው ነገር የለም።
አምባሳደሩ ጥሪ ተደርጎላቸው ስለጉዳይ እንዲያውቁ የተገደረገው ነሐሴ 24 መሆኑ ተመልክቷል።
የሱዳን የውጭ ጉዳይ መግለጫ የሰዎች አስክሬን የተለየው ምሥራቅ ሱዳን ዋድ አል ሁላዋህ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው ብላል።
በመንግሥት በኩል እስካሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ በይፋ ያለው ነገር የለም፡፡

KMN Kush Media Network


OMN: ዕለታዊ ዜና (Sep.8.2021)
OMN: ዕለታዊ ዜና (Sep.8.2021)