ቪኦኤ አሁን የዘገበው : የመድረክ መግለጫ- በትግራይ ምንም እስረኛ አለመለቀቁ -የሽግግር መንግስት

ቪኦኤ አሁን የዘገበው : የመድረክ መግለጫ- በትግራይ ምንም እስረኛ አለመለቀቁ –የሽግግር መንግስት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደባ እየተፈጸመ ስለሆነ ከጎኔ ሁኑ እያሉ ነው
===================================
ዶክተር ዐቢይ በግልጽ እኔ ከተሾምኩ በኋላ የኢኮኖሚ ሸፍጥና ቅጥፈቶች እየተፈጸመብኝ ነው። እባካችሁ እርዱኝ እያሉ ነው። አምስተኛው (ስውሩ) የሌቦች መንግሥት ገመድ ጉተታውን ጀምሯል።
“ወንጀለኛን ለቆ ንጹሐንን ማሰር በፍትሕ ላይ የሚፈጸም ሌብነት ነው” ብለዋል:: እነ ገብረዋህድን እሳቸው አልፈቱም ማለት ነው? ይህ ንግግር ህወሓቶች “ኮለኔል ደመቀ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ከተፈቱ ገብረዋህድ፣ ነጋ ገብረእግዚአብሔርን የመሰሉ ሌቦቻችችንን ይፈቱልን” ብለዋል መባሉን ያረጋግጥ ይሆን? ያው የፖለቲካ እስረኛ የሌለው ዘራፊዬ ይፈታልኝ ከማለት ሌላ ምን አማራጭ አለው?

የኤርትራ ጉዳይ ስላምም ጦርነትም የሌለው ሳይሆን ሞት አልባ ጦርነት ነበር። በጦርነት ተጠንቀቅ ውስጥ ሆኖ በስጋት መኖር ብዙ ኪሳራ ማድረሱን ገልጸው ሠላም መፍጠሩ ከአስመራ አዲሳባ ክፍት አድርጎ በጋራ ጥቅም ላይ መስራት እንደሚበጅ በመገንዘብ ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ከውሳኔ መድረሳቸውን አስረድተዋል
Kassa Yilma