“ብልፅግና ፓርቲ” የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርብ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ

“ብልፅግና ፓርቲ” የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርብ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ
የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ3ኛ ቀን ውሎ ብልፅግና ፓርቲ የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤቱ እንዲቀርብ የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ከስምምነት ላይ መድረሱን የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ አስታውቀዋል፡፡

የፓርቲው የስራ ቋንቋን በተመለከተም አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሱማልኛ፣ ትግርኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች ለስራ ቋንቋነት የተመረጡ ሲሆን ፓርቲው በአገሪቱ ለሚገኙ ቋንቋዎች በሙሉ እውቅና መስጠቱም ተገልጿል፡፡

ፓርቲው በፕሬዝዳንት እና በምክትል ፕሬዝዳንቶች ይመራልም ተብሏል፡፡ በክልሎችም የክልል ስያሜዎችን እንደያዘ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ይኖራል ተብሏል፡፡

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ3ኛው ቀን ውሎው በፓርቲው ረቂቅ ህገደንብ ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የውሳኔ ሀሳቦቹ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርቡ መስኗል፡፡

በናትናኤል ፀጋዬ

የፓርቲ ስብሰባ፣ በመንግሥት ቢሮ። እንዲህ ነው የ”ሰለጠነ” እና የ”ዘመነ” ፖለቲካ! — feeling delighted.

Tsegaye Ararssa is feeling delighted.