ብልጥግና ወንጀለኛ ድርጅት፣ አብይም ገዳይ አምባገነን ነው! ፌደራሊስት ነኝ በማለት ከተጠያቂነት አይድንም!

ብልጥግና ወንጀለኛ ድርጅት፣ አብይም ገዳይ አምባገነን ነው! ፌደራሊስት ነኝ በማለት ከተጠያቂነት አይድንም!

ብልጥግና ሰሞኑን ተሰብስባ ያስተለፈቻቸው ሁለት ውሳኔዎች አሉ። እነዚህም፣
1ኛ፣ እስከምርጫው ድረስ፣ ወደ እስር የሚጨመር እንጂ የሚፈታ አንድም እስረኛ አይኖርም፤ እና
2ኛ፣ በኦሮሚያ ውስጥ መዋቅር የነበራቸው የብአዴን/አዴፓ አደረጃጀትና የአልማ ተቋማት በሙሉ በኦሮሚያ ብልጥግና ሥር እንዲካተቱ፣
የሚሉ ናቸው።
 
በዚህም ውሳኔ መሠረት፣ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች፣ በተለይም በኦሮሚያና በደቡብ፣ ብልጥግናን የሚቃወሙ (ወይም የማይደግፉ) አደረጃጀቶች እና ማናቸውም ፖለቲካዊ ንቃትና ተሳትፎ ያላቸው ግለሰቦች እንዲያዙና እንዲታሰሩ ተወስኗል። በዚህም መሠረት የመያዝና የማሰር እርምጃው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በኦሮሚያ የሚገኙት የብአዴንና የአልማ አደረጃጀቶች ወደ ኦሮሚያ ብልጥግና መቀላቀላቸውም፣ ቡድኑ እራሱን ወደ ኢሠፓነት የመቀየር እርምጃውን በማስፋት ላይ እንደሆነ ግልጽ አድርጓል። ይህንን በማድረግም የኦሮሚያ ብልጥግና ከአማራ አቻው ጋር ወደ ሽኩቻ የገባ በማስመሰል፣ የኦሮሞን ሕዝብ ቀልብ ለመሳብ ሙከራ እየተደረገ መሆኑን የካድሬዎቸው የየድረ-ገጹ ጫጫታ ያሳያል።
 
እነዚህ ካድሬዎች፣ የአብይ አህመድ ቡድን በኦሮሚያ ውስጥ የተተፋ መሆኑን በመገንዘብ፣ የኦሮሞን ቀልብ ለመሳብ ሲሉ ብቻ፣ ደርሰው ፌደራሊስትና የብሔሮች መብት ጠበቃ እንደሆኑ ለማሳየት እየጣሩ መገኘታቸውም፣ ከላይ ለመተግበር የወሰኑትን የኢሠፓ ዓይነት የተማከለ አሃዳዊነትን የመመሥረት ዓላማ፣ የፌደራሊስት ጭንብል (mask) ለማልበስ የሚንቀሳቀሱበት ስልት መሆኑን ከውስጥ የደረሱን ምንጮች ገልጸዋል።
በመሆኑም፣ አብይ አህመድ ‘እስረኞች ይፈታልናል’ ብለው ተስፋ ያደረጉም ሆነ ከአብይ “ምህረት” እናገኛለን ብለው ድርድር ጀምረው የነበሩ ሁሉ እርማቸውን አውጥተው፣ በጽናት ቢታገሉ ይሻላል። ሕዝቡም መጠንቀቅ ያለበት፣ አብይ ተስፋ ከቆረጠ እስረኞቹን ከማጥፋት ወደ ኋላ ስለማይል፣ እስረኞቹን ከግድያ ለመጠበቅ ነገሮችን በንቃት እንዲከታተል ነው።
 
የኦሮሚያ ብልጥግና ‘ፌደራሊስት ሆነች’ እንዲሉ ዋና ዋና ተከፋይ ካድሬዎችን አሰማርቶ የኦሮሞን ሕዝብ ለማማለል እየሠራ ያለውም ይሄው ወንጀለኛው የአብይ ቡድን መሆኑን ተረድቶ፣ የእነሱን ወሬ (እና ‘የውስጥ ግጭት አላቸው’ የሚል ሃሜት) ማራገብ ትቶ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለመብቱ በመቆም ግዴታውን ሊወጣ ይገባል።
 
የአብይ ቡድን ገዳይ ነው። የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀል፣ እና በሰብአዊነት ላይ የተደረገ ወንጀል የፈጸመ ደመኛ የሕዝቦች ጠላት ነው። ከዚህ ቡድን ጋር የሚደረግ ድርድርና ውይይት፣ ምርጫ፣ ወይም የሚደራጅ የ(ፌደራል)አስተደር ሥርዓት የለም፤ አይኖርምም።
ይሄን ቡድን ለፍትህ ማቅረብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ (እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሁሉ) የትግል ክፍል ነው።
 
(Dr. Tsegaye R Ararssa)