ብሄራዊ ምርጫና በኢፌዴሪ ያለውን ቀውስ በተመለከተ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

ብሄራዊ ምርጫና በኢፌዴሪ ያለውን ቀውስ በተመለከተ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር መግለጫ

[SBO – MUDDE 12,2020] የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በፍትሃዊና ነጻ ምርጫና ሁሉን ያሳተፈ ዲሞክራዊያዊ የኢፌዴሪ መንግስት መመስረት ያምናል። ሃገሪቱን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ 6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ እአአ በ2021(2013ዓም) ለማካሄድ በማቀድ ላይ መሆኑን እያየን ነው። የሃገሪቷን ፖለቲካዊ ችግሮች በመፍታቱ ገንቢ ሚና የሚጫወት ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ሰላምና ደህንነት መረጋገጥና የፖልርቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለን እናምናለን። ይሁን እንጂ የኢፌዴሪ በቀውስ በተዘፈቀበት በኣሁኑ ወቅት ምርጫ ለማካሄድ ማቀድ ለይስሙላ ካልሆነ በስተቀር እውነተኛ ኣይመስልም። ሃገሪቷን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ ያሉ ችግሮችን ደብቆ ትኩረቱን ወደ ብሄራዊ ምርጫ ለመመለስ ቢጥርም፡ ሃገሪቷ እጅግ ኣስከፊ የደህንነትና የፖለቲና ምስቅልቅል ውስጥ ተዘፍቃለች።
 
ላለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ኦነግና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ሲተነብዩና ጊዜው ሳያልፍበት ከመሰረቱ መፍትሄ እንዲበጅለት ሃገሪቷን እያስተዳደረ ላለው ፓርቲ ሲጠቁሙ ቆይተዋል። ህግና ስርዓት ተከብሮ በዲሞክራሲያዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ ሁሉም እኩል እንዲጠቀም ድጋፋችንን ስናበረክትም ነበር። ይሁን እንጂ ሃገሪቷን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ ያቀረብነውን ሃሳብ ወደ ጎን መተው ብቻም ሳይሆም፡ በደህንነት መዋቅሩ ተጠቅሞ ድርጅታችንና በመላው ሃገሪቷ ውስጥ የምናደርገውን እንቅስቃሴ በማደናቀፉ ላይ ተሰማራ። ኣሁንም በሃገሪቷ ውስጥ መፍትሄ ያልተበጀለት ትልቅ የፖቲካ ችግር ኣለ።
 
ከዚህም ውጪ የህገ-መንግስት ቀውስና የዜጎች ችግሮችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረቧቸው ጥያቄዎች በኢፌዴሪ ህገ-መንግስትና ህጉ ላይ በተቀመጠው መሰረት ምላሽ ኣልተሰጠውም። የሃገሪቷ የፍትህ ስርዓት ነጻ ሆነ ስራውን ማከናወን ኣልቻለም፣ የደህንነት መዋቅር፣ ፖሊስና ሌሎች የታጠቁ ሃይሎች ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሃገሪቷን በማስተዳደር ላይ መሆናቸው ግልጽ ነው። እንደኦሮሚያ ያሉ የክልል መስተዳድሮች በወታደራዊ ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ ስር መኖራቸውና የሲቪል ኣስተዳደር መዋቅሩ መፈራረስ በገሃድ የሚታይ እውነታ ነው።
 
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በምርጫው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ቢሆንም፡ ኣሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ በምርጫው እጩዎችና ታዛቢዎች መሆን የሚችሉ ኣባሎቻችን፣ ኣመራሮቻችንና ደጋፊዎቻችን በሁሉም ደረጃ በእስር ላይ ባሉበትን በምርጫ መሳተፍ ኣይቻልም።
ከዚህም ሌላ ፊንፊኔ የሚገኘውን ዋናውን ጽ/ቤታችንን ጨምሮ በመላው ሃገሪቷ ያሉ የኦነግ ጽ/ቤቶች ሁሉም ሃገሪቷን እያስተዳደረ ባለው ፓርቲ የደህንነት መዋቅር ተዘርፈዋል፣ ተዘግተዋል፣ እንዲሁም በቁጥጥር ስር ይገኛሉ።
 
የታሰሩትን ኣባሎቻችንና የተዘጉ ጽ/ቤቶቻችንን ስም ዝርዝር ለኢፌዴሪ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በተደጋጋሚ ምናስገባም እስከ ኣሁን ለኣቤቱታችን ኣንዳችም ተጨባጭ ምላሽ ሳናገኝ ኣነሆ ኣራት ወራት ሆነ። ይህም የምርጫ ቦርድን ችሎታና ብቃት እንዲሁም ውሳኔዎችን የማስተላልፈና ገለልተኛ ሆኖ መስራቱን ከጥያቄ ያስገባ ነው። በመላው ሃገሪቱ ውስጥ እሁንም ኣባሎቻችንና ደጋፊዎቻችንን እንዲሁም ለኦነግ በጎ ኣመለካከት ያላቸውን ዜጎች ማደን፣ ማሰርና መግደሉ ቀጥሏል። በቀጣይነት እየተፈጸመ ካለው ከዚህ የከፋ ወንጀልና በኣካል ከሚደርስባቸው ጫናና ሰቆቃ የተነሳ የኦሮሚያ ዜጎች ወጥተው የሚያስተዳደራቸው መምረጥ ቀርቶ ነጻ ሆነው መናገር እንኳ ኣልቻሉም።
 
በኦሮሚያ ውስጥ ያሉ ግጭቶች ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ እንደነበር የሚታወቅ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ኣሳሳቢ ወደ ሆነ ደረጃ ኣሻቅቧል። የተቃውሞ ሰልፍ፣ ቀውሶና ግጭቶች በየቦታው ይስተዋላል። የህዝቡ ከቀዬው መፈናቀልና ሰብዓዊ ቀውስ ኦሮሚያን ኣለመረጋጋት ከማሳጣቱም ኣልፎ ጎረቤት ሃገራትንም በማወክ ላይ ይገኛል። በኣሁኑ ወቅት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ግጭትም ለዜጎች መፈናቀል ያበረከተው ኣስተዋጽዖ ኣለው። ሶስተኛ ኣካላት ውስብስቡች ሁኔታ ይበልጥ እንዲባባስ ከማድረጋቸውም በተጨማሪ በኣሁኑ ወቅት በሃገሪቷ ያለው የፖለቲካ ችግሮችና የደህንነት ቀውስ ኣስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።
 
ስለሆነም ኣብይ ጉዳይ ወዳልሆነው ምርጫ ከማምራት ይልቅ ሃገሪቷን እያናጋት ያለውን የፖለቲካ ችግር ሁሉን ባሳተፈ ሰላማዊ ውይይት መፍታቱ ቅድሚያ ማግኘት ይገባዋል ብለን እናምናለን። ላለፉት 27 ዓመታት የሃገሪቷን የፖለቲካ ስርዓት ወደ ባሰ ኣስከፊ ሁኔታ ያመራ የይስሙላ ምርጫዎችን ስናስተናግድ ዛሬን ደርሰናል። እንደኦነግ እምነት፡ ተመሳሳይ ስህተት መፈጸም የበለጠ ትርምስ በመፍጠር ሃገሪቷንና ጎረቤቶቿን ለኣስከፊ ኣደጋ ያጋልጣል።
 
የክልል መስተዳደሮች መዋቅር መስተካከልና ሰላማ ደህንነትን ማረጋገጥ ሊካሄድ ከታሰበው ምርጫ ኣስቀድሞ ሊተገበር ይገባዋል ብለን እናምናለን። በኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች እጅግ ኣሳሳቢ ሁኔታ በመባባስ ላይ ይገኛል። ሃገሪቷን በሃይል እየገዛ ያለው ፓርቲ ችግሮችን በታጠቁ ሃይሎችና ህዝቡን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር በማስገባት ለመፍታት ጥረት በማድረግ ላይ ነው። በሌላ በኩል ዶር. ኣብይ ኣህመድ ሰሞኑን ታህሳስ 10, 2020ዓም በኬኒያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት በሞየሌ ከተማ በሰጡት ኣስተያየት ያለንን ስጋት እንገልጻለን።
 
የኦሮሚያን ብሄራዊ የሽግግር መንግስትን በግንባር ቀደምትነት እየመሰረተ ያለውን ኦነግን ከቀጠናው ስለማጥፋት ተናገረ፣ ለዚህም የኬኒያ መንግስት እንዲረዳው ጥየቀ። ይህ ሌላ ሃገሪቷን ከሃይል እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ የሚያደርገው ከፍተኛ ኣደጋ ያለው እንቅስቃሴና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ኣጥፍቶ ምርጫውን ለብቻው ተወዳድሮ ለማሸነፍ ላለፍ ፍላጎት በቂ ማስረጃ ነው። የኬኒያ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ለነጻነቱ የሚያደርገውን ትግል በምንም መልኩ በማደናቁፉ እጁን እንዳያስገባና ድንበር የሚጋራውንና ለዘመናት ኣብሮ ከኖረው የኦሮሞ ህዝብ ጋር ግጭት ውስጥ እንዳይገባ እናሳስባለን።
 
በመጨረሻም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች መፈታት፣ የኦሮሚያ ክልል መስተዳድር መታደስና ብሄራዊ የኦሮሚያ የሽግግር መንግስት መቋቋም፡ እንዲሁም በኣፍሪካ ህብረት ካስቀመጠው ጋአ በሚጣጣም ሁኔታ ሁሉንም ኣካላት ያሳተፈ ውይይት እንዲካሄድና ከብሄራዊ መግባባት እንዲደረስ ሁኔታዎች መመቻቸት ኣለባቸው ብሎ ያምናል። ሁሉን ኣቀፍ ውይይቱን እውን ለማድረግና ከስምምነት ተደርሶ የሚካሄድን ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ ድርሻችንን ለማበርከት ዝግጁ በሆናችንን በድጋሚ እናረጋግጣለን።
 
ድል ለሰፊው ህዝብ1
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ፊንፊኔ
ታህሳስ 12, 2020ዓም
Ibsa Adda Bilisummaa Oromoo