ባህርዳር-በወታደሮች ክፉኛ የተደበደቡ የባህርዳር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል በመታከም ላይ ይገኛሉ።

ባህርዳር-በወታደሮች ክፉኛ የተደበደቡ የባህርዳር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል በመታከም ላይ ይገኛሉ።

መረጃ#ESAT
ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ተቃውሞው ቀጥሎአል
ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓትተኩል የባህር ዳር ዋናው ግቢ የሚሰሩ የዩኒቨርስቲው መምህራንና ሰራተኞች ሙሉ በሙሉ ግቢውን እንዲለቁ ታዘው ወጥተዋል፡፡በየግቢዎች ያሉትን የተማሪ ተወካዮች በመሰብሰብ የክልሉ ባለስልጣናት እያነጋገሩ ነው፡፡በሁሉም የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ግቢዎች የመማር ማስተማር ሂደቱ ተቋርጧል፡፡
በዋናው ግቢ(ፔዳ) መግቢያ በር ላይ የአድማ ብተና አለባበስ የለበሱ በርካታ ወታደሮች ይገኛሉ፡፡በግቢ ውስጥ ያሉ ተማሪዎችም እስካሁን የተቃውሞ ድምጻቸውን እያሰሙ ነው፡፡በርካታ የፌደራል ወታደሮችም ግቢውን ሞልተው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ተማሪዎች በምኝታ ቤቶች አካባቢ የሚያልፉት ወታደሮች ላይ ውሃ በመድፋት ተቃውሟቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከምሽቱ አራት ሰዓት የአጋዚ ወታደሮች በመግባት ጥቃት ሲያደርሱ አድረዋል፡፡በይባብ ካምፓስ አራት ተማሪዎች በአጋዚ ወታደሮች ከፎቅ ተወርውረው በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ክትትል ሲደረግላቸው አድሯል፡፡በተለይ አንድ ተማሪ(ከደቡብ ክልል የመጣ) በከፍተኛ ደረጃ በመጎዳቱ ራሱን ስቶ እንደ ነበር በሆስፒታሉ በእለቱ ተረኛ ከነበሩ ሃኪሞች መረዳት ተችሏል፡፡