ቢልሌ (መህቡባ):-ወላጆቿ ያወጡላት ስሟ “ቢልሌ” ሲሆን በምእራብ ኦሮሚያ ጉማ በተባለ አከባቢ በ1820 ተወለደች።

…………ቢልሌ (መህቡባ)….……….
.via Gumaa sinqe
.
ወላጆቿ ያወጡላት ስሟ “ቢልሌ” ሲሆን በምእራብ ኦሮሚያ ጉማ በተባለ አከባቢ በ1820 ተወለደች።
.
ቢልሌ ገና እድሜዋ በአስራዎቹ አጋማሽ እንደደረሰች በ1835/36 በትውልድ መንደሯ ላይ ወራሪዎች በመግባት መንደራቸው ላይ ጦርነት ከፍተው አባቷ እና ስድስት ወንድሞቿ በጦርነቱ ላይ ሲገደሉ እርሷ እና አህቷ ደግሞ በወራሪዎች እጅ ወድቀው በባሪያ ፈንጋዮች ወደ ጎንደር ተወሰዱ።
.
ጎንደር ላይ ቢልሌ እህቷን ዳግም ላታያት ሲለያዩዋቸው ቢልሌን ከጎንደር ወደ ካርቱም( ሱዳን) ቀጥሎም ወደ ግብጽ (ካይሮ) በ1837 በባሪያ ነጋዴዎች ቅብብሎሽ ደረሰች።
.
በዚህን ሰአት ነበር አንድ ስሙ ሀርማን ፓርላክ የሚባል የጀርመን ልኡል(የንጉስ ልጅ) የምስራቅ ሀገሮችን እየጎበኘ ሳለ ካይሮ የደረሰው።
ይህ እለት ደግሞ ያልታደለችው ትውልደ ኦሮሞዋ ቢልሌ እንደ ሸቀጥ ልትሸጥ ለገበያ የቀረበችበት መአልት ናት።
.
ጀርመናዊው ልኡል ድንገት ፊቷ ላይ ፍርሀት የተሞላባትን ጠይም ቆኖጆ ልጅ አይቶ በድንጋጤ ባለበት የቆመዉ።
.
በወቅቱ ከቁንጅናዋ ይልቅ በማታውቃቸውና የቆዳ ቀለማቸው ጭምር ከርሷ ለየት ባሉ ሰዎች የተከበበችውን ልጅ በጁ ሊያስገባት በማሰብ የተጠየቀውን ገንዘብ ከፍሎ ከባሪያ መነገጃው ገበያ ይዟት ወጣ።
.
ቢልሌ በወቅቱ እድሜዋ ትንሽ ቢሆንም አሰተሳሰቧ እና ውበቷ በሂደት የማረከው የጀርመን ልኡል “መህቡባ” በማለት ስም አወጣላት።
“መህቡባ” በአረብኛ ትርጉሙ “ፍቅሬ” ማለት ነው። በቢልሌ ፍቅር የተማረከው ልኡል ፓርላክ ጉብኝቱን ወደ ሌሎች ሀገሮች ሲቀጥል ቢልሌ (መህቡባ) ከጎኑ አንድትለይ አላደረገም። ልኡል ፓርላክ ወደ ወደ ሀገሩ ጀርመን መልእክት ለባለቤቱ ሲጽፍ የቢልሌንም ጉዳይ ከማንሳት አልተቆጠበም “በቢልሌ ፍቅር መነደፉን፣እርሷም እንደወደደችው፣ ፈጽሞ ሊለያትም እንደማይችል ጭምር በተለያዩ ደብዳቤዎች ላይ ለልጆቹ እናት ይጽፍላት ነበር።

ልኡሉ ቀድሞ የነበረበትን የተለየ ባህሪ ተቀይሮ መልካም ነገሮችን ብቻ ማሰብ ሲጀምር “እውነት አብራት ካለች ሰው ጋር ዉዬ ከረጅም ግዜ ቦሀላ እውነተኛ ሰው ሆንኩ” በማለት ስለ ራሱ በግላጭ ተናገረ። በ1840 ልኡል ፓርላክ እና መሀቡባ (ቢልሌ) ወደ አውሮፓ ያመሩ ሲሆን ቢልሌ በሳንባ ህመም ተያዘች። ልኡል ፓርላክ ሙስካት ምትባል ከተማ ላይ ቢልሌን አስወምጦ ድንገት ታመመች የተባለችው ባለቤቱን ለማየት ወደ በርሊን በሄደበት ወቅት በብቸኝነት እየተብሰከሰከች ሳለ ድንገት አንድ በመልክ ቀለም እሷን መሳይ ወጣት ተመለከተች። በእርግጥም በባሪያ ፈንጋዮች አመካይነት ተሸጦ አሁን ነጻ የወጣውን ኦሹ አጋን ነበር ያገኘችው።
በኦሹ አጋ አመካይነት ደግሞ ጀርመናዊውን ምሁርና በአፋን ኦሮሞ ላይ ብዙ ጠናት ያደረገውን ካርል ቱትሼይክ ጋር ተዋወቀች።
.
ጀርመናዊው ካርል ቢልሌ በኦሮምኛ የምትጽፋቸውንና ዘፈኗን ጭምር በጽሁፍ ሰንዶ ያስቀምጥ ነበር።
.
ድንገት ግን ቢልሌ ህመሟ እየጸናባት ሲመጣ ለፓርላክ ደብዳቤ ለመጻፍ እንኳን የማትችልበት ደረጃ ላይ ስለደረሰች ዶክተሯ ደብዳቤውን ጽፎላት ላከችለት።
.
ፓርላክ የመህቡባ ደብዳቤ ቢደርሰውም በሞት አፋፍ ላይ ያለች ሚስቱን ትቶ ለመሄድ አቅም ስላጣ የደረሰበትን ችግር የሚገልጽ ደብዳቤ እና “መህቡባ” የምትል የብር ሀብል ላከላት።
.
ለመህቡባ የተላከው ደብዳቤ እና ሀብል ጥቅምት 27/1840 መህቡባ ካለችበት ሙስካ ሲደርስ ግን ያቺ ከወገን እናት ምድሯ እንዳትገናኝ የሆነችው ቢልሌ ልታየው አልታደለችም ነበር።