በፍሊፕ ሶቅራጠስ: አማራ ንቃ! … ካለፈውንም ተማር:

በፍሊፕ ሶቅራጠስ
አማራ ንቃ! … ካለፈውንም ተማር
~~~~~~~~~~~~~~~
“አማራው በሙሉ አቅሙ ተነሳስቶ ጦርነት ውስጥ ገብቶ ያድነናል” በሚል አቅደው በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ አማራዎችን በግፍ የረሸኗቸው ብልፅግና ነን ባይ ተስፈኞች ናቸው! አማራ ሆይ ሰከን በል! የተደገሰልህን አላውቅህም! ከመታረድህ በፊት ንቃ!
~~~
ለዚህ ፍሪዳነትህ ደላላዎቹና አሳራጆችህ ደግሞ “የአማራ አክቲቪስት ነን” ባይ ከርሳሞችና እምቦቀቅላዎች ናቸው። ሚዲያ ላይ የሚያሽቃብጡት ጋዜጠኞችም ዋናዎቹ ናቸው።
~~~
ከልቤ ነው ምመክራችሁ! አማራዎች ከተሸፈናችሁበት የእንቅልፍ ብርድ ልብስ ውጡ! አሁን ላይ ጅቡ ብልፅግና እግራችሁን እየበላ ነው። ሳይጨርሳችሁ ንቁ! ነገ “የበለጠ እናንተን አስቆጥቶ ለማነሳሳት” በሚል ሌላ ድግስ ደግሶላችኋል። ሻሼመኔ፡ መተከል፡ ጉራፈርዳ፡ ወለጋ፡ ይቀጥላል! ምናልባትም ቀጣዩ አዲስ አበባ ሊሆን ይችላል! ማን ያውቃል? መንቃት ጥሩ ነው።


ትግራይ ከእነ ስብሃት ነጋ የጎጥና ቤተሰባዊ የህወሃት የማፍያ ቡድን የ44 አመታት ቅኝ ግዛትና ምዝበራ ነጻ ትወጣለች። ባዶ ስድስት ውስጥ ከምድር በታች ታስረው ብርሃን አይተው የማያውቁ ግፉአን ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ብርሃን ያያሉ።
የትግራይ ህዝብም የታሰረበት ሰንሰለት ሲፈታለት የደስታ እንባ እያነባ ነጻነቱን ያውጃል። መልሶ ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር እንባ እየተራጨ ይቀልቀላል። እኛም በኩራት ወገን ለመጠየቅና አክሱም ማርያምን ለመሳለም ወደዛው እናቀናለን። በቅርቡ ይሄንን ሁሉ ተአምር እናያለን! Mark my word!

Be the first to comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*


This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.