Kichuu

በጎንደር በምሽት የሚሰሩ ባጃጆች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከሉ::

በጎንደር በምሽት የሚሰሩ ባጃጆች እንዳይንቀሳቀሱ ተከለከሉ::

ሚያዚያ 16 / 2009 ማታ ከምሽቱ 1፡40 ጎንደር ለ11 ኛ ጊዜ የቦምብ ጥቃት ተፈፅሟል ጎንደር ከተማ አጣጣሚ ሚካኤል ቤ/ክርስቲን ፊትለፊት ደሻቱ ሎጂ በሚባል የውጭ ሀገር ዜጎብ ብቻ በሚያዘወትሩት ቦታ ላይ ነው የቦንብ ጥቃቱ የተፈፀመው::

በዚህ ሎጅ ከውጭ ሀገር ዜጎች ውጭ ማንም የሀገር ውስጥ ዜጋ መግባት የማይችልበት ሲሆን በአብዛኛው ተጠቃሚዎቹ ተመመሳሳይ ፆታ ያላቸው ሲሆን አስተናጋጆቹም ቢሆኑ ወንዶች ብቻ እነደሁኑ ይታወቃል ይህን ከእምነትና ከባህል ውጭ ከሆነው ስራ እንዲሰተካከሉ ቢነገራቸውም ሊመለሱ ባመቻላቸው ጥቃቱ ሊፈፀምባቸው እንደቻለ የአካባቢው ሰዎች ሲናገሩ ይሰማል ፡፡

እስካሁን በጥቃቱ ሀላፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም መንግስት የከተሞች ፎረም አከብራለሁ በማለት እንግዶችን ለማስተናገድ ከፍተኛ ሽርጉድ እያደረገ ባለበት ሰዓት መሆኑ በበአሉ አከባር ላይ ከፈተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል.:

በጥቃቱ አንድ የውጭ ሀገር ዜጋ እና የሎጅው ዘበኛ የቆሰሉ ሲሆን የሞተ ሰው እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል ፡፡ ዛሬ ጠዋት ከሎጁ አርፈው የነበሩት በሙሉ ማታ ፍንዳታው ከደረሰ በኃላ ወደ ሌላ ሆቴል ወስደው ያሳረፏቸው ቢሆንም እግዶቹ ዛሬ ከተማውን ለቀው ወደ አዲስ አበባ ሊሄዱ ተገደዋል ከዚሁ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ድንጋጤ በ50 ሜትር እርቀት ካለው ፋሲል ሎጅ አርፈው የነበሩ ሌሎች የውጭ ሀገር ዜጎች አብርው ከተማውን የለቀቁ ሲሆን ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ የጥዋቱ በረራ ከፍተኛ መጨናነቅ ተፈጥሮበት በጠዋቱ በረራ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ ቲኬት ቆርጠው ለጉዞ የተዘጋጁ የሀገር ውስጥ ዜጎች ቅድሚያ ስጡ ተብለው በረራቸው የዘገየ መሆኑን ተጓዥ የነበሩ አስረድተውናል ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ይህ ጥቃት ከተፈፀመ ከሰዓታት በኃላ ከምሽቱ 4፡30 ጀምሮ ምን እንደሆነ ባልታወቀ ምክንያት በከተማው ከፍተኛ የጥይት ተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ያደረ ሲሆን ወታደር የጫኑ የፓትሮል መኪኖች በከፍኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ ማደራቸው ታውቋል ፡፡

Via: Natnael Mokonnen

Exit mobile version