በደብረ ማርቆስና አካባቢው የሞባይል አገልግሎት ከሶስት ቀን በላይ ተቋርጧል

በደብረ ማርቆስና አካባቢው የሞባይል አገልግሎት ከሶስት ቀን በላይ ተቋርጧል- ተገልጋዮች

በደብረ ማርቆስና አካባቢው

(FANABC) -አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደብረ ማርቆስና አካባቢው ከሶስት ቀን በላይ የተቋረጠው የሞባይል አገልግሎት አሁንም አለመጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ።

የኢትዮ ቴሌኮም የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሪክተር አቶ አብዱራሂም መሃመድ፥ ችግሩ በጄኔሬተር መቃጠልና በፈኖተ ሰላም እና ደብረ ማርቆስ መካከል የሚገኝ ፋይበር መስመር በመቋረጡ ምክንያት ችግሩ መከሰቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በአሁን ወቅት ችግሩን ለመቅረፍ አዲስ ጄኔሬተር በመተካትና የፋይበር መስመር ጥገና ተደርጎ ወደስራ እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል።

አቶ አብዱራሂም ይህን ይበሉ እንጂ ነዋሪዎቹ ዛሬም የስልኩ ጥሪን ተከትሎ ሲነሳ አገልግሎቱ እንደሚቋረጥ ነው ያመላከቱት።

በታሪክ አዱኛ