በወልቂጤ ከተማ ህዝብ ዛሬ ህዝባዊ አመፁን በይፋ ተቀላቀለ ከዚህ ቀደም በከተማው ወጣቶች ለመንግሥት የተሠጠ ማሥጠንቀቅያና ለዛሬው አመፅ መክንያት እነደሚከተለው ቀርቧል

በወልቂጤ ከተማ ህዝብ ዛሬ ህዝባዊ አመፁን በይፋ ተቀላቀለ ከዚህ ቀደም በከተማው ወጣቶች ለመንግሥት የተሠጠ ማሥጠንቀቅያና ለዛሬው አመፅ መክንያት እነደሚከተለው ቀርቧል

—– ሆስፒታላችንን መልሱ ——ይሄ ጥያቄ አደለም የህዝብ ትዛዝ ነው!!!ወልቂጤ ላይ ይሰራል የተባለው ሆስፒታል እና የምርምር ተቋም በፌደራል ባለስልጣናት ትዛዝ ጉራጌ ዞን ውስጥ እንዳይሰራ ትዛዝ ተላለፈ። ”በ2007 ዓም የካቲት ወር ላይ በጣልያን ሰብዐዊ መብት ድርጅት መስርራቾች ድጋፍ በአቶ ግረማ ወ/ጊዮርጊስ በኩል እድልሉ ተገኘ ወልቂጤ ከተማ ላይም ይሰራል ተብሎ የታሰበው በወቅቱም በጀቱ ሳይለቀቅ እንደተለቀቀ ተደርጎ ሲነገር የነበረው እና በዚያው አመት ተጀምሮ በሁለት አመት ውስጥ ተሰርቶ እንደሚጠናቀቅ እና አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ሲወራ የነበረው ሁሉ መና ሊቀር ነው። ”ነገሩ እንዲህ ነው ። በወቅቱ የፌደራል ፣የክልል ፣የከተማ ባለስልጣናት እና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ህዝብ በተገኘበት የቀድሞው የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ አማካኝነት መሰረተ ድንጋዩ ተጣለ። ነገርየውም ከራረመ ህዝቡም

ሆስፒታሉስ እያለ ይጠይቃል አስተዳዳሪዎቻችንም ሊሰራነው አንድ ሀሙስ ቀረው እያሉ ሲያታልሉ ከረሙ። በመጨረሻም አስተዳዳሪዎቻችን ሆስፒታሉን ብለው ለአቶ ግርማ ወጊዮርጊስ ጥያቄ አቀረቡ ሰውየውም እኔ ምንም ማድረግ አልችልም ወደናተ አካባቢ እንዳይሰራ የፌደራልሉ ባለስልጣናት አዘዋል አሉ። አሁንም በድጋሚ አስተዳዳሪዎቻችን ለፌደራሉ ባለስልጣናት አቤት አሉ መልሳቸውም ወደሌላ አካባቢ ተዛውሯል የሚል ነበር ፤ አስተዳዳሪዎቻችን ለምንአላሉም ፤ ሎሌም አደሉ (አድር–ባይ) መተው የተጣለውን መሰረተ ድንጋይ ግንበኛ ልከው እንዲፈርስ አደረጉት በቃ በአጀብ ፣በድግስ፣በሆታና በጭብጨባ የጣሉትን መሰረተ ድንጋይ በዝምታ በአንድ ግበኛ አፈረሱት።

”ይሄ ህዝብን መናቅ ነው! የወቅቱ የጉራጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ሽኩር እና አጋፋሪዎቻቸው ሆስፒታል እና የምርምር ተቋም ልንገነባልህ ነው ብለው ሰብስበው ጮቤ ያስረገጡትን ህዝብ፤ስራው ሳይሰራ በመዘግየቱ የህዝቡን ይቅርታ ጠይቀው ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር በፍጥነት ስራውን ማስጀመር አለባቸው። ”ይሄ ህዝብ የኢህአዴግ መንግስትን ጭቆና መሸከም አንገሽግሾታል፤ የህዝብ ፣የብሄር የዞን መጨረሻ መሆን በቅቶታል ቁጣው የገነፈለ ቀን ወየው ለናተ፤ የዚህ ጉዳይ ቁርሾ ህዝቡን ወደማይፈልገው መንገድ እንደሚመራው አትጠራጠሩ።”የዞኑ አስተዳደርም ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ ከሎሌነት ወጥቶ ከህዝቡ ጎን በመቆም የህዝብ እንደራሴነቱን ማሳየት አለበት። ”ህዝቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማስተባበያ ወይንም ውይይት ሳይሆን የሆስፒታሉ ስራ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ነው የሚፈልገው። ይሄንኳ እናተም ታውቃላችሁ።

”እንደ ዞን ርዕሰ ከተማ እና እንደ ህዝብ ብዛቱ የወልቂጤ ከተማ በመንግስት በጀት ተመድቦለት እስከዛሬ ቆሽማዳ ጤና ጣብያ እንጂ ሆስፒታል እንዳልተሰራለት ይታወቃል ስለዚህ በጀት ይዛቹ ባትሰሩለት የበጎ አድራጊዎችን ችሮታ አትንጠቁት፣አታስነጥቁት ዋ!”ወጣቱና የአካባቢው ህዝብም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የዚህን ሆስፒታል እና የልማት ጥያቄውን እንዲያነሳ ይሁን።#ሆስፒታል_ለወልቂጤ#በፍጥነት_የወልቂጤ_ሆስፒታል_ዝውውር_ይቁም#የፌደራል_መንግስት_የጭቆና_እጅህን_ከጉራጌ_ዞን_ላይ_አንሳ ዘርማ