በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ላይ ዝርፊያ ተፈጸመ

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ላይ ዝርፊያ ተፈጸመ

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ

(FBC)–አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 1 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተሳተፈ በሚገኘው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አባላት ላይ ዝርፊያ ተፈጽሟል።

ዝርፊያው ትናንት ምሽት ቡድኑ ባረፈበት ጎማን ታወር በተባለው ሆቴል ውስጥ ነው የተፈጸመው።

በወቅቱም በሆቴሉ የህንጻው 9ኛ ወለል ላይ በሚገኙ ሁለት የአትሌቶች ክፍል ላይ ዝርፊያው ተፈጽሟል።

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ከሁለት እህቶቿ ጋር ያረፈችበት ክፍልና ሴት የማራቶን ተወዳዳሪዎቹ ማሬ ዲባባና አሰለፈች መርጊያ ባረፉበት ክፍል ውስጥ ነበር ዝርፊያው የተፈጸመው።

በሆቴሉ የጽዳት ሰራተኞች ሳይፈጸም አልቀረም በተባለው ዝርፊያ፥ ከአትሌቶች ኪስ፣ ቦርሳ እና መሳቢያ ውስጥ ገንዘብ መጥፋቱን የስፖርት ዞን ባልደረባ ከስፍራው ዘግቧል።

አትሌት ጥሩነሽ የሆቴሉ የጽዳት ሰራተኞች ወደ ክፍላቸው በተደጋጋሚ በመምጣት እረፍት ይነሷቸው እንደነበር ከስፖርት ዞን ጋር ባደረገችው ቆይታ ተናግራለች።

የጽዳት ሰራተኞቹ ከተለመደው ሰዓታቸው ውጪ እነርሱ ባረፉበት ወለል ላይ በተደጋጋሚ ይመጡ እንደነበርና ሁኔታው እረፍት እንዳሳጣቸውም ነው የተናገረችው።

የአትሌቶቹን ገንዘብ መጥፋት በተመለከተም የቡድኑ መሪ ሁኔታውን ለሆቴሉ ሃላፊዎች አሳውቋል።

የሆቴሉ ሃላፊዎቹም በወቅቱ ስራ ላይ የነበሩ ሰራተኞችን በማነጋገር የአትሌቶችን ገንዘብ ለማስመለስ እንሰራለን ብለዋል።

ሌሎች ዜናዎች:

ሰበር ዜና
አትሌቶቻችን በለንደን ሆቴላቸው ውስጥ
ተዘረፋ ዝርዝሩን አዳምጡት።