በአፋር ክልል በተከሰተዉ የጎርፍ አደጋእጅግ በጣም ብዙ ነዋሪዎች አደጋ ላይ ሲሆኑ ብዙ እንሰሳቶች በጎርፉ ተወስደዋል

በአፋር ክልል በተከሰተዉ የጎርፍ አደጋእጅግ በጣም ብዙ ነዋሪዎች አደጋ ላይ ሲሆኑ ብዙ እንሰሳቶች በጎርፉ ተወስደዋል

KMN:-Aug. 07/2020

በምስሉ ላይ አራስ እናት በጎርፍ ውሃ ውስጥ ነው የወለደችው። አፋር በታሪክ ያለየዉ አደጋ እያስተናገደ ይገኛል። የፌደራል መንግስት ለአፋር የሚገባውን እገዛ ድጋፍ እያደረገ አይደለም። ለዚሁ ሁሉ እልቂት የአዋሽ ተፋሰስ ባለስልጣን ተጠያቂ ነው። የበሰቃ፣ የቆቃ፣ የከሰም እና የተንዳሆ ግድብ ልቅ ውሃ ከክረምቱ ተደምሮ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን የአሳኢታ የአፋምቦ የዱብቲና ሚሌ ህዝብ በጎርፉ አስከፊ አደጋ እያስተናገደ ይገኛል። ያሉን በአከባቢዉ ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ ናቸዉ::

የክልሉ መንግስት በበኩሉ ሁኔታዉን ሲገልፅ በአጠቃላይ በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ መሙላት ሳቢያ በደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ ከ49 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል ፤ 51 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ በስጋት ላይ እንደሆኑ የክልሉ መንግሥት አስታውቋል፡፡

የጎርፍ መጥለቅለቅ በእንዲህ ያለ ዝናብ ወቅት የሚጠበቅ ቢሆንም ዘንድሮ ግን በአዋሽ ዳርቻ በሚገኙ ወረዳዎች ላይም ጎርፍ እየተከሰተ ነው ተብሏል፡፡
እስካሁን ባለው መረጃ በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰው ሕይወት አልጠፋም ነገር ግን ነዋሪዎቹ በብዛት አርብቶ አደር በመሆናቸው በርካታ እንስሳት በጎርፍ ተጎድተውባቸዋል።

አስቀድመው ሰውነታቸው የተዳከመ በርካታ እንስሳት በዝናቡ መክበድ ምክንያት እንደሞቱ የክልሉ መንግስት ገልጿል።
በጎርፍ መጥለቅለቁ አስራ ስድስት (16) ወረዳዎች ሊጠቁ እንደሚችሉ የተገለፅ ሲሆን አሁን ላይ በሰባት (7) ወረዳዎች ጎርፍ መከሰቱን የክልሉ መንግስት ገልፇል::