በአዲስ አበባ የስልጤ ሙሉ መብት እንዲከበር እንሰራለን:-አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለችም ከሚሉ ወገኖች በጭርራሽ አንስማማም

በአዲስ አበባ የስልጤ ሙሉ መብት እንዲከበር እንሰራለን

አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለችም ከሚሉ ወገኖች በጭርራሽ አንስማማም ይልቁንስ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ብሔረሰብ በአዲስ አበባ የስልጤ ህዝብን መብት እና ጥቅም ለማስጠበቅ እኛም እንሰራለን የስልጤ የፖለቲካ ድርጅትም ይሰራበታል ስልጤ በአዲስ አበባ በቋንቋው እዲማር ማስቻል በበሀሉ እንዲኮራ ማድረግ እና አጠቃላይ መብቶቹን ለማስጠበቅ ይሰራል የስልጤን ሀቅ በአዲስ አበባ እናስጠብቃለን
የስልጤን ህዝብ መብት በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በመላው ኦሮሚያ በመላው የኢትዮጵያ ግዛቶች እንደ ኢትዮጵያዊነቱ ለማስከበር ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር እና ከሌሎችም ጋር በመተባበር እንሰራለን
እንደዛውም በስልጤ ግዛት ላይ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችን መብት ለማክበር እና ለማስከበር በሀቀኝነት እንሰራለን 
ከዛ በተረፈ አዲስ አበባ የኦሮሞ አይደለችም ብለን አንክድም ሀይማኖታችንም አባቶቻችንም ክህደት አላስተማሩንም
Silta Media Network SMN


ፊንፊኔ/ሸገር/አዲስ አበባ የባለቤትነት፣ አስተዳደር መብትእና ልዩ ጥቅም ክርክር ጉዳይ በተመለከተ

ሌላው የአካባቢው እና የከተማዋን ታሪክ ለታሪክ ባለሙያዎች ትተን የቅርቡን ኩነት ብናነሳ ፊንፊኔ/ሸገር/አዲስ አበባ ተብላ የምትታወቀው ከተማ የተመሠረተችው በአሁኑ ጊዜ ሼህ አላሙዲን አጥሮ የያዘው ፊንፊኔ መናፈሻ ውስጥ በሕዳር ወር 1879 ዓ.ም. እንደሆነ ለከተማዋ 100ኛ ዓመት ምስረታ በዓል የተተከለው የማስታወሻ ሐውልት ላይ ተመልክቷል ።

ፊንፊኔ መናፈሻ በደቡብ ፊንፊኔ ወንዝ እና ፊንፊኔ ድልድይ በሰሜን dhaካ(ደካ) አራራ የሚገኘው ሚኒሊክ ቤተመንግስት፣ በምስራቅ ECA and Hilton hotel፣ በምዕራብ ደግሞ ኢዮቤሊዩ ቤተሠንግስት ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ካርታ ስራዎች ድርጅት የሚያዋስኑት መናፈሻ ነው ። ከተማዋ እዚህ ቦታ ላይ ስለመመስረትዋ በመናፈሻው ሰሜን ጫፍ በኢሕድሪ መንግስት የመታሰቢያ ድንጋይ ቆሞላታል ። የኢፌድሪ ሕገመንግስት ከኢሕድሪ ሕገመንግስት የተረከበው ይህቺን ከተማ ነው ።

ሁለቱ መንግስታት የተረካከቡዋት ከተማ ዳር ድንበር እና ስፋት የሚታሰበው ከግንቦት 20 1983 ዓ.ም. ጀምሮ ባለው የሽግግር መንግስት ቻርተር በተጠቀሰችበት ጊዜ ባላት ዳር ድንበር እና ስፋት ነው ። የግንቦት 20 1983 ዓ.ም. የከተማዋ ዳር ድንበር በከተማዋ የአስተዳደር አወቃቀር ፣ የአየር ካርታ እና የከተማ ይዞታ እና ቤት ባለቤትነት ካርታዎች ድምር ንባብ ማወቅ ይቻላል ። በዚህ ድምዳሜ መሠረት ከ1983 ዓ.ም. የከተማዋ ድንበር ውጭ ያለው መሬት ሁሉ የአጎራባችዋ የኦሮሚያ ክልል መሬት ሲሆን ነዋሪዎቹም የኦሮሚያ ነዋሪዎች ናቸው ።

የኢፌድሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 49 ከተማዋ የራስዋ አስተዳደር እንደሚኖራት ፣ የከተማዋ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግስት እንደሆነ እና ከተማዋ ኦሮሚያ ውስጥ ስለምትገኝ ኦሮሚያ ከከተማዋ ልዩ ጥቅም እንዳላት ይደነግጋል ። የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ተብለው በሕጠመንግስቱ አንቀጽ 49/5/ስር የተዘረዘሩት ጥቅሞች የአገልግሎት አቅርቦት ፣ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እና ሁለቱን የሚያሳትፉ የአስተዳደር ጉዳዮች እንደሆኑ እና ዝርዝሩ በሕግ እንደሚወሰን ተመልክተዋል ። ሕገመንግስቱ ዝርዝር ሕጉ በማን አነሳሽነት እንደሚቀርብ እና በምን ዓይነት ሕግ እንደሚወሰን አያመለክትም ። ስለሆነም የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም የሚወስነውን ሕግ ኦሮሚያ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ወይም ፌደራል መንግስት ሊያነሱት /ሊያቀርቡት/ ይችላሉ ። የዝርዝር ልዩ ጥቅሙ ተደራዳሪዎች ኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ሲሆኑ ሕጉም ሁለቱ በጋራ ያጸደቁት ወይም በፌደራል ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀ አዋጅ ሊወሰን ይችላል ።

የድንበር ማካለሉ ስራ ሲሳራ ከደርግ መንግስት ወደ ኢሕአዴግ መንግስት የተላለፈው የከተማዋ ክፍል አሁን ካለበት ስፋት ከ1/4ኛ በታች እንደሆነ ይገመታል ። ብዙው የከተማው አሮጌ ክፍል በከተማ መልሶ ማልማት መፍረሱን ልብ ይሉዋል ።

በሕገመንግስቱ ኦሮሚያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም እንደምትጠይቅ እንጂ አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ልዩ ጥቅም እንደሚኖራት አልተደነገገም ። በአሁኑ ጊዜ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሲታይ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ለነዋሪዎችዋ የምታቀርበውን ንፁሕ የመጠጥ ውሀ የምታገኘው ከኦሮሚያ ስለሆነ ኦሮሚያ ለዚህ አገልግሎትዋ ተመጣጣኝ ክፍያ የመጠየቅ መብት አላት፤ ስምምነት ከሌለም አገልግሎቱን ሙሉ ለሙሉ የማቋረጥ ሙሉ መብት አላት ።

በሌላ በኩል ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከነዋሪዎችዋ እና ኢንዱስትሪዎችዋ የሚወጣውን ደረቅ እና ፈሳሽ ቁሻሻ የምትለቀው ወደ ኦሮሚያ ስለሆነ ኦሮሚያ በቁሻሻ እና ዓየር ብክለት ለሚደርስባት ጉዳት በገንዘብ የሚከፈል ቋሚ እና ተከታታይ ካሳ የማግኘት ሙሉ መብት አላት። በካሳ ክፍያ እና መጠን ላይ ስምምነት ከሌለ ኦሮሚያ ጉዳትዋን ለመከላከል ፣ ለመቀነስ ወይም ለማስቀረት ወደ ከተማዋ የሚገቡ እና ቁሻሻ ሆነው ወደ ኦሮሚያ ሊለቀቁ የሚችሉ ለምግብኘት የሚውሉትን ጨምሮ ማንኛውም ሸቀጦች እና እቃዎች ላይ ማዕቀብ የመጣል ሙሉ ሕጋዊ መብት አላት ።

ስለሆነም የኦሮሚያ አብዮት/ተቃውሞ/ መነሻ የሆነው እና የወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት መነሻ የሆነው የፊንፊኔ/ሸገር/አዲስ አበባ የባለቤትነት ፣ አስተዳደር መብት እና የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ጉዳይ ሌላ አነታራኪ እና ደም አፋሳሽ ጉዳይ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት የኦሮሚያ መንግስት እና የከተማዋ አስተዳደር በሚያደርጉት ድርድር ለከተማዋ ድንበር ማካለል እና ለኦሮሚያ ልዩ ጥቅም በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው እንመክራለን ።

ከታች የተመለከቱት ፎተተግራፎች የፊንፊኔ ድልድይ ፣ ፊንፊኔ መናፈሻ እና በመናፈሻው ውስጥ ሰሜን ጫፍ ላይ የአዲስ አበባን 100ኛ ዓመት ለማክበር ሕዳር 17 ቀን 1979 ዓ.ም. የቆመ የማስታወሻ ሀውልት ናቸው ። ሕዳር 17 ቀን 1979 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ የቆመላት የማስታወሻ ሐውልት በፎተው ላፍ በምታዮት ሁኔታ ለማንበብ በሚያስቸግር ደረጃ ተጎሳቁሏል ።

በመጀመሪያው ፎተግራፍ ላይ እንደምታዩት ፊንፊኔ ድልድይ ላይ ከአብዮት አደባባይ ወደ ECA ሲኬድ በድልድዩ ቀኝ ክፍል ላይ ካሉት ምሰሶዎች አንዱ ላይ በብረት ተጽፎ የነበረው የድልድዩ ስም በአሸባሪዎች ተገንጥሏል ። የስሙን መገንጠል ልብ ብሎ ያረመው የለም ።

ሼክ አላሙዲን መናፈሻውን አጥሮ ሲይዝ ካላጣው ቦታ የከተማዋን መታወሻ ሀውልት የሰሜን ክፍል ገንጥሎ የራሱን ስም ጽፎበታል ። ተው ያለውም አልተገኘም ።

Via: Bayissa Olana Gonfa

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


Finfinnee(አዲስ አበባ) የኦሮሞ ናት…
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን

የብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መስተዳድሮችን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁጥር 7/1984 መሠረት አዲስ አበባ) ክልል14 በመባል እራሱን ሲያስተዳደር ነበር፡፡ የኢፌዲሪ ሕ/መ አንቀጽ 49(5) የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅም የተጠበቀ ነዉ፡፡ ቀደም ሲል ከሕገ/መንስቱ በፊት አ.አ. የሚትባል ወሰኗ የሚታወቅ ከተማ እንደነበረች ከሕገ መንግስቱ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሕገ መንግስቱ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በሚመለከት የተለያዩ ሕጎች ወጥቷል፡፡እነዚህም ሕጎች ፡-የመጀመሪያዉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 87/1989 ሲሆን አንቀፅ 2(1) ሥር ለአ.አ. በተሰጠዉ ትርጉም መሠረት አ.አ. ማለት የከተማዉ ክልልና 25 የገጠር ቀበሌዎች የሚያጠቃልል ቦታ መሆኑ ተደንግጓል፡፡ ይህ ወሰን ሕገ መንግስቱ ከሚያዉቀዉ ወሰን ሁለት እጥፍ ነዉ፡፡ በተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 311/1995፣ላይ ይህ ለአ.አ. በተሰጠዉ ትርጉም አልተሸሻለም፡፡ የተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995፣ አንቀፅ 5 ሥር ቀደም ሲል ያለዉ ወሰን እንደለ ሆኖ የከተማዉ ወሰን አስተዳደሩ ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚያደርገዉ ስምምነት ወይም በፌዴራል መንግስት ይወሰናል ይላል፡፡ ይህ አዋጅ ቀደም ሲል የተወሰነዉን ወሰን እንዳለ ሆኖ ወደፊት ሌሎች ቦታዎችን የመጨመር ፍላጎት እንዳለዉ እና አ.አ. እየሰፋች እንደምትሄድ ያለዉን ፍላጎት ያሳያል፡፡ የአ.አ. ወሰን እንደነገሩ ሁኔታ ከኦሮሚያ ጋር በመነጋገር ወይም በፌዴራል መንግስት ወደፊት ሊወሰን እንደሚችል ያሳያል፡፡ በመሆኑም በሕገመንግስቱ ብቻ ነዉ እንጂ በዚህ አዋጅ መሠረት የአ.አ. ወሰን እስከ አሁን እንደማይታወቅ ነዉ፡፡ የተሻሻለው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር ለማሻሻል የወጣ አዋጅ ቁጥር 408/1996. ቀደም ሲል ስለ አ.አ. ወሰን በአዋጅ ቁጥር 361/1995 የተጠቀሰዉ አልተሸሻለም፡፡
አዋጁም መሠረት የአ.አ. ወሰን ከዚህ በፊት የተወሰነ ቢሆንም እንዳልተወሰነ ተቆጥሮ በአዲስ ወሰን ከአሁኑ ሰፋ የሚትል አዲስ አ.አ. ወደፊት የምትወለድ እንደሆነ ያሳያል፡፡ አ.አ. ከተማ የከዚህ በፊቱ ወሰኗ መሠረት በማድረግ ሳይሆን አሁን ባለችበት ሁኔታ ወይም ተጨማሪ ቦታዎችን በማከል ወሰን ሊበጅላት እንደሚገባ መፈለጉን ያመለክታል፡፡ ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ልዩ ጥቅም እንድታሟላ የምትጠበቀዉ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ ከኦሮሚያ ጋር ያላት ወሰን በ1984 በዉል ተለይቶ የሚታወቅ ነዉ፡፡ በመሆኑም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በቅርብ ቀን የወሰን ምልክትም እንደሚያደርግ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

~By Abduljebar Hussien.