በአዲስ አበባ ከተማ ከ25 ዓመታት በላይ አፋን ኦሮሞ በማስተማር ብዙ ውጣ ውረዶችን

አዲስ አበባ ከተማ ከ25 ዓመታት በላይ አፋን ኦሮሞ በማስተማር ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፉት መምህር

መምህር ተፈራ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አፋን ኦሮሞን ያስተምራሉ

(bbcamharicnews) —ስሜ ተፈራ ተኤራ ይባላል። አንዳንድ ሰዎች አምባሳደር እያሉ ይጠሩኛል። ይህን ስም አፋን ኦሮሞን በማስተማሬ ደስተኛ የሆኑ ሰዎች ናቸው ያወጡልኝ።

በ1971 ዓ.ም ከአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የንግድ ሥራ ኮሌጅ በሒሳብ አያያዝ በዲፕሎማ ተመርቄያለሁ። ለጥቂት ዓመታትም በሒሳብ አያያዝ ሙያ ሠርቻለሁ።

ከልጅነቴ ጀምሮ ለኦሮሞ ቋንቋና ባህል ጥልቅ ፍቅር ነበረኝ። የሒሳብ ሥራ ሙያዬን እርግፍ አድርጌ በመተው ለብዙ ዓመታት ለመስራት ስመኝ የነበረውን ስራ ጀመርኩ።

መምህር ተፈራ ተኤራ

በ1985 ዓ.ም አፋን ኦሮሞ የክልሉ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ አፋን ኦሮሞን የሚያስተምር መፅሐፍ እጄ ገባ።

ከዛም ከሌሎች 7 ሰዎች ጋር በመሆን ከኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ፍቃድ በመውሰድ በባልቻ አባ ነፍሶ ትምህርት ቤት ውስጥ ማስተማር ጀመርን።

ከእኔ ጋር ማስተማር ጀምረው የነበሩት ጓደኞቼ በፖለቲካ እና በተለያየ ምክንያት ለትንሽ ጊዜ ካስተማሩ በኋላ ማስተማራቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ።

በእኔ ላይም ይደርስ የነበረውን የተለያየ ጫና ተቋቁሜ ማስተማሬን ቀጠልኩ።

ባለፉት 25 ዓመታት አፋን ኦሮሞን በማስተማሬ ደስተኛ ያልነበሩ ሰዎች ብዙ ስሞችን አውጥተውልኛል።

ቁቤ፣ ላቲን፣ ኦሮሚያ፣ ወሬ እና ሌሎችም ብዙ ስሞች ወጥተውልኝ ነበር።

አንድ ቋንቋ ሊያድግ የሚችለው የቋንቋ ተናጋሪዎችስለተናገሩት ብቻ ሳይሆን የሌላ ብሔር ተወላጆችም ቋንቋውን መናገር ሲችሉ እንደሆነ ጥልቅ እምነት አለኝ።

ለዚህም ነው መማር የሚፈልጉትን በሙሉ ሳስተምር የኖርኩት።

ሰዎች አፋን ኦሮሞን ማንበብ እና መጻፍ እንዲችሉ አስተምራለሁ።

 • [perfectpullquote align=”right” cite=”” link=”” color=”” class=”” size=”18″]
  • በባልቻ አባ ነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ለ65ኛ ዙር እያስተማሩ ነው
  • ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በሚኒሊክ ት/ቤት ለ25ኛ ዙር በማስተማር ላይ ይገኛሉ።
  [/perfectpullquote] እስከአሁን ድረስም በወር 15 ብር ብቻ በማስከፈል እያስተማርኩ እገኛለሁ። ማስተማር ስጀምር የነበረው ዋጋ አሁንም አልተቀየረም።

  በርከት ያሉ ጋዜጠኞች፣ መምህራን፣ ሃኪሞች፣ መሃንዲሶች እንዲሁም የመንግሥት ባለስልጣናት እኔ ጋር መጥተው ተምረዋል።

  ባለፉት 25 ዓመታት ቋንቋውን በማስተማሬ ብዙ ችግሮችን አሳልፌያለሁ።

  ማስተማሬን እንዳቆም የተለያዩ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች ይደርሱኝ ነበር። በስለት ተወግቼያለሁ፤ ”የተፈራ ቁቤ ይወድማል” ተብሎም ቤቴ በር ላይ ተለጥፏል።

  በዛ አስቸጋሪ ወቅት ተማሪዎቼ ነበሩ እስከ ቤቴ ድረስ የሚሸኙኝ።

  ን ኦሮሞ አሁን ተፈላጊ ሆ

  ”የተፈራ ቁቤ ይወድማል” ሲሉ የነበሩ፤ ዛቻዎችን እና ማስፈራሪያዎችን ሲልኩ የነበሩ ሰዎች ራሳቸው ዛሬ ላይ አፋን ኦሮሞ አስተምረን እያሉ ነው።

  ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ተማሪዎችጋር

  ይህም ቋንቋችን ምን ያህል ተፈላጊ እየሆነ እንደመጣ ያሳየኛል።

  አሁን ጊዜው ተቀይሯል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን የኦሮሞን ቋንቋና ታሪክ አስተምሬያለሁ።

  ዘንድሮ በአዲስ አበባ በአፋን ኦሮሞ የሚያስተምሩ ት/ቤቶች በመከፈታቸው አጅግ ደስተኛ ነኝ። ድካሜም ከንቱ አልቀረም።

  በለፉት 25 ዓመታት በስራዬ መልካም የሚባል ጊዜን ባላሳልፈም፣ በህይወቴ የሚያኮራኝን ተግባር የመፀምኩባቸው ዓመታት ናቸው።

  እድሜዬ ወደ 63 እየተጠጋ ነው። እርጅናም እየተጫጫነኝ ነው። አሁን የምፈልገው ሥራዬን ተረክበው የሚያስቀጥሉ ወጣቶችን ነው።