በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ሳምንት ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል- ፖሊስ

በአዲስ አበባ ባሳለፍነው ሳምንት ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል- ፖሊስ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ በመዲናዋ ባንዲራ ከመስቀል እንዲሁም ከሌሎች ህገ ወጥ ተግባራት ጋር ተያይዘው በተነሱ ግጭቶች የሰው ህይወት ማለፉን ተናግረዋል

ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ፥ በከተማዋ ከመስከረም 5 በፊት ማንኛውንም አይነት የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ አልተሰጠም፤ ሆኖም ግን ሁከት እስካልተፈጠረ ድረስ ማንኛውም ሰው ባንዲራ ሲሰቅል ነበር፤ የፀጥታ ሀይሉም ይህንን በንቃት ሲከታተል ነበር ብለዋል።

ሆኖም ግን ባንዲራ ከመስቀልና የመንገድ ጠርዞችን ቀለም ከመቀባት ጋር ተያይዞ የመፍቀድና የመከልከል ስራው የፖሊስ ሆኖ ሳለ፤ ማንነታቸው ያልታወቁ አካላት ከየመንደሩ በመውጣት ስርዓት አልበኝነት በሰፈነበት መንገድ ለማስቆም ሲሉ ግርግር ተፈጥሯል ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከመስከረም 2 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 7 2011 ዓ.ም በከተማዋ ሁከት እና ግርግር ተፈጥሯል ብለዋል ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ።

ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ግርግርም በኮልፌ ክፍለ ከተማ የ14፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 5፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 3፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 5 በድምሩ የ28 ሰዎች ህይወት ማለፉን አስታውቀዋል።

ከእነዚህም ውስጥ የአብዛኛዎቹ ህይወት ያለፈው በድብደባ፣ በድንጋይ እና በዱላ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የሰባት ሰዎች ህይወት ደግሞ በፀጥታ ሀይሉ ነው ብለዋል።

በፀጥታ ሀይሉ ህይወታቸው ካለፈው ውስጥ አንድ ሰው በፖሊስ ስህተት ነው ህይወቱ ያለፈው ያሉ ሲሆን፥ ይህን የፈፀመው ፖሊስም በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድተዋል።

በተጨማሪም አንድ ሰው ፍርድ ቤት ሊዘርፍ ሲል በፀጥታ ሀይል ህይወቱ ማለፉን እና ቀሪዎቹ 5 ሰዎች ደግሞ መስከረም 7 ቀን 2011 ዓ.ም በተፈጠረው ሁከት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ህይወታቸው ማለፉን አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ላይ በድብደባ ጉዳት ደርሷል ያሉ ሲሆን፥ በንብረት ላይም ባንክን ከመዝረፍ ሙከራ ጀምሮ በርካታ ጉዳቶች መድረሳቸውን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጠፋው የሰው ህይወት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማውም ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ተናግረዋል።

ፖሊስ ሁከቱን ለማስቆም ባደረገው ሙከራም በህገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው የተገኙ በርከት ያሉ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንም ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛውን በማጣራት እና በመምከር ከእስር እንዲለቀቁ ማድረጉንም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በሁከቱ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩ 1 ሺህ 204 የሚሆኑ ግለሰቦችን ከተለያዩ አካባቢዎች በመሰብሰብ በቀጣይ ሌላ ጥፋት ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ሰንዳፋ እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ለተሃድሶ ስልጠና ወደ ጦላይ እንዲገቡ መደረጉንም ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በ10ሩም ክፍለ ከተሞች በሁከትና ግርግሩ ተሳታፊ የነበሩ እና ማስረጃ የተገኘባቸው 107 ተጠርጣሪዎችን ደግሞ ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ነው ኮሚሽነሩ ያስታወቁት።

ከዚህ ውጪ ግን ፖሊስ ከሺሻ ቤት፣ ቁማር ቤት እና ጫት ቤት ጋር በተያያዘ በድምሩ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።

ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል ባደረገው ዘመቻም በሺሻ ቤት 1 ሺህ 459 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ 94 ሰዎች በጫት ቤት እንዲሁም 31 ሰዎች በቁማር ቤት በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።

ከእነዚህ ውስጥም በቁማር ቤት ከተያዙት ውጪ አብዛኛው ምክርና እና ተግሳፅ ተሰጥቷቸው መለቀቃቸውንም ተናግረዋል።

ከዚህ ውጪ ግን ሰሞኑን በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች ገሚሱ ስንዝናና፣ ስንጠጣ፣ ኳስ ስናይ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለን እየተባለ የሚሰራጨው ወሬ ሀሰት መሆኑንም ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ አስታውቀዋል።

ይህንን ማረጋገጥ ለሚፈልግ አካል ካለ ፖሊስ አስፈላጊውን ማስረጃ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።

ነገር ግን ፖሊስ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በሚሰራበት ወቅት የሚናፈሱ ወሬዎች ህገ ወጥነትን ለማስፋፋት ካልሆነ ሌላ አላማ የላቸውም ሲሉም ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ አክለውም፥ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ውስጥ እስከ መኪና ስርቆት የደረሰ ዘረፋ መስፋፋቱንም አንስተዋል።

አብዛኛዎቹ ዘራፊዎችም ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ የመጡ ናቸው ያሉት ኮሚሽነሩ፥ ከደሴ፣ ጎንደር እና አርባ ምንጭ ከተሞች የመጡ ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም አስታውቀዋል።

ፖሊስ ከዚህ በኋላ ዝርፊያን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚሰራውን ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል፤ ህብረተሰቡም ለፖሊስ የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥል ሲሉ ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በሙለታ መንገሻ


አዲስአበቤ አሁንም ከኢትዮጵያዊው አብርሃም ሊንከን ጐን እንቁም!

አዲስአበቤዎች ከፊታችን የህልውና አደጋ ተጋርጦብናል። አዲስአበቤ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር የጀመረው ንቅናቄ ያስፈራቸው የመንፈስ ጐልያዶች ሰይፋቸውን መዘውብናል። ተስፋ የጣልንበት ዛሬም ተስፋችን ያልተሟጠጠበት የዶክተር አቢይ መንግስት ግራ በሚያጋባ ሁኔታ የጅምላ እስሩን አይቶ እንዳላየ ሆኗል። ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኗል። ከሁኔታዎች እንደምንረዳው የለውጥ ሃይል የሆነው የዶክተር አቢይ ቡድን የሴራውን ባለቤቶች በሚገባ አውቋቸዋል። ይህም ሆኖ ከኪሳቸው እያወጡ “ሳሪስና መርካቶ ያለ አዲስአበቤ 43 ኦሮሞ ገደለ” ብለው የሩዋንዳ መሰል እልቂትና ብጥብጥ ሲደግሱ መንግስታዊ ምላሽ ለመስጠት አልፈለገም። እናቴ ምነው በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ እንደሚባለው አዲስአበቤ አጠፋ የተባለው ነብስ ከ43 ወደ 60 አድጓል። ነገ 100 አሊያም 200 የማይሆንበት አንዳችም ምክንያት የለም። ከነገ ወዲያ አንድ ሺህ ይደርሳል።

አዲስአበቤ ሆይ! አደጋ መጣሁ መጣሁ እያለህ ነው። ሁኔታዎች አደገኛ አቅጣጫ እየያዙ ነው። በዚህ ከቀጠለ ሩዋንዳን የመሰለ አደገኛ የታሪክ ክስተት በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ አያንዣብብም ማለት አይቻልም። ” መርካቶ ላይ ጉራጌ ችግር ፈጥሮብሃል” የሚል የእርምጀሰ ውሰድ መልእክት ከአክራሪው ቡድን የተላለፈው ዝም ብሎ አይደለም። የተጠና፣ የታቀደ፣ ህዝብን መሃል መርካቶ ላይ ለማፋጀትና ለማተራመስ በማሰብ የተዘጋጀ ውጥን ነው። እርግጥም አክራሪው ቡድን እሳቱን ማቀጣጠል ከመርካቶ መጀመሩ እልቂቱን ወደ ስበት ማእከሉ ለመጐተት በማሰብ ነው። እርግጥ ይሄ ለአዲስአበቤ የመረረ ጥላቻና የበታችነት ስሜት ያለው ቡድን ያልተገነዘበው ነገር አዲስ አበባ ውስጥ አንዴ እሳቱ ከተቀጣጠለ ሁላችንም ሰለባ እንሆናለን እንጂ ማንም ወገን አሸናፊ የሚሆንበት እድል የለም።

አዲስአበቤ ሆይ! የዶክተር አቢይ የለውጥ አስተሳሰብ ተሸንፎ ስልጣን በእነዚህ አደገኛ ሃይሎች ከተጠለፈ የሰነቅነው ተስፋ ወደ ጥልቅ ባህር ይወረወራል። እነዚህ አገር ለማፍረስ ቆርጠው የተነሱ አዲስ በቀል ዘረኞች ዋነኛ አላማቸው የለውጥ ሃይሉን ጉዞ መቀልበስ ነው። ይሄ ካልተሳካላቸው የለውጥ አስተሳሰቡን በማስገደድ ጠምዝዞ ማስቀየር ነው። ይህን እኩይ ተልእኮአቸውን ለማስፈፀም ከህውሓት ቆሞ ቀር ቡድን እና ለውጡ ይጐዳኛል ብለው ከሚያምኑት ጋር የሶስትዬሽ የጋራ ግንባር ፈጥረዋል። ይህ በሶስት ትናንሽ ጭንቅላት የተፈጠረው የጋራ ግንባር መዳረሻው አንድ ባይሆንም ታላቁን የለውጥ አጀንዳችንን ለመቀማት የሚችሉበት እድል ሠፊ ነው። ሰሞኑን ዶክተር አቢይ ሽግግር እያካሄደ አይደለም፣ ብቃት የለውም፣ አገሪቷ ላይ ሰላም ማስፈን ስላልቻለ ከስልጣን ይውረድ የሚል መፈክር ይዘው ብቅ ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።

አዲስአበቤ ሆይ! ይህንን እና የመሳሰለውን ሁኔታ ሁላችሁም በያላችሁበት የታዘባችሁት ይመስለኛል። አሁን ያለው ጥያቄ እያንዳንዳችን ምን ልናደርግ እንችላለን የሚለው ነው። በተለይ ከሶስት ሚሊዬን የሚበልጠው አዲስአበቤ ወጣት መዲናውን አልፎ ሄዶም አገሩን እንዲያድን ምን አይነት ሰላማዊ እንቅስቃሴ እናቀጣጥል የሚለው “በጊዜ የለንም” እሳቤ ምላሽ ማግኘት አለበት። ለጊዜው የማላስታውሰው ታዋቂ ፈላስፋ ” አለምን አሸንፈህ ለመያዝ ከፈለክ ፣መጀመሪያ ራስህን አሸንፍ” ይላል። If you want to conqure the world, conquer yourself first!

እናም ራሳችንን እናሸንፍ። ከተስፋ መቁረጥና ጨለምተኝነት እንውጣ። የተጀመረውን መነቃቃት ተቋማዊ ይዘት እንስጠው። የማንም ባለጊዜ እፉኝት ዘረኛ በበታችነት ስሜት ውስጥ ሆኖ እንደ መንገድ ጭቃ እንዳይረግጠን ንቅናቄያችንን እናቀጣጥል። የአዲስአበቤ የተባበረ ሃይልና አቋም ዘረኞቹን ከመድፈቅ ተሻግሮ የኢትዮጵያዊነት የድል ምልክት ነው። በአገር ደረጃ የተነዛውን ሽብር፣ እልቂትና የአገር ጥፋት ልንከላከል እንችላለን። የእኛ የኢትዮጵያውያን ደምና አጥንት የታፈረና የተከበረ እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ክቡርነቱን እናስጠብቅ።

የአዲስ አበቤ ወጣቶች! እኛ መንቀሳቀስ ከጀመርን በስልጣን ላይ ያለውና ታላቅ ራዕይ ያነገበው የዶክተር አቢይ ቡድን ከጐናችን ይቆማል። ያለምንም ጥርጥር ይረዳናል። እዚህ ላይ እንድትገነዘቡት የምፈልገው ቁምነገር ሶስት የጋራ ግምባር የፈጠሩት የዘረኛ ስብስቦች ፍላጐታቸው እኛን የለውጥ አራማጅ ከሆነው ዶክተር አቢይ ጋር ማጣላት ነው።

በእኔ እምነት ዶክተር አቢይ በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ሊጫወት የሚፈልገው ሚና የአሜሪካ ተወዳጅ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን የተጫወተውን ይመስለኛል። በለውጥ አመራር ውስጥ 16ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት አብርሃም ሊንከን ” የወደፊት መውደቅ” ተምሳሌት ተደርጐ ይወሰዳል። ወደፊት የሚወድቅ ሰው ብርቱ ፍላጐት፣ የመለወጥ ጽናት፣ የኃላፊነት ስሜት፣ ለራስ የሚሰጥ ክብር፣ ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ፈቃደኝነትን ይጠይቃል። አብርሃም ሊንከን እንደዚህ አይነት ስብእና እንዳለው ይነገራል። ከሁሉም በላይ ግን አብርሃም ሊንከን የተገኘው የአሜሪካ ጥቁሮች ጭንቀት እጅግ በከበደበትና የአሜሪካ አንድነት በተናጋበት ዘመን ነበር። ኢትዮጵያዊው አብርሃም ሊንከንም ከባህሪም ሆነ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተመሳሳይ ይመስለኛል።

Ermias Legesse Wakjira

Qeerroon lola isaanii keessa darbee injifate, nagaa qabsoon isaa fides ni tikfata. Kaayyoo isaas haalan fiixa baasa.

You have prevailed in the struggle (which was no less than a full scale war). You shall win the peace too–and the politics of transition thereof. We persevered through ‘war’. We will survive the intrigues of their cheap politics.

#OromoRevolution #Qeerroo


#Amboo: bu’aa qabso tikfadhaa!!! (via inbox)

“Qeerroon oromiyaa qabsoo dhiiga ilmaan oromootiin jijjirama dhufaa jiru akka diinoota keenyaan duubatti hin deebne bakka jirtu hundatti waardiyyaa ta’ii eeggadhu !!!!!!
Qeerroo Amboo!”

Tsegaye Ararssa

 

ኣንድ የገረመኝ ነገር
ከሁለት ሶስት ኣመታት በፊት ቄሮ የተለያዩ የኦሮምያ ከተሞችን በጸረ ወያኔ ኣመጽ ሲያንቀጠቅጥ እልህ የተጋባው ግንቦት ሰባት ከኣንድም ሁለት ሶስቴ ለኣዲስ ኣበቤዎቹ የሰልፍ ጥሪ ኣቅርቦ ሰሚ ማጣቱን እናስታውሳለን። የቅርብ ጊዜ ትዝታ እንኳን ብናይ ዶር ኣብይ ወደ ስልጣን ከመምጣቱ ጥቂት ወራት በፊት የሸገር ሰው የነፍስ ወከፍ ቀይ ካርድ ኣዘጋጅቶ ሰልፍ እንዲወጣ ቀን ተጠቅሶ የጦፈ ጥሪ በኢሳት ሚድያ ኣማካኝነት መደረጉን ኣልረሳንም። ነገር ግን በቀጠሮው እለት ወፍ ኣልነበረም። ሲጠቃለል የሸገር ወጣት ያን ሁሉ የግንቦት ሰባት ጥሪ ያልተቀበለው በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበረው ወያኔ ስለሆነ ነው። የወያኔን ዱላ ቀምሶ ያየ በመሆኑ ፈራ። ጎመን በጤና ኣለ። ቄሮ ግን ደረቱን ለወያኔ ጥይት በመስጠት ሸገር ውስጥም ጭምር ሰልፍ ወጥቶ ወያኔን ነቀነቀው። ዛሬ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው የሸገር ኣራዳ ቄሮ መስቀል ኣደባባይ ላይ ከወያኔ ቅልብ ጦር ጋር ኣንገት ለኣንገት ሲተናነቅ ሽንቱን ሱሪው ላይ እየለቀቀ በመስኮት ኣጮልቆ ከማየት ውጭ ወያኔ ለኔም ጠላቴ ነው ብሎ ቄሮን የመቀላቀል ድፍረት ኣልነበረውም። ቄሮ በመጨረሻም ወያኔን ነቅንቆ በመንቀል የዛሬውን ነጻ ቀን ኣመጣ። ወያኔን ያንበረከከውን ቄሮ የሸገር ወጣት ሲሳፈጠውም ለማየት በቃን። “ኣያውቁንም ኣዎ ኣያውቁንም” ነበር ያለው ዘፋኙ? ኣዎ ረስተውናል።

Yaya Beshir

Kekiya Badhadha – Dhugaa Maseenaaree!! – New Ethiopian Oromo Music 2018 (Official Video)