በአዲስ አበባ በመንግስት የፀጥታ አካላት የተከለከለ መግለጫ አለመኖሩን ፖሊስ አስታወቀ

በአዲስ አበባ በመንግስት የፀጥታ አካላት የተከለከለ መግለጫ አለመኖሩን ፖሊስ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በከተማዉ በመንግስት የፀጥታ አካላት የተከለከለ መግለጫ አለመኖሩን ገለፀ፡፡

ጌት አማካሪዎች የንግድና ኢንቨስትመንት የተባለ ድርጅት ግን በዚህ ሳምንት ለሁለት ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳልሰጥ ተከልክያለሁ ብሏል፡፡

የድርጅቱ ዳይሬክተር አቶ ጌታነህ ባልቻ ለኢቲቪ እንደተናገሩት አዲስ የሚቋቋምን የቴሌቭዥን ጣቢያ አስመልክቶ ትናንት በሂልተን ሆቴል ሊሰጥ የነበረዉ መግለጫ በሆቴሉ የፀጥታ ሀላፊ በኩል መግለጫዉ በመንግስት አካላት ስለመከልከሉ ተነግሮናል ብለዋል፡፡

የሂልተን አዲስ ሆቴል በበኩሉ ጋዜጣዊ መግለጫዉ የተከለከለዉ ከሆቴሉ ጋር ውል የሌላቸዉ ግለሰቦች መግለጫዉን እንሰጣለን በማለታቸዉ ነዉ ብሏል፡፡

የሆቴሉ ጊዜአዊ የጥበቃ ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ስለሺ ተሰማ መግለጫዉ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንደሚሰጥ የተፈፀመ ዉል እንደሌላቸዉ ለአዲስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡

Ethiopian Broadcasting Corporation


#ቅሌት
“ግለሰቡ ከሆቴሉ ምን አይነት ውል ሳይኖረው በሌላ ድርጀት በተያዘ የአዳራሽ ኪራይ ውል ተጠቅሞ መግለጫ ለመስጠት ሲሞክር በሆቴሉ አሰራር መሰረት ተከልክሏል” #የሂልተን_ሆቴል_ስራ_አስኪያጅ
ላደርገው የነበረው መግለጫ በመንግስት ሃይሎች ታግዶብኝል፡፡ #ጋዜጠኛ_እስክንድር_ነጋ
ስለ መግለጫው መረጃም አልነበረብኝም፣ ክልከላም እንዳላደረኩም- #የአአ_ፖሊስ_ኮሚሽን

Segni Gudina