በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መንግሥት የሚጠቀመው ሥልጣን፣ ሕጋዊ መሠረት ያለው መንግሥት ሥልጣን ነው እንጂ ያልተመረጠ መንግሥት ሥልጣን አይደለም።

በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መንግሥት የሚጠቀመው ሥልጣን፣ ሕጋዊ መሠረት ያለው መንግሥት ሥልጣን ነው እንጂ ያልተመረጠ መንግሥት ሥልጣን አይደለም።

1. በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ፣ አንድ፣ በሕዝብ በተመረጠ ፓርላማ የተሰየመ ሕጋዊ መንግሥት፣ አስቸኳይ ሁኔታውን ያስገደደውን አደጋ ለመቋቋም ወይም ለመመከት እንዲችል፣ የተለየ ሥልጣን ይሰጠዋል።

አደጋውን ለመቆጣጠር አስፈላጊ በሆነ መጠንም፣ አንዳንድ ለመብት እውቅና የሚሰጡ የሕግ ድንጋጌዎችን፣ በተወሰነ ገደብ ውስጥ፣ ለመተላለፍ እንዲችል ይፈቀድለታል።

በምንም ሁኔታ የማይተላለፋቸው ድንጋጌዎችና የማይጥሳቸው መብቶችም በዝርዝር ይቀመጣሉ።

ብቻም አይደለም።

የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣኑን፣ ለተፈለገው ዓላማና በትክክለኛው አግባብ መጠቀም አለመጠቀሙን የሚቆጣጣጠር፣ ይሄንንም ለፓርላማው በዝርዝር የሚያስረዳ፣ የአስቸኳይ ጊዜ መርማሪ ቦርድ ወይም ኮሚሽን ይቋቋማል።

ምንም እንኳን በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ፣ ለወትሮው የመንግሥትን ሥልጣን በወሰን የሚያቆዩ ገደቦች ላላ (relax) የሚደረጉ ቢሆንም፣ የአስቸኳይ ጊዜ ስላለ ብቻ፣ መንግሥት እንደፈለገ ይሆናል ማለት አይደለም። በአስቸኳይ ጊዜም ቢሆን ለሥልጣን አጠቃቀም ገደብ አለ። የሕዝብ ሥልጣን ይዞ መረን መውጣት አይፈቀድም።

2. በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ውስጥ፣ የአስቸኳይ ጊዜን የሚመለከተው አንቀጽም (ማለትም አንቀጽ 93) ይሄንኑ ያረጋግጣል። በዚህም መሠረት፣ አስቸኳይ ጊዜ ሁኔታን በማወጅ፣ መንግሥት (ማለትም ሥራ አስፈፃሚው)፣ ከወትሮው የተለየ ሥልጣን እንዲጠቀም ምክንያት የሚሆኑት፦

ሀ. ጦርነት

ለ. ከወትሮው የሕግ አስከባሪዎች አቅም በላይ ሆኖ፣ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ውስጥ የሚከት የሕግና ሥርዓት መፍረስ፣

ሐ. የተፈጥሮ አደጋ፣ እና

መ. ወረርሽኝ

ናቸው።

እነዚህ ሁኔታዎች መኖራቸው በተጨባጭ ከተረጋገጠ፣ የምኒሥትሮች ምክር ቤት፣ ይሄን በመግለፅ ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጆ፣ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለፓርላማው ያሳውቃል። ፓርላማው ካጸደቀው፣ አዋጁ እስከ 6 ወር ለሚሆን ጊዜ ሕግ ሆኖ ያገለግላል። በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ ችግሩን መቆጣጠር ካልተቻለ፣ መንግሥት አዋጁን ለተጨማሪ አራት ወራት እንዲያራዝምለት ይጠይቃል።

የመንግሥትን አተገባበር ለመቆጣጠርም አጣሪ ቦርድ ይቋቋማል። ቦርዱም የተከሰቱ መተላለፎችና ተቀባይነት የሌላቸው የመብት ጥሰቶችን ይመረምራል፣ ጥፋቱን የፈጸሙትም እንዲጠየቁ የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ያቀርባል።

ጥሰቶች ተቀባይነት አላቸው የላቸውም የሚለውን ለመወሰን ደግሞ፣ ምክንያታዊነትን (rationality, i.e., the existence of causal relations between the violative act and the harm the act was intended to avert)፣ ተመጣጣኝነትን (proportionality)፣ እና የሰብዓዊ ክብርን አይነኬነት (dignity) ከግንዛቤ ይከታሉ።

ይሄም ሆኖ፣ በዚህ ጊዜም እንኳን፣ መንግሥት፣ የማይተላለፋቸው ድንጋጌዎች፣ የማይጥስ-የማያጥፋቸው መብቶች አሉ። እነዚህም፣ በአንቀጽ 93(4) ውስጥ እንዲሚከተለው ተዘርዝረው ይገኛሉ፦

-አንቀጽ 1: የአገረ-መንግሥቱ ኦፊሴላዊ ሥም እና ሥሙ የሚገልጸው (ወይም የተሸከመው) የፌደራላዊ፣ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሥርዓትና የአገረ-መንግሥት አወቃቀር፤

-አንቀጽ 18፡ የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብርን ለማስከበር ዓላማ ተብሎ የተቀመጠ፣ ኢሰብዓዊና ጭካኔ የተሞላበት አያያዝና ቅጣትን ለምስቀረት የተጣለ ክልከላ፤

-አንቀጽ 25፡ የእኩልነት መብትና በማናቸውም ምክንያት የተለያየ አያያዝ እንዳይደረግ የሚከለክል ድንጋጌ፤

-አንቀጽ 39(1)፡ የብሔሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት፣ እስከ መገንጠል ድረስ፤

-አንቀጽ 39(2)፡ የብሔሮች የባህል፣ የቋንቋ፣ የታሪክና የማንነት መብት።

(በሕይወት የመኖር መብት ከዚህ የአይነኬ መብቶች ዝርዝር ውስጥ መካተት ሲገባው አለመካተቱ ሥህተት ይመስለኛል።)

ይሄ ሁሉ፣ ከላይ የተቀመጠው ዝርዝር ድንጋጌ፣ የመንግሥት ሥልጣን፣ በአስቸኳይ ጊዜም እንኳን አለገደብ የተለቀቀ ሳይሆን፣ በገደብ ውስጥ ተወስኖ የተቀመጠ መሆኑን ያሳያል።
——-

3. መቼም ቢሆን መረሳት የሌለበት ነጥብ፣ እንዲህ ዓይነቱን የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን የሚጠቀመው አካል፣ በሕገ-መንግሥቱ ድንጋጌዎች መሠረት በአግባቡ በተመረጠና የሥልጣን ዘመኑም ባላለቀ ፓርላማ የተሰየመ፣ ሙሉ ሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ማንዴት ያለው፣ መንግሥት ብቻ መሆኑን ነው።

በመሆኑም፣ የሥልጣን ዘመኑ ያለቀ ፓርላማ፣ ያስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን፣ ለሥራ አስፈፃሚው ለመስጠት አይችልም።

ወይም፣ የራሱንና የሰየመውን መንግሥት የሥልጣን ዘመን ለማራዘም ሲል ብቻ የአስቸኳይ ጊዜ ማወጅ አይችልም። የአስቸኳይ ጊዜ ለማወጅ የሚያስገድዱት ሁኔታዎች ዝርዝር ይሄን አይመለከትምና።

ዘመኑ ባለቀ ፓርላማ የተሰየመ መንግሥትም፣ በአስቸኳይ ሁኔታ ሥም ከተሰየመለት በላይ ስልጣኑን በማራዘም፣ ማገልገል አይችልም።
——–

4. የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ፣ ምርጫን ለመሰረዝ ወይም ለማስተላለፍና የመንግሥትንና የፓርላማን የሥራ ዘመን ለማስቀጠል፣ ምክንያት አይሆንም።

የምርጫ ወቅት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀበት ወቅት የሚውል ከሆነ፣ የግድ (ወይም necessarily and automatically) ምርጫን ላለማድረግ ምክንያት ይሆናል ማለት አይደለም።

ለጤና ሲባል የታወጀ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታም፣ ምርጫን አያስቀርም–በግልፅ፣ በሳይንስ በተደገፈ መልኩ፣ አዋጁን ያስገደደው ምክንያት፣ ከምርጫ ሂደት ጋር ተጨባጭ ግንኙነት እንዳለው ካልተረጋገጠ በቀር።

5. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመኖሩ ምክንያት የሚገደቡ መብቶችና ድንጋጌዎች እንዳሉ ግልፅ ነው። የማይገደቡም መኖራቸው አይታበልም።

ከማይገደቡ ድንጋጌዎች መካከል ደግሞ አንቀጽ አንድ ዋነኛውና የመጀመሪያው ነው።

በዚህም መሠረት፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም፣ የአገረ-መንግሥቱን ዴሞክራሲያዊና ፌደራላዊ አወቃቀር መንካት አይቻልም።

ምርጫን በማራዘም፣ ባልተመረጠ መንግሥት ለማስተዳደር መሞከር፣ ዴሞክራሲያዊ አወቃቀሩን፣ ከመሠረቱ መናድ ነው። አይፈቀድም። አያስኬድም።

በተመሳሳይ መልኩ፣ ክልሎች፣ ምርጫ በማድረግ እራሳቸውን የሚያስተዳድሩበትን መንግሥት እንዳያዋቅሩ ማገድ፣ የፌደራላዊ አወቃቀሩን በመናድ፣ ወደ ተማከለ አምባገነናዊ ሥርዓት መመለስ ነው። ይሄም አይፈቀድም። አያስኬድም።

በበሽታ ምክንያት በታወጀ (ያውም በበቂ የህግ አግባብ እንኳን ባልታወጀ) አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም፣ የአንቀጽ አንድን ድንጋጌ መተላለፍ፣ በአንቀጽ አንድ ብቻ የሚያቆም አይደለም። ሥልጣን የሕዝብ መሆኑን የሚገልጸውን የዴሞክራሲ መርሕ እና የብሔሮችን ሉዓላዊነት መርሕ (አንቀጽ 8ን)፣ ሕገ-መንግሥታዊነትን (አንቀጽ)፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብትን (አንቀጽ 39(1-2)፣ በፌደሬሽን ውስጥ እራስን በራስ ማስተዳደርን (39(3))፣ ወዘተ ይጥሳል።

አንዳንድ የብልጥግና ፓርቲ አጨብጫቢዎች፣ “በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ ስላለን፣ በአንቀጽ 38 የተደነገገውን የመምረጥና የመመረጥ መብት መጣስ ስለሚቻል፣ ምርጫን በአስቸኳይ ጊዜ ሥም ማራዘም ይቻላል” እያሉ ሲከራከሩ ይሰማሉ። (ያላዋቂ ሳሚ ነገር!)

ስተዋል።

ምርጫን ማራዘም ማለት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣንን የሚጠቀመውን መንግሥት ሕጋዊነት እራሱ መናድ ማለት ነው።

ከላይ እንደገለፅኩት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣን መጠቀም የሚችለው የሥራ ዘመኑ ያላለቀ ፓርላማ የሰየመው ሕጋዊ መንግሥት ብቻ ነው። ከሥራ ዘመኑ ማለቅ ጋር ተያይዞ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሥልጣኑም ከዋናው የውክልና ሥልጣኑ ጋር ያከትማልና። ዋናው ሥልጣን ዘመኑ አልቆ ካበቃ፣ ተጨማሪው (የአስቸኳይ ጊዜ) ሥልጣን በምን አግባብ (በምን ላይ ተጨምሮ) ይቀጥላል? መልሱ ቀላል ነው፦ አይቀጥልም።

በተጨማሪም፣ ብዙ የዓለም-አቀፍ ሰነዶችም ሆኑ፣ ሰሞኑን አብይ እንኳን ለማጭበርበር ሲል የጠቀሰው የአፍሪካ የዴሞክራሲ ድንጋጌ (Declaration)፣ ምርጫ የሕዝቦች እና/ወይም የአገሮች መብት መሆኑን ያስቀምጣሉ። ሕዝቦች፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ (ማለትም፦ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ፉክክር ያለበት፣ ጊዜውን ጠበቆ፣ በመደበኛነት የሚካሄድ ምርጫ) የማድረግ መብት ከሌላቸው፣ ግለሰቦች፣ የመምረጥና የመመረጥ መብት አይኖራቸውም። The right of nations/peoples to democracy, or to a democratic election (i.e., the right to free, fair, competitive, and periodic elections), precedes the exercise of the right of individuals to vote (in order to elect or be elected).

አስተውል! በአስቸኳይ ጊዜ ሥም፣ ምርጫን በማራዘም የምትጥሰው፣ አይነኬውን የሕዝቦች የዴሞክራሲ መብት (ቁ. 1, 8, 9, 39 (1-3)) ነው። በአስቸኳይ ጊዜ ሥም የምትጥሰው፣ መሠረታዊውን የአገረ-መንግሥቱን ዴሞክራሲያዊ፣ ፌደራላዊ፣ ሪፐብሊካዊ አወቃቀርሩን (Structure) ነው። ይሄን በማድረግም፣ የቆምክበትን መሠረት ነው የምትንደው።

ይሄ ከዚህ በላይ ያለው ነው፣ ትክክለኛውና አዋጭ የሆነው፣ አወቃቀር ላይ የተመሠረተው የሕገ-መንግሥት አተረጓጎም (structural interpretation of constitutions).

(ስለዚህም መፃፍ ያስፈልግ ይሆን?)

Via: Tsegaye Ararssa


በአማራ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስድስት አመት እስራት የተፈረደባቸው አቶ በረከት ስምኦን በችሎት ተገኝተው ያሰሙት ንግግር:-
………….
⭕️ በፌደራል ሃላፊነት ላይ ሆኜ በአማራ ክልል ያልተሳፍኩበት የልማት መስክ አይገኝም። ከበረሃ ይዘናቸው በመጣነው አሮጌ መኪናዎች ባቋቋምነው ጥቁር አባይ ትራንስፖርት አፈር በመጥረግ ጥረት ኮርፖሬትን አቋቁመናል።

ከዛም አምባሰል የንግድ ስራዎች ድርጅት ፣ ጎንደር ዳሽን ቢራ ፋብሪካ፣ የብቅል ፋብሪካ፣ የቆርኪ ፋብሪካ፣ የሰሊጥና የማር ማቀናበሪያ ፋብሪካዎች፣ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካ፣ የሞባይልና የፍሪጅ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች፣ የጋርመንትና የብረታብረት ፋብሪካዎች፣ ደብረብርሃን ዳሽን ቢራ፣ ጨርቃ ጨርቅና ሌሎች ፋብሪካዎች፣ እንዲሁም የሎጅስቲክና ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎችን ጨምሮ በድምሩ 16 ፋብሪካዎችና 7 የአገልግሎት ኩባኒያዎችን አቋቁመን፣ ገንብተን አስፋፍተናል።

በሺህ ለሚቆጠሩ የክልሉ ስራ አጦች የስራ እድል ፈጥረናል። ጥረት ኮርፖሬትን በ20 ሚሊዮን ብር ካፒታል ከማቋቋም ጀምሮ የ11 ቢሊዮን ብር ባለሃብት በማድረስ ነው ከጥረት የተሰናበትነው።

ከዚህ በተጨማሪ በሌሎች የከልሉ ልማቶችም አገልግያለሁ።

⭕️ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም /አብቁተ/ን ያቋቋምነው እኔና ታደሰ ነን ። ከዚያም ታደሰ ለክልሉ ገበሬዎች በየገጠሩ እየወረደ የቁጠባና የብድር አገልግሎት በመስጠት የአማራ ገበሬን የደገፈ ተቋም እንዲሆን በማድረግ ከአፍሪካ ተሸላሚ ተቋም እንዲሆን አድርጎታል ።

⭕️ አልማን ሀ ብለን ያቋቋምነው እኔና ህላዌ ነን ።

የክልላችን አፈር እየተጠረገ ወደ ሱዳንና ግብጽ እንዳይሄድ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን አስፋፍተናል። ይህ ስራ ቀላል አይደለም። በጣም ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ከባድ ስራ ነው ።
በክልሉ የግብርና መስክም ከጽሁፍ ዝግጅት ጀምሮ ፣ በኦሬንቴሽን፣ በስልጠናና ትግበራ ክልሉን በማገዝ ያልተሳተፍኩበት ወቅት አልነበረም ።

ይሄን ሁሉ ስራ መስራታችንና ጥረት በአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በቀዳሚነት የተሰማራ ኮርፖሬት እንዲሆን ማድረጋችን እንዴት ተብሎ ነው “የአማራን ህዝብ ጥቅም ሆን ብለው በመጉዳት ከባድ ወንጀል” የምንቀጣው ?!

⭕️ በፌደራልም የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከባድ ሃላፊነት በመሸከም ተመድቤ የማነሳሳትና ገቢ የማሰባሰብ ሃላፊነቴን ተወጥቻለሁ።
በዚህ ሁሉ አገልግሎታችን የቅጣት መቅለል አይደለም ማናቸውም አይነት ቅጣት የሚገባን ሰዎች አይደለንም ።

⭕️ የጤንነታችን ሁኔታ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ለህይወታችን አስጊ ሆኗል፣ በአፋጣኝ ህክምና ማግኘት አለብን ።

⭕️ ቤት አልሰራሁም ። ከመንግስት የአንድ ካ.ሜ ቁራጭ መሬት አልወሰድኩም፣ በማገኘው ደመወዝ ቤት መስራት እንደማልችል አውቃለሁ ።
ከዚህ ሁሉ የ15 አመት ትግል ሜዳና የ27 አመት የክልሉና የፌደራል የሚኒስትርነት አገልግሎቴ በኋላ በ5.900 ብር ጡረታ የተሰናበትኩ ጡረተኛ ነኝ ።

ከጡረታ በኋላ ቤተሰቤን ለማገዝ ተዘጋጅቼ እያለሁ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ባለቤቴ እንደምንም ብላ እየሰራች ለአንድ አመት ተኩል ከአዲስ አበባ ባህር ዳር እየተመላለሰች ተሸክማኝ አለች።

በ19 አመቴ ነው ወደ ትግል የገባሁት ። ያኔ አድራሻው በማይታወቅ ጥይት እንደምሞት አውቄ ነው ወደ ሞት የመጣሁት ። አሁን በ62 አመቴ ሞት የምፈራ ሰው አይደለሁም ።

በእስር ቤት ውስጥ ተኝቼ ከማደር ውጭ ምንም አይነት የህሊና ፀፀት የለብኝም ።

⭕️ ነገር ግን ይህ ቅጣት ለኔ የሚገባ አይደለም ⭕️